ተስፋዬ ገብረአብ ከሚበጀው የሚፈጀው
ዓለማየሁ ገላጋይ
ጋዜጠኛና ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ ሰሞኑን የኖህን ልጅ ካምን ሆኖ ከረመ ማለት ይቻላል። አባቱ ኖህ በወይን ጠጅ ሰክሮ እራሱን በማይቆጣጠርበት ጊዜ እራቁትነቱን (ነውሩን) ያየውን ካምን… አይቶ ያልበቃውን፣ ወንድሞቹም የአባታቸውን እራቁትነት አይተው እንዲሳለቁ የጋበዘውን ካምን… ይህን በማድረጉም ዘር ማንዘሩ በአባቱ የተረገመውን ካምን… ተስፋዬ ሆኖ ከረመ። ካምን ለመሆን ህሊና ቢስነት እንጂ ሌላ ችሎታ አለመጠየቁን ተስፋዬ የተረዳው አይመስልም። ድፍረት እንጂ ብልሃት ግድ እንደማይል የገባው አይመስልም። ይህም በሚያቀርባቸው ቁንፅል ታሪኮች ላይ በጉልህ ይነበባል።
ተስፋዬ ገብረአብ ሰሞኑን ካምን የሆነው እንዲህ ነው። ባትወልደውም ያሳደገችውን አገር የታሪክ ጉንፍ እየገላለጠ እራቁትነት ለማየት እጅግ በመጣር ላይ ይገኛል። ለማየት መጣሩ ሳይበቃው ሌሎችም እንዲሳለቁ ‹‹የቅዳሜ ማስታወሻ›› ብሎ በሰየመው ብሎጉ በመጋበዝ ላይ ነው። በተለይ አፄ ምኒልክን፣ አፄ ኃይለሥላሴን፣ እቴጌ ጣይቱ እና እቴጌ መነን የቀጥታ ተጠቂ ለማድረግ ፍላጐት እንዳለው በጉልህ ይታያል። ከእነሱ በሰተጀርባ ደግሞ እኛን ኢላማ አድርጓል፡፡ ‹‹የንጉሠ-ነገሥቱ እናት››፣ ‹‹የጎጃም ልዕልት›› እና ‹‹የመነን አራተኛ ባል›› በተሰኘ ፅሁፉ እነዚህ አጤዎችና ንግሥቶች ላይ ቦጫቂ የንሥር ጥፍር የመሰለ ብዕሩ ሲያንዣብብ በገሃድ ይስተዋላል። እንዴት? ለምን? ምን ፍለጋ? ምን ለማትረፍ? ይሄን ከመፈተሻችን በፊት ተስፋዬ ገብረአብን በጥቂቱ ለማየት እንሞክር።
የማይታበለው ነገር ተስፋዬ ገብረአብ ለአማርኛ ሥነ-ፅሁፍ ባለውለታ ነው። ‹‹ያልተመለሰው ባቡር››፣ ‹‹የቢሾፍቱ ቆሪጦች›› እና ‹‹የቡርቃ ዝምታ›› የተሰኙ ልቦለዶቹ እንደውርዴ ከወላጆቻቸው የወረሱት የዘር ጠባይ ቢኖርባቸውም የትረካ ጥበባቸው ቅርሳችን መሆኑን መካድ አይቻልም። እንዲሁም ሁለት ‹‹ባለቅፅ›› መጽሐፎችንም አበርክቶልናል። ‹‹ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ›› እና ‹‹እፍታ›› የተሰኙት እነዚህ ‹‹ባለቅፅ›› መጽሐፎች ተስፋዬ የጡት አባት ሆኗቸው በጉዲፈቻነት ባያሳድጋቸው ኖሮ ምናልባትም የሥነ- ፅሁፍ አፀድ ውስጥ የማይቀበሩ በጨቅላነት የተቀጠፉ በሆኑ ነበር። ከእነዚህ ሁሉ በኋላ ደግሞ ሁለቱ ‹‹የጋዜጠኛው›› እና ‹‹የደራሲው›› ማስታወሻዎች ተከትለዋል። የዘር በሽታው ካንዱ ሥራ አንዱ የማይሻል ቢሆንም በሁለቱ ‹‹ማስታወሻዎች›› ላይ ተስፋዬ ለጋነቱን አጥቶ፣ እንደዛፍ ተንጋዶ መብቀሉ በጉልህ የሚስተዋልባቸው ሆነዋል።
የተስፋዬ ገብረአብ አብዛኞቹ ሥራዎች (ብሎጉን ጨምሮ) እንደ ገጠር ሴትወይዘሮ መኳኳያቸው ‹‹ጥላሸት›› ነው። ‹‹ጥላሸቱ›› ደግሞ ከስም ማጥፋት ጥቀርሻ የሚገኝ ነው። ይሁንና ሥራዎቹ ገና በፈገግታ ሲቀርቡን ጉራማይሌአቸው የጥላሸት እንዳልሆነ ሁሉ በውበት ይጠልፉናል። ተስፋዬ ‹‹የሚነቅስበት›› የራሱ የሆነ የቋንቋ እሾህም አለው። እየጠቀጠቀ ከሚያደማው ‹‹ድድ›› ሆነ ‹‹አንገት›› ውስጥ ከማዝጐርጐር የሚመነጭ ውበት ያፈልቃል። ይሄንን ደግሞ ተስፋዬ ያውቃልና የስም ማጥፋት ጥቀርሻውን ሆነ መጠቅጠቂያ እሾሁን አይጥልም። ‹‹የጋዜጠኛው ማስታወሻ›› ላይ ስለመኳኳያ ‹‹ጥላሸቱ›› እንዲህ ይላል።
‹‹በዚህ መጽሐፍ ባልተለመደ ሁኔታ እውነተኛ ስማችሁን ለተጠቀምኩ ሁሉ ባለማስፈቀዴ ይቅርታ እየጠየቅሁ፤ አትቀየሙኝም ብዬ በመገመቴ ደግሞ አመሰግናለሁ።››
ከእጅ ያፈተለከ የጫካ እርግብ ይመስል መጽሐፍን ያህል የረጅም ዘመን ነዋሪ በዘፈቀደ መልቀቅ ከባድ ጥፋት ነው። ተስፋዬ ገብረአብ ሆን ብሎ ለሰራው ጥፋት ይቅርታውን የጥፋቱ አባሪ አድርጐ መልቀቁ ደግሞ ትልቅ ሹፈት ይሆንብናል። ተስፋዬ የጥፋቱን ጥፋትነት ቀድሞ ቢረዳውም እራሱን ገስፆ መተው የሚችል አይመስልም። ምክንያቱ ደግሞ ግልፅ ነው። የተጋባበትን ሳይሆን የለማበትን አንጡራ ባህርይ ስለሚያስተናግድ ብቻ ነው። ልጅ ሆኖ በእናቱ ላይ ያደረገውን ‹‹የደራሲው ማስታወሻ›› ላይ እንዲህ ይተርክልናል። ንዑስ ርዕሱ ‹‹የልጅነት ተራሮች›› ነው።
የጓደኛው የነብዩ አባት ኢሬቻን ለማክበር ወደሆራ እየወሰዱአቸው ነው። መንገድ ላይ ስለክብረ በዓሉ መልካም መልካም ነገር ይነግሯቸዋል። ተስፋዬ በጨዋታው መካከል ገብቶ ‹‹እናቴ ግን እንዲህ አልነገረችኝም›› በማለት ክብረ- በዓሉን የሚያጥላላ ነገር ይዘበዝባል። የነብዩ አባት ይሄን በሆዳቸው ይዘው ወደ ተስፋዬ እናት ይሄዳሉ። በነገሩም ላይ ይነጋገራሉ። ሰውዬው ገና እግራቸው ከቤት እንደወጣ እናት ከጉማሬ ቆዳ የተሰራውን አለንጋ አንስተው ተስፋዬ ላይ ይወርዱበታል። ‹‹ስትገርፈኝ እንዲህ እያለች ነበር›› ይላል፡ -
‹‹የቤትህን ምስጢር ደጅ እያወጣህ ትዘረግፋለህ? ጅላጅል የሆንክ ፍጡር። ለሰው የሚነገርና የማይነገረው መቼ ይሆን የሚገባህ? በችግር ጊዜ ከሚደርሱልኝ፣ ተከባብረን ከኖርነው ጐረቤቶቼ ልታጣላኝ! ጅል!፣ ልጅ የሆንክ ፍጥረት…›› (ከገፅ 38-39)
ተስፋዬ ገብረአብ በመጽሐፎቹና በብሎጉ ሥማቸውን ካነሳቸው አራት ግለሰቦች ጋር በጉዳዩ ላይ አውርቼአለሁ። የእናቱን እሮሮ ነው ሁሉም የደገሙልኝ። በተለይ አንደኛው ‹‹ለምን እኔን ማጥቂያ ያደርገኛል? ስለምን ከሚጐዱኝ ሰዎች ጋር ያያይዘኛል?›› ነበር ያለኝ። ቀላል የሚመስሉ ግን ከባድ የሆኑ የእናቱ ሮሮዎች ተስፋዬ እስካለ ድረስ ለመቀጠላቸው ምንም የሚያጠራጥር ነገር የለበትም። እናቱ ካሉት ውስጥ ‹‹ጅል›› የምትለው ቃል ብቻ የምትታመን አይሆንም። እናት በመሆናቸው የልጃቸውን ጥፋት ከጅልነት ቆጥረውታል፣ ካልሆነም ተስፋዬ ለማደናገሪያነት እናቱ አፍ ላይ ቃሏን አኑሯታል እንጂ ተስፋዬ ጅል አይደለም። ውጤቱን እየገመተ ብቻ ሳይሆን ቀድሞ እያወቀ የሚያደርግ ለመሰሪነት የቀረበ ሰው ነው።
ተስፋዬ ገብረአብ የአካባቢ ተቆርቋሪ ይመስል ከውድቅዳቂ የታሪክ ፌስታል ቆሻሻ ኢትዮጵያዊ ዘንቢል የመስራቱ የሰሞኑ ሙከራ በጅልነት የተፈፀመ አይደለም። ያስወነጨፈብን ጫፉ የክፋት መርዝ የተቀባ የጠላትነት ቀስት ነው። በሚያመረቅዝ የሐፍረት ቁስል ሊመታን ሆን ብሎ የታሪክ ምሁራንን ከለላ አድርጐ ሰንዝሮብናል። ቁንፅል እውነታዎችን በመቅመል መላው ታሪካችንን የውቤ-በረሃ ገድል ሊያስመስለው ሞክሯል። ነገሥታቱን፣ መኳንንቱንና ሴትወይዘሮዎቹን ለድሪያ ብቻ የተፈጠሩ አሻንጉሊቶች በማድረግ ከኢትዮጵያ ውስጥ በታሪክ መኩራትን ጠራርጐ ለማጥፋት አልሞ አንዲት የዶሎዶመች ሙሬ አዘጋጅቷል።
ኢትዮጵያዊ የስብዕና ነውጥ በመሻት ከታሪክ ነቁጥ ተነስቶ የፃፈው አንዱ ሥራው ‹‹የንጉሠ ነገሥቱ እናት›› የሚል ርዕስ ተሰጥቶታል፡፡ የሚተርከው አጤ ምኒልክ ‹‹ከሥራየ ቤት›› (ገረድ) ስለወለዷት ሸዋረጋ ነው። ገና በእናቷ ሆድ ሳለች ከአጤ ምኒልክ እንደተረገዘች ያወቁት እቴጌ ጣይቱ ከቤተመንግሥት እንዳባረሯት ይተርካል። የሰባት አመት ልጅ ሳለች እናቷ ስለሞተችባት እንዴት የመከራ ጊዜ እንደገፋች ያጫውተናል። በመጨረሻ ወታደር አግብታ ሐረር ስትኖር የአባቷ ስም ማተቧ ላይ ተፅፎ በመገኘቱ ባሏ ወደቤተመንግሥት ያመጣታል። አጤ ምኒልክ ከልጃገረዶች መካከል ይለይዋታል፣ ለራስ አሊም ይድሯታል። በ1888 ዓ.ም. ልጅ እያሱ የተወለደው ከሸዋረጋ እንደሆነ ይነግረናል።
እዚህ የተስፋዬ ትርክት ውስጥ ፅሁፉን ወደ ውሸትነት ሊለውጥ የሚችል ከፍተኛ የዘመን ዝንፈት ይታያል። ሸዋረጋ ስትረገዝ እናቷን ከቤተመንግሥት ያባረሯት እቴጌ ጣይቱ እንደሆኑ በገደምዳሜ ተነግሮናል። እንዲያ ከሆነ ጉዳዩ የተፈፀመው ከ1876 ዓ.ም. ወዲህ ነው ማለት ነው። ምክንያቱም እቴጌ ጣይቱና አጤ ምኒልክ ተገናኝተው የተጋቡት በዚህ ዘመን በመሆኑ ነው። ሸዋረጋ እንደው ከአመት በኋላ ተወለደች ቢባል እንኳን ከ1877 ልጅ ኢያሱን እስከወለደች ጊዜ (1888 ዓ.ም) ያለው ዕድሜ ገና አስራ አንድ ዓመት ብቻ ይሆናል። ተስፋዬ፣ ሸዋረጋ ወታደሩን ያገባችው ለአቅመ ሔዋን ደርሳ መሆኑን ደግሞ ነግሮናል። ታዲያ እንዴት በአስራ አንድ አመት ዕድሜዋ ልትወልድ ቻለች? ድሎት በዝቶ የሴት ወጓን ቀድማ አየች እንዳይባል ሸዋረጋ በችግር ተቆራምዳ ያደገች ናት። ታዲያስ? እንዴት? በምን?...
ሙግት እንጂ ስድብ በመረጃ አይደገፍም። ተስፋዬ ገብረአብ ከዘመኑ አፋትቶና አፍኖ እዚህ ዘመን ያመጣው ታሪክ ለዚህ ትውልድ ነውር የሚመስል ጥቃቅን ነገር ስላለበት ብቻ ሙሉ ትኩረቱን የሰጠው ታሪኩን አቅርቦ አንጡራ ኢትዮጵያውያኑን ማሸማቀቁ ላይ ነው። ከዚያም ኢትዮጵያዊ ኩራትን ሰብሮ ሀገር ተከላካይነትን ማዳከም። ከዚያስ?
ተስፋዬ ገብረአብ ታሪካችንን ከክብሩ አውርዶ የሴትና የወንድ ‹‹ሎሚ ውርወራ›› ብቻ ለማስመሰል የጣረው ተደጋጋሚና አንድ አይነት ቁመና ያላቸውን ታሪክ ነክ ፅሁፎች በማቅረብ ነው። ‹‹የጎጃም ልዕልት›› የተሰኘው ፅሁፉ በንጉሥ ተክለኃይማኖት ልጅ የተነሳው መኳንንታዊ የጋብቻ ውርክብ እንዴት ለአጠቃላይ ጦርነት አስግቶ እንደነበር ይተርክልናል። በመጨረሻ አጤ ምኒልክ እንዴት እንደቋጩት ይነግረናል። ከቁመታቸውም፣ ከወርዳቸውም ቀናንሶ ለመፍጠር የፈለጋቸውን አጤ ምኒሊክ በዘዴ ያስተዋውቀናል።
‹‹የመነን 4ኛ ባል›› የተሰኘ ፅሁፉ ደግሞ ያነጣጠረው አጼ ኃይለሥላሴ ላይ ነው። መነን በፊት ሁለት አግብተው ፈትተዋል ይለናል። ልጆችም አሏቸው። በኋላ ሦስተኛ ትዳራቸው ላይ ሳሉ ነው ልጅ ኢያሱ አፋትቶ ለራስ ተፈሪ ሲድራቸው የምንመለከተው ‹‹አምላክ በዚሁ በቃሽ ይበለኝ›› በማለት አራተኛ ትዳራቸውን የተቀበሉት እቴጌ መነን ዘመኑና ዘመነኞቹ ያደረሱባቸው ‹‹ጥቃት›› አጥንታችንን ሰርስሮ ይገባል። ይሄ እንግዲህ ተስፋዬ ገብረአብ ቆንፅሎ እንዳቀረበው ሁሉ ነገሩን ከሁኔታዎች ነጥለን ስንመለከተው ነው ሀፍረት እንዲሰማን የምንሆነው። ከዚያ ውጭ ግን ነገሩ ሌላ ነው። የዚያ ዘመን ፖለቲካዊ ሀይል የሚመነጨው ከዘር ብቻ ነበር። በመሆኑም አካባቢዎችና ግዛቶች ከማዕከላዊ መንግሥት ጋር ተሳስረው የሚቆዩት በፍትሃዊ የበጀት ክፍፍል ሳይሆን በሚዛናዊ የትዳር ስርጭት ነበር። ሁሉም አካባቢና ግዛት የጋብቻ ዝምድናንና መዋለድን ለዙፋኑ የነገ ተስፋ በዋስትናነት ከያዙ ብቻ የሰላሙ ተባባሪዎች ናቸው። ስለዚህ በንጉሠ ነገሥቱና በመኳንንቱ አካባቢ የነበሩ ሴቶች እንደ ዋነኛ የፖለቲካ መሣሪያ መታየታቸው ግድ ነበር ይሄ በእኛ ብቻ ሳይሆን በአውሮፓውያን ታሪክ ውስጥ ቦታ ያለው ክስተት ነበር። የሔነሪ ስምንተኛን ታሪክ ማንበብ በቂ ነው።
የተስፋዬ ገብረአብ በዚህ ዘመን አስተሳሰብ ለማስዳኘት ከታሪክ ጋር የመካሰስ አዝማሚያ ጅልነት ሳይሆን፣ መሰሪነት እንዳለበት እንድንጠረጥር የሚያደርገን ይሄ ነው። ተስፋዬ ያለጥርጥር ከታሪክ ነቁጥ ኢትዮጵያዊ የስብዕና ነውጥ ለመፍጠር በመሞከር ላይ ነው። በተስፋዬ ገብረአብ መስገር ሁልጊዜም የሚፈልገው ቦታ የሚደርሰው ጀርባውን የተከራየው አካል እንደሆነ ግልፅ ነው። ተስፋዬ የራሱ መዳረሻ የለውም። ተስፋዬን እዚህ ታሪክ የመቅመል ሥራ ውስጥ የከተተው ጀርባን አከራይቶ የመኖር ፈረሳዊ ጣጣ ነው። ጋላቢው መንፈስ በግልፅ እኔ ነኝ ባይልም ከተስፋዬ አሰጋገር አስጋሪውን መለየት የሚያዳግት አይደለም። ግን… ግን ተስፋዬን ያለጋላቢ የማይሰግር ‹‹የጋማ-ከብት›› አድርጐ አጉልኛ የገራው ማን ይሆን? እሱ እንደሚለው ባንወልደውም አሳድገነዋልና ጀርባን አከራይቶ የመኖር ፖለቲካዊ ስብዕናው የእኛም መሰደቢያ ገመና ሳይሆን ይቀራል? ‹‹አሳዳጊ…›› በሚል የገመና ተጋሪዎቹ መሆናችን እርግጥ ነው፡፡

Comments
Demerew Abera (not verified)
Sat, 07/07/2012 - 13:34
Permalink
niece piece!
Thanks for the nice piece. Tesfaye is a cheap and venomous personality who calls himself 'gazetegna'. Please try and translate the article in this link - http://www.bbc.co.uk/news/science-environment-18526428 - for him for he cannot understand it. Neither do i think he appreciates the significance of it anyway.
As you rightly put it, Tesfaye grew up as a 'foreigner' /Eritrean in Ethiopia, his young mind being poisoned by his parents about how bad and inferior Amharas and Ethiopians were. Because of his poor upbringing and infantile personality, Tesfaye could not manage to do anything that would help him support himself. Desperation sent him to the Derg army. Once there he started working for Shabiya in earnest, which planted him within Woyane. His negative upbringing, Shabia and fate led him to who he is now – a negative, coincidence-less, and opportunist personality. Unfortunately, gullible Ethiopians and some opportunist ‘opposition’ groups try to make him what he is not. The true Tesfaye is someone who grew up hating Amharas, in particular, and Ethiopians, in general. He is badly crooked personality due to these and he is and will remain an enemy of Ethiopia and Ethiopians.
Anonymous (not verified)
Sat, 07/07/2012 - 16:11
Permalink
Well said.
Well said.
ንጉስ (not verified)
Sat, 07/07/2012 - 20:27
Permalink
ሙጀሌውን በነቀሰበት መርፌ ታሪክ የሚነቅስ አተላ-ተስፋየ ገብረአብ(ቶፋየ ገብረእብድ)
ተስፋየ ገብረአብ:
ንጉስ ለመሆን የመ'ቀደስና የመ'ወለድ ጉዳይ ስለነበር-ለሶስት ሺህ አመታት:: እሱ እዛ ጎራ ባለመሆኑ የቤተ-መንግስቱን ግቢ አለማወቁ ብቻ ሳይሆን ፈጽሞ አለማሰቡ ጥሩ አስጋሪ ሳይሆን መሀል ሰፋሪ አገናኝ ጋላቢ ባለማግኝቱ ጀርባው ለጭነት በመከራየቱ ላምባዲና እየተሞላ በ"ፋርሱ" መታጠብ ያስፈልገዋል-አጣቢ ቢጤውን ካገኘ አልያም አፍንጫው በጉንፋን ስራውን ያቆመ-ሌላም ሰው ቢሆን!! " አህያ ባልዋለበት ፋንድያ....." እንዲሉ አካባቢው ምን እንደሆነ አስቦ የማያቅ "የጋማ ከብት" ስለምን ታወሰው ዛሬ? ተጭኖ እንዳንል አጤወቹም ሆኑ እቴጌወቹ ስድር አፍንጫ የነበራቸው ስለነበሩ በዚህም አያስኬደውም:: በዚህ አይነት ኩንቢውን የሚወጥረው የቅርብ ጊዜ ሁሉን እሺ ባይ የማጀት ሰገራ እንኳን ከማጀት ወጥቶ አስጋሪ የናቀው የ"ጋማ-ከብት" ለመሆን አበቃው ብለን ስለመፈጠሩ እንኳ እንደማናቀው ብናልፈው ይሻላል እንጅ እሱማ ሁሌም ጭነቱን ማራገፉ የተፈጥሮ ጠጋው ነው-ያው ቢያራግፈውም መልሶ ይጫናል እንጅ::
ነጭ ወረቀት ዘርግቶ የብዕሩን አፍ ያናፈጠ ሁሉ ጸሀፊ ቢባል ኖሮ: የጋማ ከብትም መሀንዲስ ይባል ነበር-ከፋንድያ በሚሰራው ቤት!
መሆን ስለማትችል ብቻ በቅናት ሌሎችን መራገጥ ተገቢ አይደለም-ማነህ የገብረአብ ጅል:: ባንተ ግን ማን ፈርዶ "እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አለች አህያ" ሆኖብህ አይደል!!!
Abel (not verified)
Sun, 07/08/2012 - 00:29
Permalink
የተስፋዬ ተንኮል
አለማየሁ፤ ግሩም አርገህ ስለ መለስክለት አመሰግናለሁ። መርዛማ ጽሑፎቹን ሲያወጣ-በተለይ በተከታታይ አጤ ምኒልክን በተመለከተ ሲያስነብበን፣ በአስተያየት መስጫ ሳጥኑ ውስጥ መልዕክት ልኬለት ነበር! አላወጣትም! ኮፒ ስላለኝ፣ እነሆ በዚሁ ላኳት! ተስፋዬም መጀመሪያ የብቻው ያነበባትን-አሁን ደግሞ ከህዝብ ጋር፤ የሹፈት አስተያዬቴን እንዲያነብ ጋብዠዋለሁ!
-------
ርዕስ፡ አጤ ምኒልክን ከኢትዮጵያዊያን ልብ ማውጣት
ዓላማ
• አጤ ምኒልክ አፍሪካን ለመቀራመት ነጮች ያለሙትን ሕልም ስላከሸፉ፤ ትውልዱ የእሳቸውን ፈለግ እንዳይከተል ያልሆነ ስም መስጠት
ስልት
• በቀላሉ ሌሎች ኢትዮጵያውያን እንዲቀበሉት፡ የስም ማጥፋት ወንጀሉን በኢትዮጵያውያን ማድረግ
• በንግስናቸው ወቅት ወይም በዃላ በተለያዩ ጸሐፍት በቅናት፤ እንዲሁም ለተንኮል የተጻፉ ለማስረጃነት በማጣቀስ መጠቀም። ልክ አሁን ተስፋዬ ገብርአብ የሻቢያ ቅጥረኛ፤ ገብረ እባብ እየተባለ እንደሚጻፍበት። ዃላ የሚመጣው ትውልድ ሲያነበው ግን ሊመስለው ይችላል። ተስፋዬን የሚጠላም እኒህን ጹሑፎች በማስረጃነት እያጣቀሰ ሊያጥላላው ይችላል።
ለንባብ የበቁ መርዞች
እቅዱን ለማሳካት አጤ ምኒልክን በተመለከተ እስካሁን ልዩ ልዩ ጽሑፎች ለንባብ በቅተዋል። የሌሎችን ወደ ጎን ብንተዋቸው፤ በተስፋዬ ማስረጃ መሳይ መጣጥፎች እየቀረቡልን ነው። አንዱ በዚሁ ከላይ የአቀረበልን ነው። አሁን ያቀረበልንን ይዘቱን ብንመረምረው፤ አጤ ምኒልክ የበታቾቻቸውን ሹማምን እያስገቡ በዱላ የሚነርቱ ንጉስ እንደነበሩ አድርጎ ማቅረብ ነው። ታሪክ የሚነግረን ግን ስለ አርቆ አስተዋይነታቸው፤ ብልሕነታቸው ነው። እንኳንስ የሾሙትን፤ አልገብርም ብሎ ያመጸባቸውን ተዋግተው፤ ቆስሎ ሲማርኩት በሐዘኔታ ቁስሉን እያከሙ ይንከባከቡ ነበር። አንድ ሰው በእነድ ጊዜ ሁለት ሊገናኙ የማችሉ ዋ ጠባዮች አይኖሩትም። ትሕትናቸውን አንብበን፤ ተመረን ላደግነው አረመኔ ነበሩ ብሎ ለማቅረብ መሞከር ፍጹም ቅዠት ነው።
ሌላው ባለፈው በትዳራቸው ዋልጌ እንደነበሩ ቀርቦልናል። ከዚያ ቀደም ደግሞ የንጉሰ ነገስቱ እናት በሚል ከታሪክ ጋር ሊጣጣም የማይችል ተረት ተረት ቀርቦልናል።
ማጠቃለያ
እኒህ አጤ ምኒልክን በተመለከተ የሚረጩ በሬ ወለደ ይዘት ያላቸው ጽሑፎች አንባቢው 21ኛው ክፍለዘመን እንደሆነ የዘነጋ ይመስላል። የሰከነ አእምሮ ያለው፤ መረጃ በቀላሉ በማገላበጥ ምርቱን ከገለባ መለየት ይቻል። እናም ገለባ አቅራቢዎች በከንቱ ባይደክሙ ይመረጣል። እምየ ምኒልክን ከኢትዮጵያውያን ልብ ለማውጣት መሞከር ከንቱ ድካም ነው። ስራቸው በምድር እንደ ፀሐይ የሚያበራን ንጉስ ለማራከስ መሞከር፤ ሕሊናን ማቁሰል ነው። ራስንም ለትችት አጋልጦ መስጠት ነው። በጣም የሚያሳስብ ጥያቄ አለኝ። ለምን ከአጤ ምኒልክ መውረድ አቃተህ? በአገር ቤት የተከፈተባቸው የማጥላላት ዘመቻ፤ ከአንተው ጋር መሳ ለመሳ መሆኑ ለምን ይሆን?
tesfaye shabiya new (not verified)
Sun, 07/08/2012 - 05:03
Permalink
Alemayehu tikikil bilehal
Alemayehu tikikil bilehal beteley ye burQa zimitan lanebebe sew tesfaye be ewinet man endehone Qulich argo yasayenal lemaninyawim betam enameseginalen bezihu yiQetil
Justice (not verified)
Sun, 07/08/2012 - 07:50
Permalink
smetawi anhun
Alemayehu Tshufh kelogic ybelt smetawinet ytaybetal.Tariku ewenet endalhone gn alasayehm.yengusan metfo tarik menesatu sleenesu yalen amelekaket yqensal enji keethiopiwinet kurat gar ayyayazm.keethiopiawinet gar kayayazkew BETAM TESASTEHAL.pls tshufhn weqesa atargew.
Misganaw (not verified)
Sun, 07/08/2012 - 13:03
Permalink
ጥሩ ምልከታ
'እሾህን በእሾህ' ይላል ያገሬ ሰው። የተስፋዬ መርዛማ ጥሑፎች-ማርከሻ አገኙ። ግለሰቡ፤ እየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ የእፉኝት ልጆች ብሎ ከወቀሳቸው መካከል አንዱ ሆኖ ይታዬኛል። እፉኝት የራሷ ባሕሪ አላት! ወደ ምድር ለመቀላቀል-ቤተሰቦቿ ማለቅ አለባቸው! ተስፋዬም ኢንዲሁ! አለም ውስጥ ለመታወቅ-ቤተሰብን የመብላት አባዜ አለበት! እፉኝት እናትና አባቷን መስዋዕት አድርጋ እንደምትመጣው-ተስፋዬም ኢትዬጵያን መስዋዕት እያደረጋት ነው። ኢትዬጵያን የመሰለች አሳዳጊ እናት ላይ መርዝ መነስነስ ለምን እንደፈለገ አይገባኝም! ሰው መርዝ እየረጨ እንዴት ይኖራል? ለዚህም አይነቱ ሰው፤ ማን ይሆን የሚመልስ ስል-ይሄው በአማዬሁ ገላገለን! በእርግጥ-ተስፋዬ እንዲህ አይነት ነገር ሲመጣበት ልክ እንደ እባብ ወደ መሬት ራሱን ይቀብራል። ዝም ይላል። ፈጣን ምላሽ አይሰጥም። ፍሬ ሐሳቡ ከተዘነጋ በዃላ ግን መርዝ የያዙ መልሶች ያመጣል። እስከ አሁን ድረስ ያዬነው ጠባዩ ይኸው ነው! መርዝ የሚረጨውን ብዕርህን እንደጨበጥህ፤ አምላከ ኢትዬጵያ የስራህን ይስጥህ! አለማዬሁ ብርታልን። የኢትዬጵያ አምላክ ይጠብቅህ!
Kassa (not verified)
Mon, 07/09/2012 - 10:10
Permalink
Tesfaye's writings
Good observation. This person should stop his evil act somewhere.Although you expose his mistakes in his writings he never accept even he knows his mistakes.He is very sure that there are number of innocent people who accept and think what he writes as true evidence and pass the information to others.This is the very systematic way Galabewochu Behizbachin wousti Yemitekemubet.Shame on him.He was grown up,educated by the wealth of this nation.Yemiasazinew Yenat tut nekash mehonu becha new...
anonymous (not verified)
Sun, 07/08/2012 - 18:17
Permalink
"... ባንወልደውም አሳድገነዋልና ጀርባን
"... ባንወልደውም አሳድገነዋልና ጀርባን አከራይቶ የመኖር ፖለቲካዊ ስብዕናው የእኛም መሰደቢያ ገመና ሳይሆን ይቀራል? " አንዳንድ ሰው ድፍረቱ ገደብ የለዉም: አሁን አንተ ማን ስለሆንክ ነው አሳዳጊ ቅብጥርሴ እያልክ ተስፋዬ ላይ ምላስህን እምታረዝመው : ማነው አንተን የአትዮጵአዊነት ሰጭና ከልካይ ያደረገህ ?
Tulu Forza (Austria) (not verified)
Sun, 07/08/2012 - 20:31
Permalink
"ገብረ እባብ፤አልቦ ክታብ"
እነ መለስ ዜናዊ እንኳን፤ ለ ዓመታት ያለማቋረጥ የዘመቱበት ኢትዮጵያዊነት፤ “ወይ ፍንክች” ብሏል። ራሱ መለስ ኢትዮጵያዊነትን “በህዳሴ” ጠበል ሊያለመልመው ተነስቷል እንጂ፤ እንደቀድሞው “ሲያብጠለጥለው” እጅግም አይሰማ። “If you can’t beat them, join them” ብሎ ይሆን?። “ተራሮችን ያንቀጠቀጠው” ትውልድ፤ ኢትዮጵያዊነትን ማንቀጥቀጥ ገዶት፤ አጀንዳውን ቀይሯል። ዕድሜ ለጨዋ ኢትዮጵያውያን-- ከትግራይ እስከ ጋምቤላ፤ ከጎንደር እስከ ወለጋ፤ ለሚኖሩ፤ የእናት አገራቸውን ፍቅር ከ ወላጅ እናታቸው ፍቅር ለማይለዩ ጨዋ ሰዎች። ለእዚህም ነው የተስፋዬ ዱልዱም ብዕር እጅግም ዕንቅልፍ የማይነሳኝ። ምስጋና ግን ለአለማየሁ ገላጋይ፤ በተባ polemics የ“ገብረ እባብ፤አልቦ ክታብ”ን አንገት በአደባባይ ስለመታው። የማንም አገር ታሪክ በጎ እና በጎ የማይሰኝ ገጽታ እንዳለው እሙን ነው። ደጋግሞ የትኛውን የማንሳት ጉዳይ፤ የየግለሰቡ ምርጫ ጥያቄ ነው። ግን አለማየሁ እንዳስተዋለው፤ ይሄ ምርጫ የግለሰቡን ማንነት የማሳበቅ አዝማሚያ አለው። አገር ወዳዱ ባለቅኔ ፀጋዬ ገ/መድህን፤ በአንድ ወቅት ለምን ስለ አጼ ቴዎደሮስ በጎ በጎውን ብቻ ትጽፋለህ? ተብሎ ሲጠየቅ፤ “መጥፎ መጥፎውንማ፤ የኢትዮጵያ ጠላቶች ይጽፉት የለም ወይ?” ሲል ጥያቄውን በጥያቄ የመለሰው፤ ያለ ምክንያትም አልነበረም-- ያለ መላ።
Anonymous (not verified)
Sun, 07/08/2012 - 23:17
Permalink
Dear, Alemayehu!
Dear, Alemayehu!
free medians, journalist, and Ethiopian historian need come out to telling the truth as you do. so far you are the only one defend our history and heroes. i was read the articles Ats Tedros Between you and Bewuketu Syume. you did good job. you won. as this New Articles what you Have Tesfay Gebrabe. i have been sick since i read his deferents untie Ethiopians articles. first of all he his not Ethiopian. if there are Ethiopian they need come out defend his poisons historys. this war need knowledge and pane. not weapon. Why Tesfaye did what he does? Remember when Tesfye was Derg Army he was spay for shabia, He was working as Weyane Cadre journalist. if he talk those positions he had, we may get some thing we don't know. we never been spay or weyane cadre. about Ethiopans kings Minilek or others we are Ethiopians we know more than he does. Alemayehu i hope you will do more job about this Articles. there is good say. " Awera Enqawan Wedagen Ayebelam" he is worst than Awera Ethiopia Feed, rise and educated him. he didn't appreciate what he got. the word he use to attack as our fedel amargna Ethiomeian langue there nor worst than this.
wanka (not verified)
Mon, 07/09/2012 - 01:44
Permalink
Tesfaye is anti ethiopia we
Tesfaye is anti ethiopia we all know that thank u Alemayehu keep up the good worke
tebebe (not verified)
Mon, 07/09/2012 - 03:13
Permalink
Too late to know him!
Too late to know him!
netsanet (not verified)
Mon, 07/09/2012 - 09:18
Permalink
dear Tesfaye
Tesfaye i feel you are someone who lacks the meaning to life. you live in misery. you don't know who you are, you have no culture, history and identity. i doubt you read half or all of the stuff you put out(write) its a shame you are still not aware of the fact that Ethiopian history is powerful and deep and cannot be erased or rewritten. dear, Teafsye i hope and pray you will come to your senses and realize that Ethiopian history is none like other and that were all blessed to be a part of this holy nation.
Kassa (not verified)
Mon, 07/09/2012 - 10:08
Permalink
Tesfaye's writings
Good observation. This person should stop his evil act somewhere.Although you expose his mistakes in his writings he never accept even he knows his mistakes.He is very sure that there are number of innocent people who accept and think what he writes as true evidence and pass the information to others.This is the very systematic way Galabewochu Behizbachin wousti Yemitekemubet.Shame on him.He was grown up,educated by the wealth of this nation.Yemiasazinew Yenat tut nekash mehonu becha new...
tamrat tesfaye (not verified)
Mon, 07/09/2012 - 11:09
Permalink
wrong
u guys wht i want to say is,tesfaye writes wht he read and saw.......wht is z matter with u man.......he is unique.......i am fallin in love with his books.......endmibletehe emne.....
Anonymous (not verified)
Mon, 07/09/2012 - 11:17
Permalink
tesfaye is right!
bravo tesfaye! long live tesfaye gebreab!
balcha (not verified)
Mon, 07/09/2012 - 13:18
Permalink
ይድረሰ ለተስፋዬ
ተስፋዬ የራሱ መዳረሻ የለውም። ተስፋዬን እዚህ ታሪክ የመቅመል ሥራ ውስጥ የከተተው ጀርባን አከራይቶ የመኖር ፈረሳዊ ጣጣ ነው። ጋላቢው መንፈስ በግልፅ እኔ ነኝ ባይልም ከተስፋዬ አሰጋገር አስጋሪውን መለየት የሚያዳግት አይደለም። ግን… ግን ተስፋዬን ያለጋላቢ የማይሰግር ‹‹የጋማ-ከብት›› አድርጐ አጉልኛ የገራው ማን ይሆን?
ጸረ ባንዳ ፍሊት (not verified)
Mon, 07/09/2012 - 15:19
Permalink
ለባንዳው ዓሳ፤ የመንጠቆ ብእር ያስፈልገዋል!
ተስፋዬ ባንዳነት እየጨቆነ ያሰቃየዋል። ከዚህ ስቃይ ደግሞ ጥቂት እረፍት ለማግኘት የመተንፈሻ ስንጥብ /gill/ በመፈለግ በኢትዮጵያዊ ታሪኰች ውስጥ ዓሳ ሆኖ ለመዋኘት ይፈልጋል። ችግሩ ተስፋዬ ባንዳ ነው። የባንዳ ስንጥቡ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ባህር ውስጥ ለመዋኘት የሚስማማ ስላልሆነ ጽሁፎቹ ሁሉ ትንፋሽ ያጠራቸውና አፍንጫውን ያፈኑ ሆነው ማንነቱን የሚያጋልጡ ናቸው። የባንዳነቱ ስንጥብ በዓሳነት እንደማያስዋኘው ሲያውቅ ደግሞ ሰዎች በሱ ጽሁፍ ለመልስና ለትችት ጊዜ ሲወስዱ በማየት የባንዳነት እፎይታውን ለማጣጣም የሚፈልግ ጅል ነው። አንድ ሰው በታሪክ ውስጥ ግብሩ ትክክል ላይሆን ይችላል፤ ሕዝብ ግን መቼም ተሳስቶ አያውቅም። የሰዎችን የታሪክ ስህተት እየነቀሱ፤ በህዝብ ላይ ለመደረት ወይም ሰዎችን እንዲያቆሽሹ ለማሳሰብ መሞከር የጨቀየ አእምሮ ውጤት ነው። ለታመመ ሰው መድኃኒት ይፈልጉለታል እንጂ የህመሙን ጽናትና ጥልቀት እያነሱ ህመሙን እያሰበ እንዲያለቅስ አይቀሰቅሱበትም። ባንዳዎች ግን ድክመቶቻችንን እያነሱ ሊያሳምሙን ይፈልጋሉ። ቀደምት ሰዎቻችንን እስከነድክመቶቻቸውን ተቀብለን የሰጡንን ጥንካሬ ለመጻዒ ብርታቶቻችን እንዳንጠቀም እንድንጸየፋቸው የሙት ከፈናቸውን ሊገልጡልን ይፈልጋሉ። ለዚያውም ዛሬ በተደራረበ ውርደት ውስጥ እያለንና ከቀደምት መሪዎቻችን የጥንካሬአቸውን መንፈስ በመበደር መጠንከር በሚገባን ወቅት ላይ «ቆሻሾቻችሁን ተመልከቱ!» ለማለት ባንዳዎች ሲፈልጉ ማየት ያስገርማል!! በእርግጥ አያሳዝንም፤ አያበሳጭምም። ምክንያቱም የባንዳ ሀገሩ ሆዱ ነው። የባንዳ ጭንቅላቱ ስጋትና ፍርሃት ነው። የባንዳ ተልእኰ ዋጋ ካወጣች እናቱንም ቢሆን መሸጥ ነው። ስለዚህ እርባና በሌለው በባንዳው ተስፋዬ ሳንገረም፤ በጽሁፉ ስንጥብ በኢትዮጵያ የታሪክ ባህር ውስጥ ለመዋኘት ሲፈልግ እንደዚህ እንደ ዓለምአየሁ ቀዛፊው ብእር፤ መንጥቆ በማውጣት ዓሳው ይሞት ዘንድ ለጸሀይ አጋልጦ መስጠት ይገባል።
Jabo (not verified)
Mon, 07/09/2012 - 15:59
Permalink
Menelik-the barbarian
I really liked what Tesfaye wrote. He is great. The so-called Atse Menelik is a barbarian who killed many Oromos and Aderes. You may call him 'Imeyie' but Oromos call him 'Hattuu Loonii' and rememebers him by what he have done in Anole, Arsi and Chelenko, Harar. Two thumbs up for Tesfaye. Keep up writing the true History of Ethiopia.
dear jabo (not verified)
Tue, 07/10/2012 - 09:02
Permalink
temokro, temokro aktoal.
temokro, temokro aktoal. IMIYE MENELIKIN ke Ethiopian leb west mawtat ayechalem. beziya zemen alem syneka hagerachewn tebekew yakoyu asteway abat neberu. ahun esachew eyemerun behon noro endi be fereng baltedeferen. manbeb kemezebarek yadenal selezi tarikehen anbeb eshi.
በለው (not verified)
Tue, 07/10/2012 - 15:14
Permalink
ያኔ 100% ትክክል ነው፤ ዛሬ 100% ትክክል አይደለም።
አጼ ምንሊክ ኢትዮጵያን በሁለት እግር ለማቆም ብዙ እንቅፋቶችን ነቅለዋል፤ ሲሄዱም ሆነ ሲጓዙ ብዙ እሾህ ነቅሰዋል። እንቅፋቶቻቸውንና የሚወጓቸውን እሾሆች ሲነቅሉ የጉዳት ሰለባ እንደሚኖር ሳይታለም የተፈታ ነው። ያ የሚጎዳው የንጉሥ እንቅፋት ደግሞ ሕዝብ ነው። ያንን ካላደረጉ ደግሞ ፊውዳላዊ ንጉሥታቸው ምኑ ላይ ነው? ፊውዳላዊ ንጉሥ ማለት የወደደውን በውድ፤ እንቢ ያለውን በግድ የሚያስገብር ገዢ ማለት ነው። አራት ነጥብ።
የግልና የቡድን መብት የተከበረበትን ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ከፊውዳላዊ ነገሥታት እጅ ጠብቀህ ከሆነ ጅል ነህ። ጥላውን እያየ ወዲህና ወዲህ የሚንቀሳቀስ ጅል!!
ጀርመንን ኦቶ ቨን ቢስማርክ፤ ኢጣልያንን ጁሴፔ ማዚኒ እንዴት አድርገው እየጨፈለቁና እየገደሉ ዛሬ ያለችውን ጀርመንንና ኢጣሊያን እንደመሰረቱ ታውቃለህ? ሰው መግደል ጥሩ አለመሆኑ ይታወቃል። ሀገር ለመመስረት ግን አድርገውታል። ያንን ያደረገው የሥርዓት አስተሳሰብ ነው።
በኢትዮጵያችንም «ሃርካ ሙራ፤ ሃርማ ሙራ» በአኖሌ፤ የጨለንቆ እልቂትም ሁሉ የፊውዳላዊ ሥርዓት መገለጫዎች ሲሆኑ የድርጊቱ ችግር በሥርዓቱ አስተሳሰብና በሰዎች ላይ ባለው ኃይል ይገለጻል። የባሪያ ሽያጭ ህጋዊ የነበረበትን ዘመን ወደኋላ በመመለስ ገዢና ሻጭን ዛሬ ላይ መጠየቅ ጅልነት ነው። ስህተቱን በተስተካከል የስርዓት አስተሳሰብ ከመለወጥ ባሻገር ያለፈውን አስተሳሰብ በዛሬ ሚዛን መለካት ከጭንጫ አእምሮ የሚወጣ ነው።
ሳጠቃልል የአፄውን የቀድሞ ድርጊት በያኔው አስተሳሰብና የያኔው ሰው ሆነን ስንመለከተው ከምንም በላይ ትክክልና አስፈላጊ ሲሆን፤ በዛሬው ዘመን ላይ ያንን ለመተግበር በመሞከር ወደዚህ ብናመጣው ግን ወንጀልና ኢ- ሰብአዊነት የተሞላበት ይሆናል። አራት ነጥብ።
Mike (not verified)
Mon, 07/09/2012 - 16:46
Permalink
Thank you Alemayehu,
Thank you Alemayehu,
Tesfaye has got a sinister mitive to stir up hatread among Ethiopian Ethnic groups, and to degrade Ethiopian kings. Most of his articles very poisnous. What strikes me most is that the Ethiopian websites are giving him a platform so that he can spread his wicked ideas. Alemayehu, I appreaciate you for you adressing the feeling that have been harbouring for quite some time.
selam (not verified)
Tue, 07/10/2012 - 05:46
Permalink
I agree with you. This guy
I agree with you. This guy Tesfaye is a grass snake. What baffles me is why the Ethiopian websites and ESAT radio give him the plat form to spread his venom. If our history needs to be told, we have well educated historians who can put things in perspective, not this high school drop out grass snake. Shame on Ethiopian sites who publish his garbage.
desu (not verified)
Mon, 07/09/2012 - 18:40
Permalink
THank you for good
THank you for good understanding about him.Really what is he doing still he has other agenda to destoyed this country
አለም (not verified)
Mon, 07/09/2012 - 18:42
Permalink
እንዲህ ገላግለን እንጂ
ዓለማየሁ ገላጋይ፣ ከዚህ ሰው ድብቅ አጀንዳ እንዲህ ገላግለን እንጂ።
mezidmo (not verified)
Mon, 07/09/2012 - 23:40
Permalink
tegsat
enante yemeselachun endemtawerut esum yemeselewn endil....... lemawared kemnmocr lnmelsew bntr (bebahlachn)
Boruu Hussein (not verified)
Tue, 07/10/2012 - 07:11
Permalink
Tesfaye keep writing. The
Tesfaye keep writing. The Amhara elites have always been defending injustice. Tesfaye keep writing and exposing them. They have always been saying we are one people. That is false. We have been forced to stay together by previous and current repressive regimes. We are like bees and ants and cannot coexist. The solution is separation. This problem, for instance, in Wollo over 4oo years, and other Oromo
areas is over 100 years.
We cannot go on like this. We have the Gadaa System, and we want to practice it. Period. We are tired of hearing this fake Ethiopianism. Keep the name 'Ethiopia' in the museum as M. A. said. When a husband and wife cannot hammer out their difference, the only option is divorce. We, Oromo people, do not want those people who are singing day and night Ethiopianism. Keep it to yourselves; do not impose on us.
netsanet (not verified)
Tue, 07/10/2012 - 14:24
Permalink
dear boruu hussein
Amhara elities??!!? what in Gods name r u talking abt?? no race in Ethiopia is elite. y do u bother writing such garbage?! listen, Ethiopia is and will always be 1 nation. no one ,nothing will separate us.gena yetesenetekewn engetemalen!!!bzw Ethiopianisim is the spirit that freed z rest of Africa from colonial rule. u r an Ethiopian 4 God's sake! where is ur pride?
ሁልጊዜ (not verified)
Tue, 07/10/2012 - 15:30
Permalink
አንድ እውነት አለ። የሰዎች ዲሞክራሲያዊና
አንድ እውነት አለ። የሰዎች ዲሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶች መከበር እንዳለበት የመስማማት ጥቅል ሃሳብ እና ያንንም ለመተግበር በጋራ የመታገል ሰውኛ አስተሳሰብ። በዚህ ዙሪያ ኦሮሞም ይሁን ሌላው ሕዝብ ሊታገል ይገባዋል። ከዚያ ባሻገር ኦሮሚያን እገነጥላለሁ የሚል እሳቤ ከጠባቦች አእምሮ ባይጠፋም እንደ ሀገር ኦሮሚያን አቋቁማለሁ የሚል ጭቃ አስተሳሰብ ግን በየትኛውም አመክንዮ በተግባር የሚረጋገጥ አይሆንም። ምክንያት፤
1/ የህዝቦችና የብሔረሰቦች ስብጥር
2/ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥና ትስስር
3/ እገነጠላለሁ የሚል እንዳለ ሁሉ አልገነጠልም የሚል መኖሩ
4/ ከባቢያዊ ሁኔታ
5/ ሽብር እንጂ ያንን ለመተግበር የሚችል የኃይል ሚዛን አለመኖሩ
6/ የሕብረተሰብ አስተሳሰብ በለውጥ ውስጥ ያለ በመሆኑ
ከብዙ በጥቂቱ የሚነሱ ጭብጦች ናቸው። በየትኛውም ዓለም ተገንጥለናል ያሉ ሕዝቦች በዚህ መሰረታዊ ነጥቦች ላይ መፍትሄ መስጠት የቻሉ ናቸው። ከዚህ ውጭ የገዳ ስርዓት ህልም ጨረቃ ላይ ካልሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ መቼም አይመጣም። ህልም ግን ለእነ ቦሩ ሁሴን አይከለከልም።
ሄሌሌ ሀንባቤ (not verified)
Tue, 07/10/2012 - 10:16
Permalink
ተስፋዬ ገብረ አብ ያላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ለቅላቂ
ተስፋዬ ገብረ አብ የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት የለዉም። ደርግን ለመጣል በተደረገዉ ትግል ተስፋዬ ያደርግ የነበረዉ የካድሬነት ሙያ ከለብ ለብ ሰሚናርና ከሰርኩለር መረጃ ጥናት በስተቀር ዋጋ የሚሰጠዉ ትምህርት ቀስሞ አያዉቅም። ማርክስ እንዳለዉ፣ ሌኒን እንዳለዉ፣ መለስ እንዳለዉ እያሉ ከመለፈፍ በስተቀር የረባ የታሪክ ወይም የፖለቲካ ሳይንስ ትምህርት ቀስሞ አያዉቅም። ኢትዮጵያዉያን የምንኮራባቸዉና በዓለም ታሪክ የተዘገበላቸዉ ጀግና መሪዎች አሏት። የእነዚህ ጀግኖች ታሪከ የሚያበግናቸዉ ባንዶችና የምዕራባዉያን አጎብዳጅ ቡችሎች ዘወትር በተገኘዉ ቀዳዳ የጀግኖቻችንን ታሪከ ለማጉደፍ ከመፍጨርጨር ወደ ሗላ አይሉም። የታሪክ ቅናት ያበግናቸዋል። ተስፋዬ ገብረ አብ እነዚህን ከመሰሉ ባንዳዎችና ታሪክ አጉዳፊዎች አንዱ ነዉ። ወያኔ ሲተፋዉ ልክ ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ እንደሆነ አድርጎ ወያኔን የሚያጥላላ ጽሁፍ ጀመረ። ወንድ ከሆነ ለምን ኤርትራ ዉስጥ በኮንቴይነር እስር ቤቶች ዉስጥ ስለሚማቅቁት ኤርትራዉያን አይጽፍም? በእርግጥም ሙያተኛ ጋዜጠኛ ከሆነ በኤርትራ ዉስጥ ስለሚካሄደዉ የሰብአዊ መብት መጣስ ለምን አይጽፍም? ወጥ አዋቂ ቀለዋጭ ይመስል በበላበት ማሟሟቅ ይወዳል። ጣሊያኖች አፄ ሚኒልክን ከሚጠሉት በላይ ሆኖ ነዉ ተስፋዬ ጥላቻዉን በጽሁፍ የሚገልጸዉ። ስለኤርትራ ለምን አይጽፍም? በኢትዮጵያ ነገስታት ታሪክ ተለክፏል ወይ? ወይንስ በጻፈ ቁጥር ከኢጣሊያ መንግስት ጋኞታ ያገኛል? ያ ከሆነ ደግሞ “ቅጥረኛ” የሚል ቅጽል ስም ይለጠፍበታል። “ቂጥኛም ከዉርዴ” ነዉ የሚባለዉም እንዲህ አይነት ታሪክና ንክኪት ላላቸዉ ግለሰቦች የተተረተ ነዉ።
Finfinne oromia (not verified)
Tue, 07/10/2012 - 17:36
Permalink
Bravo tesfaye!
Tesfaye you did well. Expose them again. They all are haters. We love finfinne as much as we love Finfinne! Long live Tesfaye Gebreab!
Wodajo (not verified)
Thu, 07/12/2012 - 11:54
Permalink
Gebre Ebab bakeh sima
...አገር ወዳዱ ባለቅኔ ፀጋዬ ገ/መድህን፤ በአንድ ወቅት ለምን ስለ አጼ ቴዎደሮስ በጎ በጎውን ብቻ ትጽፋለህ? ተብሎ ሲጠየቅ፤ “መጥፎ መጥፎውንማ፤ የኢትዮጵያ ጠላቶች ይጽፉት የለም ወይ?” ሲል ጥያቄውን በጥያቄ የመለሰው፤ ያለ ምክንያትም አልነበረም-- ያለ መላ። This is more than enough to tell Ato Gebre Ebab who he is what he is doing!
habil (not verified)
Thu, 07/12/2012 - 12:09
Permalink
to these who encourage the evil
i wonder that there are also few evil who still can't understand who tesfay is. Tesfaye never worried me, coz i knew he is band, he is Eritrean who hate ethiopia and ethiopianism. What made me worry is that these who appreciate his poisonous entofento butuo fabrics.
Ashenafi Biramo (not verified)
Thu, 07/12/2012 - 16:09
Permalink
Complain
Alemayehu Gelagaye is always complainer to those who are out standing authors because he has to known by his complain.But his complain words is so beutful these may be psychological analysis efects.........
Add new comment