የህዝብ እና የተቃዋሚ ፓርቲዎች መንታ መንገድ

ተመስገን ደሳለኝ

የመኢአድ ም/ሊቀመንበር ዶ/ር ታዲዮስ ቦጋለ የመኢአድ ሊቀመንበር በሆኑት ኢንጂነር ኃይሉ ሻወል በተከሰሱበት ክስ ሁለት አመት ከስድስት ወር ተፈርዶባቸው ከርቸሌ ገቡ፤ መኢአድ እንደአንባሻ ተከፋፈለ፤ የማይለያዩት ኃይሉ ሻውል እና ማሙሸት አማረ ተለያዩ። አንድነት ፓርቲ ብርቱካን ሚደቅሳ ትፈታ ይል የነበረውን ጥያቄ አንዱአለም አራጌ ይፈታ በሚል ቀየረው፤ ብርቱካንን በማስብ ይበራ የነበረውንም ሻማ አንዷአለምን በማሰብ ይበራ ዘንድ ወሰነ፤ ብርቱካን ሚደቅሳ ስለኢትዮጵያ ፖለቲካ ልታጠና ዋሽንግተን ሄደች፣ ስዬ አብርሃ ለትምህርት ወደአሜሪካ ሄዱ፤ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ጀርመናዊ ህፃናቶችን ስለኢትዮጵያ ፖለቲካ ሊያስተምሩ ጀርመን ገቡ፡፡ ዶ/ር መረራ ጉዲና እና ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ዘንድሮም ሊቀመንበር ናቸው፤ ዘንድሮም ምክትል ሊቀመናብርቶቻቸው አይታወቁም። ሳሳሁልህ ከበደ ስልጣን ያዙ፤ አየለ ጫሚሶ ተባረሩ፡፡ ኢዴፓ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ትልቁ ችግር የአፍሪካ የሌብራል ፓርቲ ስብሰባን ያለማካሄድ ነው በሚል ቁጭት የአፍሪካ ሌበራል ፓርቲ ስብሰባ አዲስ አበባ እንዲካሄድ አደረገ፤ ልደቱ አያሌው ከፓርላማ ሲባረሩ ትምህርት ቤት ገቡ…. ከሞላ ጎደል ይህን ይመስላል ‹‹አጀንዳ አልባው›› የተቃዋሚ ፓርቲ ሠፈር አክራሞት።

እነሆ ዘንድሮም በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተያዘው የትግል ስልት ‹‹ኢህአዴግ አምባገነን ነው››፣ ‹‹ኢህአዴግ ምርጫ ያጭበረብራል››፣ ‹‹የፀረ-ሽብርተኝነት ህጉ አፋኝ ነው››፣ ‹‹ከኢህአዴግ አመራር በሙስና የተጨማለቀው ይበዛል››፣ ‹‹ሀገሪቱ በአውራ ፓርቲ መዳፍ ስር ወደቀቸ›› …ከሚል ማጋለጥ ያለፈ ሊሆን አለመቻሉንም እያየነው ነው፡፡ ይህ ደግሞ በተቃዋሚዎች ትግል የተገኝ ‹‹መረጃ›› ሳይሆን ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ጠንቅቆ የሚያውቀው ተራ ወሬ ነው፡፡

በእርግጥ በግሌ በሀገሬ ያሉ ሁሉም ተቃዋሚዎች ‹‹ከጥቆማ ያለፈ›› ትግል የማድረግ ወይ ወኔው የላቸውም፤ ወይ ብርታቱ የላቸውም ብሎ ለመደምደም ይቸግረኛል። በተለይ ደግም የተሻለ እንቅስቃሴ ሊያደርጉ የሚችሉትን አራቱን ፓርቲዎች እዚህ ውስጥ መደመሩ ለተቀማጭ ሰማይ… ይሆንብኛል፡፡ (አንድነት፣ መኢአድ፣ አረና እና ኦፌደንን ማለቴ ነው) ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ እንዳናጨበጭብላቸው የምርጫ ቦርድን የምዝገባ ሰርተፍኬት ታቅፎ ከመቀመጥ የዘለለ ስራ ሲሰሩ አይታዩም፡፡

በነገራችን ላይ ደጋግሜ እንደፃፍኩት ምክንያታቸው ምንም ይሁን ምን የተቃውሞውን ጎራ ለመምራት ወደ አደባባይ የወጡት ፖለቲከኞች በዛጎላቸው ከተሸሸጉት ‹‹ሌሎች ኢትዮጵያውያን›› የበለጠ ‹‹አክብሮት›› ይገባቸዋል። (ይሁንና ግን ሌሎች ኢትዮጵያውያኖች ማለት ምን ማለት ይሆን? እዚህ ውስጥ የሚመደቡትስ እነማን ይሆኑ? ከኢትዮጵያ ሌላ ትርፍ አገር ያላቸው ናቸው ወይስ የስርአቱ ምንደኞች?) ብቻ ከዚህ ባለፈ ክንብንባቸውን ገልጠው ፊታቸውን ያስመቱ ፖለቲከኞቻችን ለእስከአሁኑ አበርክቶታቸው ዋጋ ሊያገኙ ይገባል። በዚህ በኩል ችግር የለም፡፡ ችግር የሚኖረው ያ የአክብሮት ዋጋ በየአመቱ እየተመነዘረ ‹‹መሪ›› በሚል ስም ዛሬም በስልጣናችን እንደተቀመጥን መቀጠል አለብን ሲሉ ነው። ይሄ ወደድናቸውም ጠላናቸውም ትልቅ ችግር ፈጣሪ ነው፡፡ ምክንያቱም አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት አጣብቂኝ ከጥቆማና ከአጋላጭ ባለፈ ‹‹አንቂና አደራጅ›› መሪ የሚፈልግበት ወሳኝ ጊዜ ላይ ነውና።

እናም ማህተም እና የምርጫ ቦርድ ፈቃድ ያላቸው ፓርቲዎችን ብቻ ሳይሆን ‹‹የተሻሉ›› ሊባሉ የሚችሉት አራቱ ድርጅቶችም ቢሆኑ ለኑባሪያቸው (ህልውናቸው) መገለጫ ሊሆን የሚችል ስራ ሲሰሩ ማየት እንፈልጋለን።

ከዚህ ውጭ ቀጣዩ ውድድር ወይም ፉክክር እንደቀድሞው ሁሉ በገዢው ፓርቲ እና በተቃዋሚዎች ብቻ የመሆን እድሉ ከቀን ወደ ቀን እየጠበበ ነው። ምክንያቱ ደግሞ በርካታ ‹‹ተቀጣጣይ ነገሮች›› በህዝብ እና በመንግስት መካከል የከረረ ፍጥጫን እየፈጠሩ በመሆኑ ነው። ይህንን ሁኔታ በግልፅ አማርኛ ስንነጋገርበት ‹‹ዙሩ እየከረረ ነው›› የሚል ሆኖ እናገኘዋለን። ይህን ጊዜም ነው የአደባባይ ሰው ወይም መሪ ድርጅት ከወዴት ነህ? ብለን እንድንጠይቅ የምንገደደው፡፡

አሁን ያሉት የፖለቲካ ድርጅቶች ‹‹ከሞላ ጎደል…›› ተብለው እንኳ ሊመረጡ የሚችሉ አይደሉም። እንደዋዛ ‹‹ኢህአዴግን ማውረድ ቀላል ነው›› ሲሉ ልትሰሟቸው ትችላላችሁ፡፡ ነገር ግን ያንን ‹‹ቀላል›› መንገድ አያሳዩዋችሁም ወይም አያውቁትም። እናም ይህንን ‹‹ዋዛ ፈዛዛ›› ለማስወገድ ቀድመን መነጋገር አለብን። ለምሳሌ ረጅም የትግል ልምድ አላቸው የሚባሉትን የፕ/ር በየነ ጴጥሮስን እና የዶ/ር መረራ ጉዲናን ድርጅቶች ብናይ የሀገራችን የፖለቲካ ፓርቲዎች መንደር ከክበበው ገዳ የበለጠ ኮሜዲያን የበዛበት ሆኖ እናገኘዋለን።

በእርግጥ በየነም ሆኑ መረራ ‹‹ፖለቲካ እና ኮረንቲ በሩቁ›› እየተባለ ለንፅፅር በሚቀርብበት ሀገር በተቃውሞ ጎራ መገኘታቸው በራሱ ዋጋ ሊያሰጣቸው እንደሚገባ ከላይ ተስማምተናል። ሆኖም ያ ዋጋ ግን ዛሬም ድረስ ሊጨበጥ እና ሊዳሰስ የማይችል ፓርቲ ይዘው ‹‹መድረክ›› በሚባል የተበሳሳ ዣንጥላ ተጠልለው ‹‹ወከልነው›› በሚሉት ህዝብ ላይ እየቀለዱ እንዲጓዙ የሚያስችላቸው መሆን የለበትም። አሁንም ጉዳዩን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ እነዚህ ሁለት ሊቀመንበሮች ‹‹ድርጅት›› ይሁኑ ‹‹ግለሰቦች›› ሊለዩ የማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል፡፡ መለስ ዜናዊ ላይ ሲሆን የሚቃወሙትን የአንድ ሰው ፈላጭ ቆራጭነት እነሱ ጋ ሲደርስ ‹‹ትክክል ነው›› ይሉናል። ለዚህም ነው አንድም ቀን ጠቅላላ ጉባኤ ሲያካሄዱም ሆነ የራሳቸውን አጀንዳ ቀርፀው ሲታገሉ ያላየናቸውን ፓርቲዎቻቸውን እንደፓርቲ ልንቀበል አይገባም የምለው። አመንም አላመንም በየነ ወይም መራራ የሚባል ግለሰብ ይኖራል እንጂ የሚመሩት ፓርቲ በህይወት የለም፡፡

ሌላው ቀርቶ የመረራ ጉዲና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ የሆነው ኦላና ሌሊሳ በአሸባሪነት ተጠርጥሮ ሲታሰር በህይወት ስለመኖሩ ከማህተም ባለፈ ማስረጃ ሊቀርብለት ያልቻለው የዶ/ር መረራ ኦህኮ በያዘው ማህተም እንኳ ተጠቅሞ አንዳች ያደረገው ነገር የለም፡፡ እልፍ አእላፋት የኦሮሞ ልጆች እንደበግ ከትምህርት ቤት እና ከእርሻ ቦታቸው እየታነቁ ሲታሰሩ ‹‹የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስ›› ድምፁን ማሰማት ያልቻለው ለምን ይሆን? ዛሬ የወለጋ እና የባሌ እናቶች የደረሱ ልጆቻቸው እየታነቁባቸው ‹‹የፍትህ ያለህ?›› ሲሉ እያየን መራራን እንደፖለቲካ ታጋይ መውሰዱ ለታሪክ ስህተት እንደሚዳርግ አትጠራጠሩ፡፡ የሀድያ ብላቴናዎች በ‹‹ችጋር›› ከቀዬአቸው መሰደድን በየነ ጴጥሮስ ከቁም ነገር እንደማይቆጥሩት ሁሉ፤ ኦሮሞ መሆን ብቻውን ‹‹አሸባሪ›› ማስባሉ ለመራራ ጉዲና ችግር አይደለም፡፡ ይህንን ለማለት የሚያስደፍረው ችግሩን እንደ አንድ የመቀስቀሻ (የመታገያ) ስልት ወስደው ሲጠቀሙበት እና ሲያውገዙት አለመታየታቸውም ጭምር ነው። ይህ የሆነው ደግሞ ፓርቲው ከመህተም ውጭ ህይወት አልባ በመሆኑ ይመስለኛል።

…ከዚህ በኋላ ምን አልባት ራሳቸውን አጠናክረው ከ‹‹እስኮላር›› እና ‹‹ፌሎው-ሽፕ›› ማሳደድ እርቀው መውጣት ከቻሉ አንድነት፣ መኢአድ፣ አረና እና ኦፌዴን የተሻለ ተቀባይነት የሚያገኙበት እድል ከየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ የሰፋ ነው። ይህ ሊሆን የሚችለው ግን ከሚማልሉበት የውጭ ሀገር ትምህርት ዕድል ብቻ ሳይሆን እየተከተሉት ካለው የዘልማድ ‹‹ፖለቲካ ፓርቲ››ነት መላቀቅ ከቻሉ ብቻ ነው።

እዚህ ጋ አንድ ነገር ግልፅ መሆን አለበት፡፡ እነዚህን ፓርቲዎችም ቢሆን የሰፋ እድል አላቸው ያልኩት በአመራሩ ጥንካሬ ተማምኜ አይደለም፡፡ ይልቁንም የዕድላቸው እጣ ፈንታ ገና ‹‹ያልተፋቀ›› የሆነው ጠንካራ የድርጅት ፍቅር ባለው አባሎቻቸው ብርቱነት ላይ ተመስርቼ ነው፡፡ በዚህ ቀመር መሰረትም አንድነት እና መኢአድ ልዩነታቸውን አጥበው በጋራ መስራት ከቻሉ ሰፊ ሊባል የሚችል ዕድል አላቸው፡፡ ምንአልባት ይህ የሚቸግራቸው ከሆነም ከሁለቱ የትኛው ልቆ ይወጣል? የሚለው አጨቃጫቂ ቢሆንም ሁለቱም ከሰሩ ከገቡበት ቅርቃር ሊወጡ የሚችሉባቸው ሽርፍራፊ ዕድሎች አላቸው፤ ከነአሰልቺና ማለቂያ የሌለው ችግሮቻቸው ማለቴ ነው፡፡ የአረናና የኦፌዴን ከዚህ የተለየ ነው፡ ፡ ምክንያቱም ሁለቱ ፓርቲዎች ብሄር ተኮር ከመሆናቸው አኳያ የሚነፃፀሩት በወከሉት ብሄር ውስጥ ባላቸው ተቀባይነት ነው፡፡ እናም ንፅፅሩ ኦሮሚያ ውስጥ ኦፌዴንን ከኦህዴድ፤ በትግራይ መሬት ላይ ደግሞ አረናን ከህወሓት ይሆናል ማለት ነው፡፡ እንግዲህ በሚዛን የሚቀመጠው የኦሮሚያ እና የትግራይ ህዝብ ነፃ የመወዳደሪያ መድረክ ከተመቻቸለት ለየትኛው ድርጅት የተሻለ ድጋፍ ይሰጣል የሚለው ነው፡፡ መቼም ለ21 አመታት ያህል ግብር ከመሰብሰብ እና ማዳበሪያ ከመቸርቸር የዘለለ ፋይዳ ለሌላቸው ኦህዴድ እና ህወሓት ነው የሚል ቀልደኛ ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡

ከዚህ ባሻገር በሀገራችን ፖለቲካ ላይ በየአመቱ እንደአዶ-ከበሬ የሚከሰት አንድ አደገኛ ተመላላሽ ችግር አለ። የአንጃ ፖለቲካ የሚባል። ይህ አይነቱ አደጋ ነው የፓርቲውን ውስጠ ሚስጥር የጉሊት ሽንኩርት የሚያደርገው፡ ፡ ብዙውን ጊዜ በኢትዮጵያ ባሉ ተቃዋሚዎች ውስጥ የአንጃ ፖለቲካ የሚከሰተው በሶስት ምክንያቶች ነው። የመጀመሪያው መናፍቅነት / ጥርጣሬ/ ሲከሰት ነው። በዚህ ጉዳይ ደግሞ ‹‹አንጋፋ›› ፖለቲከኞቻችን የተካኑ ናቸው። ልክ መለስ ‹‹በሲኒ ውስጥ ማዕበል የሚፈጥሩ›› የሚሏቸው አይነት፤ ‹‹እከሌ ወያኔ ነው›› ይሉና ጠርጥረው ያሰጠረጥራሉ፤ ፈርጀው ያስፈርጃሉ። ይህንን ተከትሎም በአንጃዎች መናጥ የፓርቲው ዕጣ ፈንታ ይሆናል። ይህን ጊዜም ትላልቆቹ ፖለቲከኞች ሽሚያ ይገባሉ፤ ሽሚያው ግን ፓርቲውን ከአንጃ ወጀብ ለመታደግ አይደለም፤ ትከሻው ለ‹‹ሎሌነት›› የተመቻቸውን ለማፈስ እንጂ፡፡

ሁለተኛው ችግር የውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊነት ነው። በዚህ ተቃዋሚዎች የሰናፍጭ ቅንጣት ያህል ከኢህአዴግ አይለዩም። ክፉ አቻዎች ናቸው። በመኢአድ ውስጥ የኢንጅነር ኃይሉ ሻወልን ሃሳብ መቃወም ዛሬ መኢድ ያለበት ደረጃ ያደርሳል። መሰነጣጠቅ ማለቴ ነው። አመራሩን መገምገም ወይም የአደባባይ ስህተቱን መተቸት ‹‹መናፈቅ›› ያስብላል፡፡ እናም በሁሉም ፓርቲዎች ለማለት በሚያስደፍር ሁኔታ ‹‹ውስጠ-ዲሞክራሲ›› የሚባል ነገር እምጥ ይግባ ስምጥ አይታወቅም፡፡ በዚህም የተነሳ ለገዥው ፓርቲ ሲሆን ‹‹ለልዑላኑ እውነት መናገር አንገት ያስቀነጥሳል›› ማኪያቬሊያዊ አስተምህሮት በተቃዋሚዎች ሰፈር ሲደርስ እንዲህ የሚል ሆኖ እናገኘዋለን ‹‹አመራሩን መተቸት መናፍቅነት ነው››፤ መናፍቁ ደግሞ የራሱን አማኝ ያሰባስብና አንጃ ይፈጥራል፡፡

ሶስተኛው Personality Cult (የተክል ስብዕና አምልኮ) ለመፍጠር የሚደረገው እሽቅድምድም ነው ለአንጃ መፈጠር በር ከፋቻ የሚሆነው፡፡ ለምሳሌ በትግሉ ዘመን በህወሓት ውስጥ ግለሰብን ማምለክም ሆነ ለመመለክ ራስን ማመቻቸት በሞት የሚያስቀጣ ወንጀል ነበር፡ ፡ ከ1993ዓ.ም በኋላ ግን ይህ ሁኔታ ተቀይሮ በግልባጩ መለስ ዜናዊን ያለማምለክ በሞት ባያስቀጣም ከፓርቲ ጥቅማ ጥቅም በእጅጉ ያርቃል ተባለ- ባልተፃፈው የህወሓት ህግ፡ ፡ ይህንንም ተከትሎ አንጃ ተፈጠረ፡፡ እናም በህወሓት ውስጥ ‹‹ውድብ /ድርጅት ወስናለች›› ተረት የሆነውን ያህል በተቃዋሚዎችም ‹‹ቅድሚያ ለፓርቲው ውሳኔ›› የሚለው መርህ ተረት ሆኖአል። ለዚህ ትልቁ ማሳያ በየነ ጴጥሮስ እና መረራ ጉዲና ናቸው። ለምሳሌ የመረራ ጉዲና ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ገብሩ ገ/ማርያም በማንኛውም መልኩ ከመራራ የሚያንስ አቅም የላቸውም። እንዲያውም በአንዳንድ ነገሮች፣ ሀሳብን አፍታቶ በማብራራት እና በመሳሰሉት የተሻሉ ናቸው። ነገር ግን ላለፉት አስራ ስድስት አመታት ከመረራ ውጭ ማንም ሊቀመንበር ሆኖ አያውቅም፡፡ ምንአልባትም በቀጣዩ አስራ ስድስት አመታትም ኦህኮ በዚህ መልኩ የሚቆይ ከሆነ እመኑኝ መረራንም በሊቀመንበር ወንበር ላይ እናገኛቸዋለን፡፡ ሌላው ቀርቶ በየትኛውም ሚዲያም ሆነ መድረክ ም/ል ሊቀመንበራቸውን ገብሩ ገብረማሪያም ኦህኮን ወክለው ሲናገሩ አናያቸውም። ይህ የሆነው በመለኮታዊ ስልጣን አይደለም፤ መረራ የመሰረቱት ፓርቲ የራሳቸውን ተክለ ስብዕና ብቻ ይዞ ይገነባ ዘንድ ስላመቻቹት እንጂ። እናም ልክ ኢህአዴግ ሲነሳ መለስ ዜናዊ፤ ህወሓት ሲነሳ መለስ ዜናዊ እንደሆነው ሁሉ ኦህኮም ሲነሳ ከፊት መራራ ጉዲና ናቸው፡፡ በየነ ጴጥሮስም ‹‹ጽዋ›› እየተጠጣ የሚዘከርለት መላዕክ ይመስል በፓርቲያቸው ውስጥ ራሳቸውን ‹‹አምላክ›› አድረገዋል፤ ያውም የማይከሰስ፣ የማይወቀስ። በዚህም ተደጋጋሚ ጊዜ በአንጃ ተከፋፍለው ከጦር መሳሪያ ፍልሚያ መለስ ባሉ ፍልሚያዎች ሲፋለሙ ማየቱ አዲስ አይደለም፡፡

ከዚህም አልፈው በተለያዩ ጋዜጦች ላይ በመድረክ በኩል የሚተሳሰሩትን የአንድነት ም/ሊቀመንበር /በዚህ ወቅት ሊቀመንበሩን ወክለው እየሰሩ ነው/ ግርማ ሰይፉ ፓርላማ በመግባታቸው ደጋግመው ወርፈዋቸዋል። በቅርቡ አንድ የመድረክ አመራር እንደነገሩኝ በዚህ ጉዳይ ላይ የስራ አስፈፃሚ አባላት ተሰብስበው እየተወያዩ ሳለ መራራ ጉዲና ‹‹ድንጋይ እየተወራወርን ነው›› ሲሉ የመወራረፉን የእድገት ደረጃ በገደምዳሜ ገልፀዋል፡፡ ከዚህ በተረፈ መቼም የሽግግር ወቅቱን ጨምሮ ለአራት ክፍለ ጊዜ / Term/ በፓርላማው ቋሚ ተሰላፊ የነበሩት በየነ ጴጥሮስ ‹‹ፓርላማ መግባትን›› ሲቃወሙ መስማት የተቃውሞ ስብስብ መሪዎች የሞራል ደረጃችው የት እንዳለ ያሳያል፡፡ በዚህ መልኩም በእንዲህ አይነት ፖለቲከኞች የምንሻገረው ወንዝ ሊኖር ይችላል ብሎ ማሰብ ደመናን የመጨበጥ፣ ጉምን የመዝገን ያህል ይሆንብናል።

ይህንን ጽሑፍ እያዘጋጀሁ ሳለ በመሀሉ የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ቢሮ ጎራ ለማለት ሞከርኩ። ፕሮግራማቸውን በደምሳሳው ለመቃኘት። ነገር ግን የአብዛኞቹ ቢሮ ዝግ ነው። እናም ሁለተኛ አማራጭን ተጠቀምኩ። ኢንተርኔትን፡፡ በመረራ ጉዲና የሚመራውን የኦህኮ ፕሮግራም አገኘሁና በእጅጉ ተገረምኩ። ያስገረመኝ ምን መሰላችሁ? ከሀገሪቱ የህዝብ ቁጥር ከፍተኛ የሆነውን ኦሮሞን የሚወክለው ኦህኮ ፕሮግራሙ በአምስት ገፅ የሚጠናቀቅ መሆኑ ነው። እንዴት ነው ነገሩ? ምን አልባት ‹‹ኢየሱስ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ ነው በዚህ አለም የኖረው›› የሚል የመፀሀፍ ቃል ሰምተው ይሆን እንዲህ በአምስት ነጠላ ወረቀት የተዘጋጀ ፕሮግራም የቀረፁት? ብቻ እንጃ፡ ፡ (እንደማሳሰቢያ፡- በበየነ ጴጥሮስ እና በመረራ ጉዲና ላይ ያተኮርኩት በአሁኑ ወቅት በተቃውሞ ጎራ ያለውን ፖለቲካ በመምራት ከሁሉም የበለጠ የትግል ዕድሜ ስላስቆጠሩ ነው፡፡ በተጨማሪም የሁለቱ ሰዎች የፖለቲካ አዙሪት ሌሎችንም ይወክላል በሚል ነው)

የመውጫ በር አለ?

የወንድ በር ሳይሆን የመውጫ በር ለፈለገ አለ፡፡ በተለይ ለአንድነት፣ ለመኢአድ፣ ለኦፌዴን እና ለአረና። ለምሳሌ የፀረ መጅሊስ እንቅስቃሴ፣ የመምህራን ጥያቄ፣ የጉራፈርዳ መፈናቀል፤ የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ሳንሱር፣ የኑሮ ውድነት፣ በልማት ስም ኢፍትሃዊ መፈናቀል… ሌላም ሌላም ጥያቄዎችን በማጎን ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ። ከእንዲህ አይነት ህዝባዊ አጀንዳዎች ጎን ከመቆም ባሻገርም ሌሎች ድርጅታዊ ጥንካሬን የመፍጠሪያ ስልቶችን መንደፍ እና አድፋጭ ምሁራኖችን ወደ አደባባይ ማምጣትም ሌላው የመጠናከሪያ መንገድ ነው። activist (ተሟጋቾችን) መመልመል እና ማብቃት፤ ከዛም ሀገራዊ ጉዳዮችን በሚመለከት በአለም አቀፍ መድረኮች ሳይቀር ለመሟገት የሚችሉበትን መደላድል ማመቻቸትም እንዲሁ ለድርጅት ጥንካሬ የጎላ ጠቀሜታ አለው።

በአናቱም ራሳቸውን ስልጣን ላይ እንዳለ ገዢ ፓርቲ በመውሰድ ለእያንዳንዱ ጉድልቶች የመፍትሄ ሀሳቦችን መሸጥ ፓርቲዎቹ ለመጠናከር ከሚችሉባቸው ስልቶች ዋነኛው ነው። በተለይም አማራጭ መንገዶችን ማሳየት ጠቀሜታው የላቀ ነው። ወጣቶችን ወደፊት ማምጣትም ሌላኛው ጠቃሚ ስልት ነው። በ‹‹ያ ትውልድ›› እና በ‹‹66ቱ ፖለቲካ›› የእኔን ትውልድ ‹‹አማልላለሁ›› ማለቱ ግን አስቸጋሪ ነው። እናም ፓርቲዎቹ የአመራር ቦታውን በወጣቶችም ጭምር ከአጠናከሩት ለተሻጋሪነቱ አስተማማኝ መንገድ ይፈጥርላቸዋል። በዚህ ደግሞ ቢያንስ በቀጣዩ አመት የሚደረገውን የአዲስ አበባ ምርጫን ‹‹እንደሰርቶ ማሳያ›› የሙከራ ፕሮግራም ወስደው ራሳቸውን ሊፈተሹ የሚችሉበትን አጋጣሚ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ ይህ እንግዲህ መልካም ምኞቴ ነው፡፡ ሆኖም ‹‹የፖለቲካ ምህዳር መጥበብን›› ብቻ በመግለጫ እየተቃወሙ፣ በሰላማዊ የትግል ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ አማራጮችን ‹‹አይቶ እንዳላየ፣ ሰምቶ እንዳልሰማ›› እያለፉ፣ 150 ሰው ብቻ በተሰለፈበት ሰላማዊ ሰልፍ ‹‹ብርቱካን ትፈታ›› ተብሎ የተጠየቀውን አይነት ጥያቄ ያህል እንኳ ‹‹አንዷአለም ይፈታ›› በሚል መድገም አቅቶአቸው እያየን ‹‹መጪው ጊዜ ለተቃዋሚዎች ጨለማ ነው›› ለማለት ነብይ መሆንን አይጠይቅም፡፡ ከዚህ በተረፈ ህዝቡ ከፓርቲዎቹ ቀድሞ ወደአደባባይ በመውጣት፡-

‹‹ገለል ይሻልሃል
ገለል ያለው መቶልሃል›› ያለ እንደሆነ የሀገሪቱ ዕጣ ፈንታ የሊቢያ ወይም የሶሪያ ከመሆን አይመለስም። በሊቢያ እና በሶሪያ ህዝባዊ አመፅ በተቀሰቀሰ ጊዜ የተፈጠረው ነገር ምንድር ነው? ብሎ መጠየቁ የተሻለ ተሞክሮ እንዲኖር ያስችላል፡፡ ምንአልባትም እንዲህ የሚል መልስ ልናገኝ እንችላለንና፡፡ በእነዚህ ሀገራት ህዝባዊ ተቃውሞውን መስመር የሚያሲዝ ጠንካራ ፓርቲ ባለመኖሩ፣ ህዝቡ በጎበዝ አለቃ ተደራጅቶ ከመንግስት ጋ መፋለሙ ሀገራቱ የመፈራረስ አደጋ ውስጥ እንዲወድቁ አድርጓቸዋል። በቱኒዚያ እና በግብፅ ግን የታየው የዚህ ተቃራኒ ነው። ምክንያቱም በሁለቱ አገራት የነበሩ ፓርቲዎች ምንም እንኳን በጠበበ ምህዳር እና በአምባገነን ስርዓት ውስጥ ቢሆኑም ከአብዮቱ በፊት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ራሳቸውን ከማጠናከር ያልሰነፉ ስለነበር ተቃውሞ ሲቀሰቀስ ከፊት መስመር ለመገኘት አላዳገታቸውም። እናም የፈነዳውን ህዝባዊ ቁጣ ተከትሎ ሀገሬው አደባባይ መዋል ሲጀምር ፓርቲዎቹ በቀላሉ
‹‹አንበሳው ጋሜ
አይዞህ ወንድሜ››ን እየዘፈኑ አብዮቱን ከመቀላቀል ያገዳቸው አልነበረም። ይህ ደግሞ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር አስችሎአል።
(…በአነሰተኛና ጥቃቅን መደራጀትም ስራ ነው፣ ኮብል ስቶን ማንጠፍም ስራ ነው፣ የፖለቲካ ፓርቲ ማቋቋምም ‹‹ኢንተር ፕሩነር ነው›› /ስራ ፈጠራ ነው/ በሚል ስለተቋቋሙ ፓርቲዎች ሌላ ቀን እመለስበታለሁ)

Comments

Teme today you come to the point! This is what we need from you,that is, you mentioned how much the opposition leaders are weak and selfish! This is fact!
We the people need a leader, a leader like Moses and Mandela! So far, however, we haven't seen such kind of leader! Anyway I'm sure God has a plan for us hopefully we will get our Moses and Mandela soon! Take care Teme!

You just hammer the nail on the head buddy!

ተሜ! እንደምን ስነበትክ? ያው እንደተለመደው በሁሉም ኢትዮጵያዊ ልብ እና አእዕምሮ ውስጥ የሚብላላውን ሀሳብ ለንባብ በማብቃትህ ከልብ አምሰግናለሁ።(sorry, my Amharica font is not good)
Tama, As usual, you did a good job! It shows your committeeman. You have been trying to show your facts and opinions. These facts and opinions are not only yours but also all Ethiopians’.
From my perceptive, and as you have mentioned, all Ethiopian’s political parties have three main problems. These are good leadership, organization, and discipline. Even if these pillar qualities is not developed within one over night, all parties have to be invest their time to cultivate, and to nurture their parties by these three critical and back bones a political party qualities.

ዘልማድን በቃ ልንለዉ ይገባል! ሁለ ነገራችን የዘልማድ ኑሯችን፣አስተሳሰባችን፣አደረጃጀታችን፣ዓላመችን፣መንገዳችን፣አመለካከታችን፣ተቃዉሟችን፣ አተቻቸታችን ዘልማዳዊ እየሆነ ይሄዉ ጠብ የሚል ነገር ሳንፈጥር ትናት አልፎ ዛሬ መጥቶ ሌላ ነገን የምንጠብቅ ታካቾች ከመሆን አልዳንም፡፡ ዛሬም በእኛ ዘመን በሃበሻ ምድር አዲስ የትዉልድ ትግል በማካሄድ የሰለጠነ እና አግባብ የሆነ ስርዓት ተከትልን የሃገራችን ቅጥር እንደገና መገንባት እንችላለን፤ያ የሚሆነዉ ግን እራስን ለሰለጠነ አስተሳሰብ በማስገዛት የማይነዋፅ ሃገራዊ ፍቅር በማደበር እራሳችን ከብሄር ቸርቻሪነት በማዉጣት በሰብኣዊ እኩልነት አምነን ላመነዉም ታማኝ ሆነን መደብ ዘለለ አስተሳሰብ ያዳበርን እንደሆነ የፈራረሰዉን ቅጥራችን እንገነባለን፤ ካለበለዚያ ግን ያሰብነዉ እየከሰመ፣የያዝነዉ ከእጃችን እያመለጠ፣ያለምነዉ እየጨለመ ነፋስን እንደመከተል ይሆንብናል፡፡
እንደ እኔ ከሆነ ግን ለሃገራችን የተቃዋሚ ጎራ አፍዝ አደግዝ የሆነዉ ዋነኛዉ ነገር በጎራዉ የተኮለኮሉ ተቃዋሚወች የመጨረሻ ግብ (ultimate end) ማነስ ወይም መኮሰስ ይመስለኛል፡፡ ለምሳሌ እንደ ማሳያ በፁሁፉ ላይ የተጠቀሱትን ሁለት የተቃዋሚ መሪዎች ፕሮፌሰር በየነ ና ዶ/ር መረራ ጉዲና ብንወስድ የእነሱ የመጨረሻ የትግል ግባቸዉ በቃ ሁሌም እየተቹ መኖርና በተቃዋሚ ጎራ መኮልኮል ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም እዚህ የዘለለ የመጨረሻ የትግል ግብ ቢኖራቸዉ ወከልንህ የሚሉትን ህዝብ ታግለዉ ባታገሉት ነበር፣ ለህዝባቸዉ በሞቱለት በታሰሩለት ነበር፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ገና ከስሩ እርስ በእራሳቸዉ አሁንም የሃገርንና የህዝብን ጥቅም በማስጠበቅ ሳይሆን ግለሰብ ተኮር የሆነን ጉዳይ በማግዘፍ እና በመፈትፈት ወደ አደባባይ በመምጣት የድርጅታቸዉንም ሆነ ግለሰባዊ የትግል የመጨረሻ ግብ ያሳንሱታልም ያኮስሱታልም፡፡ ስለዚህ እኔም እላለዉ የትግል ግባችን ወደ ሃገራዊ እና ህዝባዊ ጥቅም ከፍ በማድረግ ከ ዘልማዳዊ የተቃዉሞ ስርዓት በመዉጣት ሃገራችንና ህዝባችን ከአፋኞች መንጋጋ እናላቃት!!
ሰብዓዊነትን በማስቀደም የትግል ግባችን ከፍ እናድርግ!!

በ‹‹ያ ትውልድ›› እና በ‹‹66ቱ ፖለቲካ›› የእኔን ትውልድ ‹‹አማልላለሁ›› ማለቱ ግን አስቸጋሪ ነው። Perfect

እነዚህ "ፓርቲዎች" እኮ "ተቃዋሚ ፓርቲ" የሚለው ስም ራሱ ተገቢ አይደለም:: አነስተኛና ጥቃቅን ለዛውም በሰፈር ተደራጅተው ኮረት(ኮብል) ድንጋይ የሚያነጥፉ ሳይሆኑ ድንጋይ ውርወራ የሚገጥሙ ቡድኖች እንጂ::አነጠፉ ካልነም እንኳ ኮረት እያነጠፉለት ያለ ለህወሃት ነው:: ለህዝቡ ግን "የውሻ መንቆር" ነው የሆኑበት!ህዝቡ እንዳይንቀሳቀስ በማዘናጋት የመንግስትን ማፍያ ቡድን እድሜ ለማራዘም "የተገዙ" ኪኒኖች ናቸው:: ጀግና መሪ እና ህዝቡን ከፊት ሆኖ ለመምራት የትዘጋጁትማ ታስረዋል: ተገድለዋል:: እንዲያውም ለነዝህ ጀግኖች መታሰር "ጠቋሚ ጆሮ ጠቢዎች" እዛው "ፓርትው" ውስጥ ተውሽቀው ያሉ ጓደኞቻቸው ("ጓዶቻቸው" ግን አይደሉም) ናቸው:: "እነርሱ" ለፓርላማ ሲያልፉ ቂጣቸውን ቃርያ ቀብተው ነው ወደ 4 ኪሎ የሚሮጡት የሚቀድማቸው የለም:: ነገር ግን ካልተመረጡ የሚገባ ሰው ይተርባሉ: ቅናት አቀንቅኗቸው ነው!
ሀገር ነጻ የምትወጣው "ለስልጣን" በተዘጋጀ: የሸረሪት ድር ያደራበት የምስክር ወረቀት አሮጌ ሳጥን ውስጥ ወሽቆ ራሱን የተሻለ "በማስመሰል"እኔ ከሞትኩ ማን ይመራል በማለት የሚመጻደቅ ፈሪ የ እውቀት ሳይሆን "የወረቀት" ጆንያዎች አይደለም! ስልጣን ብቻ ሳይሆን ህይዎቱንም ለማይፈልግ ግን ለለሎች ነጻነትና የተሻለ እኩልነት ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ: ነገን እኔ እመራታለሁ ሳይሆን ነገ በኔ ደምና አጥንት ላይ ሆነው የሚመሯት: የነጻነት አየር ለሚተ'ነፈስባት ሀገር በሚፈልግ መንፈሳዊና አካላዊ ጀግኖች ነው!
ጋምቤላ ጫካ ግቡ: ሊማሊሞ ገደል ግቡ: ኦሮሚያ ጫካ ግቡ እየተባሉ የሚሰደቡ የአልጋ ላይ እንጂ የወኔ ብልት ያላንጠለጠሉ መጻጉዕ; ህዝቡን በማዘናጋት ለህወሃት መቆየት የበኩላቸውን ጊዜ እየገበሩ እድሜውን የሚያራዝሙ; ህወሃት እራሱ ባደባባይ የሚናገረውን: ሃገር ያወቀውን ፀሐይ የሞቀውን ስህተቱን ተቀብለው በማራገብና "ራቦል" በመደረት የሚኖሩ ናቸው:: ስለዚህ እነዚህን ከህዝቡ 3 ጊዜ ወደኋላ የቀሩ "የጋሪ ዳውላዎች" እንዳያዘናጉን አርፈው እንዲቀመጡና የገዥውን ማፍያ ቡድን ገጽታ ለመገንባት የተኮለኮሉ የህወሃት ሴተኛ አዳሪወችና የእርዳታ መቀበያ ጓንቶች(ኮንዶሞች) አርፈው እንዲቀመጡ ሃግ ሊባሉ ይገባል::...........

iwunetm fith land hager idgetna lehisocha liulina ijigun asfelgi new. fitihgazeta be fitih zura ......tetenakro yiketil.

Teme belebe moleto metenefesha yatahuleten hasab endihe gilet seladerekew Tebarek.

good very very good . i like your view. there are a lot more re searchable news article like this one . please wide this topic you will have a lot more to say about it . then you can go to the followers too as you go to the leaders.

ደ/ር በየነና መራራ ኢንጂነር ሀይሉን ጨምሮ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ካላቸው አንጋፋነት አንፃር የተከበሩ ቢሆንም ይበልጥ ልዩ ነገር ሰርተው እንድናደንቃቸውና እንድንከተላቸው ባለማድረጋቸው ከወቀሳና ከትችት አንፃር ተመስገንን እጋራለሁ፡፡ ፖለቲካውን በፖለቲካ ብስለትና በምሁርነት በመሪነት በታጋይነት በአባትነት እንዲሁም ለወጣቶች በአማካሪነት መምራት ሲጠበቅባቸው ይልቁኑ በጥቂት ሳይሆን በብዙ ፖለቲካውን አበላሸተውታል፡፡ አሁንም ድረስ የማከብራቸው ቢሆንም በቃችሁ የሚል የታናሸነት ምክሬን እለግሳቸዋለሁ እነሱም ይህንን የሚቀበሉ ይመስለኘ
ል፡፡

Really a very nice article. Thanx teme. Eski nigerachew ... minim enkua awuko yetegan ... bihonim kilu.

ኢዴፓ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ትልቁ ችግር የአፍሪካ የሌብራል ፓርቲ ስብሰባን ያለማካሄድ ነው በሚል ቁጭት የአፍሪካ ሌበራል ፓርቲ ስብሰባ አዲስ አበባ እንዲካሄድ አደረገ፤
teme
beacuse of this idea i totally decided not to read ur articles . u equals to etv.
megemerria ende zena mech akirbe new ahun negetive side yemitaworaw???

COME WITH SOLUTIONS!!!
what is your choice?
1 joining strong parties curently in our poletics or?
2 establishing new? or
3 talking as you mastered?

First,I do appreciate FETEHE as it gave opportunities for both.Then,I think that Bewketu has lost the debate 6/1.I also think that Bewketu doesnt have morale capabilities to discuss about strength and weakness of the only Hereo.I would'nt say bewketu need to be killed for this position,but,read more before posting his views and then repent.
In addition,i have more books to lend so that he could re-think and get a better knowledge.This will help him to know and think before
what to write or talk. Writers may create two types of Theodros:one like a devil and the other like rightous.However,I would say he was a human being with more of sternghs and less weakeness.
Finally,I questioned my self whether The So Called Bewketu is healthy or not.On the otherhand, i argued that his exceptional positioning may have value to search truth.
For example,plato was the one who lost acceptance until proven right lately.

Thanks Temesgen, it’s an interesting and timely article. Especially, the statement: “ለምሳሌ የፀረ መጅሊስ እንቅስቃሴ፣ የመምህራን ጥያቄ፣ የጉራፈርዳ መፈናቀል፤ የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ሳንሱር፣ የኑሮ ውድነት፣ በልማት ስም ኢፍትሃዊ መፈናቀል… ሌላም ሌላም ጥያቄዎችን በማጎን ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ። ከእንዲህ አይነት ህዝባዊ አጀንዳዎች ጎን ከመቆም ባሻገርም ሌሎች ድርጅታዊ ጥንካሬን የመፍጠሪያ ስልቶችን መንደፍ እና አድፋጭ ምሁራኖችን ወደ አደባባይ ማምጣትም ሌላው የመጠናከሪያ መንገድ ነው። activist (ተሟጋቾችን) መመልመል እና ማብቃት፤ ከዛም ሀገራዊ ጉዳዮችን በሚመለከት በአለም አቀፍ መድረኮች ሳይቀር ለመሟገት የሚችሉበትን መደላድል ማመቻቸትም እንዲሁ ለድርጅት ጥንካሬ የጎላ ጠቀሜታ አለው።”has echoed the opinion of many of us. For quite long time I was wondering why can’t they at least say something especially about the ‘development through displacement’ approach of the developmental policy of the government, particularly in Gambela. Your article has answered many of my questions about the opposition parties. Keep it up!!

we need to learn more, pls make us know people. dont blame those who share their political views rather take the one which is favourable for your capacity.

i want to say we are living under unknown system meaning aleader who have no confidence with leading the people for example from fillipens they say to as every student should pass coc taking 2 or 3 questions as personal competence for agiven student their by producing many hopeless students after examined ,they don't pass because the questions are for fillioens and also the answers are for fillipens so producing or increasing many number of hope less yougsters because they are not employed unless they pass this fucken coc having short answer for every question for example for bill of quantities and specifications they have only one answer if fillipens have wroten 30 m2 for site clearnce evry student of ethiopia should bring 30 m2 imagine gthe whole tvet student of ethiopaui should get this other wise he will not get job

I have to say.....well done. You seem to grasp the working of our opposition parties very well. I always wonder what people really want to achieve when they form a party or become a member. Observing what most people do and how they do it, I usually ask: is it worth risking ones life? or do they have a hidden agenda? When forming a party or joining one, we should define our purpose clearly. I joined an opposition party sometime back after considering many options. I had a deep-rooted commitment to help in the peaceful struggle. But what I found out was the exact opposite of what I expected. I stayed for sometime but couldn't stand the injustice and mess in the party. Let me now tell you from experience what our main opposition parties are like.
In the first place the parties do not practice the democratic system they preach about. They find loop holes in their articles to staff the offices with appointed people rather than conducting elections. Lack of good governance: they don't abide by the very rules they establish. They feel threatened when people question the way they do things and they find ways to get rid off those people.Poor administration: document and finance handling. Most of them neither collect membership fees correctly or raise funds from other sources. Our opposition parties are so poor. They usually depend on a few individuals for financial support, hence the parties become private properties.
From my observation as a member and a coordinator, most of the people in the opposition camp are not different from those in the ruling party. It is just that they are playing on different fields. We need parties with new ideas. And they should be founded on strong grounds. Forming parties just to oppose others is a waste of time. Opposition should be based on knowledge and parties should come up with policy options. I believe the people who have been leaders in the opposition parties should take time off and think what they have been doing. If they really want to help, let them groom young politicians and see how it works for them. They have "tried" for a long time and it never worked, so they have give other people a chance.
So who is going to do all that has been said? All of us. After all has been said, I would like to give some credit to those who have been in the opposition despite the fact that our government makes things so difficult.

Teme...yetsafekewen anibebewalew tekekelegn neteb new:: inazih sewoch eko beer eyeteu change mametat yemimereu nachew. serachewem full time politicians sayhon partime new:: gena legena enitaseralen bilew yemisegu:: gefa silem Pro. Beyene Petros, Dr. Merara, Ato Bulecha, Ato Geberu eko ke EPRDF menem ayeleyum ye ethinic federalizem yemidegefu ena ye gosa party yemeserety nachew:: so leyunetachew lene siletan yeyaze EPRDF ena siletan yaleyaze ye EPRDF asitesaseb aramajoch nachew:: ahun yemiyasifelegew ke 66 abiyot wechi yehonu wetatoch nachew:: mefetehew esu bicha new inazih tagelew lewet liyametu aydelem erasachewenem yemilewetu aydelem lene.

I think opposition groups in Ethiopia are weak not largely b/c of their own limitations but largely due to the doings of the regime in power. The government has been doing all its level best to dismantle opposition groups by allocating significant amount of money. This does not mean that the opposition groups have no limitations. They definitely have!!!! But the TPLF-led government should be blamed for its unethical and illegal actions against them. From the outset it has been following the politics of exclusion in Ethiopian politics which is a continuation of policy of the past regimes, "BURDEN OF HISTORY?" . In this regard respectfully disagree with Temesgen.

Add new comment

Filtered HTML

  • Web page addresses and e-mail addresses turn into links automatically.
  • Allowed HTML tags: <a> <em> <strong> <cite> <blockquote> <code> <ul> <ol> <li> <dl> <dt> <dd>
  • Lines and paragraphs break automatically.

Plain text

  • No HTML tags allowed.
  • Web page addresses and e-mail addresses turn into links automatically.
  • Lines and paragraphs break automatically.