የመለስ ህመም፣ ታክቲክ እና መፃኢ እጣ ፈንታ
ተመስገን ደሳለኝ
ሰሞኑን አዲስ አበባ በወሬ መጋኛ ተመታለች። ወሬው በአዲስ አበባ ብቻ የተወሰነ አይደለም። በተለይም በአውሮፓ እና ሰሜን አሜሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንደ ጉድ እየተራገበ ነው- የ57 ዓመቱ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በጠና መታመም። ህመማቸውንም ተከትሎ ቤልጂየም ለህክምና መሄዳቸው እና ከፍተኛ ሊባል የሚችል ክብደት የመቀነሳቸውም ወሬ እንዲሁ የመጋኛ ያህል ነው።
በእርግጥ የጉብዝናውን ወራት የዱር ፍሬ እየበላ በረሃ የታገለ ቀርቶ በቤተመንግስት ያደገ ‹‹ልዑል››ም ቢሆን የዚህን ያህል አመት በስልጣን መቆየቱ (ሌላ ምክንያት እንኳ ባይኖር) በጤናው ላይ አንዳች ጉዳት ማስከተሉ አይቀሬ ነው። የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ችግርም ይህ ነው። ሌላ አይደለም። በበርካታ አምባገነን መሪዎች ላይ የታየ ማለቴ ነው፡፡
ምናልባትም የጠቅላይ ሚንስትሩን መታመም ተከትሎ በሀገሪቱ ውጥረት የነገሰበት ምክንያት የስርዓቱ ዴሞክራሲያዊ ያለመሆንም ነው። ምክንያቱም ዴሞክራሲያዊ በሆኑ ሀገራት የፕሬዚዳንቱ ወይም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጤንነት አደጋ ላይ ከወደቀ እያንዳንዱ የህክምና ሁኔታ እና ሰውዬው ያለበት ደረጃ ለሁሉም ሚዲያዎች ይፋ ስለሚሆን ለአሉባልታ የሚጋለጥበት ክፍተት አይኖርም። ለዚህም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከታመሙ ጀምሮ ‹‹ከፍተኛ የጤና መታወክ ገጠማቸው››፣ ‹‹ሕይወታቸው አልፏል››፣ ‹‹ሙሉ በሙሉ ተሽሏቸዋል›› የሚሉ እርስ በእርስ የሚጣረሱ ወሬዎችን እየሰማን ያለነው። ይህ ሁኔታ ወደታች ብቻ ሳይሆን ወደላይም ላሉት ግልፅ አይደለም። ለስርዓቱ ቅርብ የሆኑ ሰው ‹‹ከዚህ በኋላ ወደ ስራቸው አይመለሱም፡፡ ጉዳቱ ከፍተኛ ስለሆነ ሀኪም ለረጅም ጊዜ ከስራ ካልተገለሉ ለህይወታቸው አስጊ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ነግሮአቸዋል›› ሲሉኝ፤ ሌላኛው የፍትህ ምንጭ ደግሞ የዚህን ተቃራኒ ይናገራሉ። የእኚህ መረጃ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙሉ በሙሉ ማገገማቸውን የሚያረጋግጥ እና በመኖሪያ ቤታቸው ስብሰባም እያካሄዱ እንደሆነ የሚገልፅ ነው። ‹‹ይህ የሆነው›› ይላሉ ምንጫችን ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩን በደንብ ካለማወቅ ነው። ምክንያቱም የህወሓት አመራሮች አብዛኛውን ጊዜ ይታመማሉ። ህመም የማያጠቃቸው አቶ መለስ እና አቶ ስዬን ብቻ ነው። ሆኖም እነዚህ ሰዎች ሲታመሙ ጉዳታቸው ‹ሞቶ የመነሳት› ያህል ነው። የአቶ መለስም የሰሞኑ ሁኔታ የዚሁ አይነት ሲሆን፣ ሰውዬው ወደ ስራቸው ለመመለስ እየተዘጋጁ ነው። የሰውነታቸው መጎዳትም የህመሙ ብርታት ሳይሆን የህክምናው ባህሪ (Treatment) የሚፈጥረው ተጽዕኖ ነው›› ሲሉ ወሬውን አጣጥለውታል።
የሆነ ሆኖ መለስ ከወትሮ በተለየ መልኩ ከፍተኛ ሊባል የሚችል የጤና መታወክ እንደደረሰባቸው እርግጥ ነው። በዚህም ቤተሰቦቻቸው ተጨንቀዋል፤ የፓርቲያቸው አመራርም ከሚገባው በላይ አሳስቦታል፤ ከስር ያለው ካድሬም የተረጋገጠ መረጃ ባይኖረውም በደፈናው መደናገጡ የሚጠበቅ ነው፡፡ ‹‹ሌሎች›› ኢትዮጵያውያን (ይህ አገላለፅ ከ1983 ዓ.ም በኋላ የመጣ ነው) ደግሞ እንደ ልብ አንጠልጣይ ሲኒማ ክስተቱን በተመልካችነት እየተሳተፉበት ነው፡፡ ሁኔታው የአፄ ምንሊክን የመጨረሻ ዘመን ያስታውሳል፡፡ (ሰውየው ሀገሪቱን ለሁለት አስርት ዓመታት ቀጥቅጠው የገዙ ቢሆንም ‹‹እግዜር ይማሮት›› ማለት ባህላዊ ወጋችን ይመስለኛል፡፡ ለማንኛው እግዜር ይማራቸው) ጉዳዩ ግን ይህ አይደለም። ጉዳዩ የጤንነታቸው ሁኔታ እየተባባሰ ከሄደ ወይም የከፋ ከሆነ ‹‹በማን ይተካሉ?›› የሚለው ነው፡፡ ይህ አሳሳቢ ነው፡፡ ምንም እንኳ አብዛኛው ዜጋ ለዓመታት በሀገሩ ጉዳይ ባይተዋር የተደረገ ቢሆንም በእንዲህ አይነት ቀውጢ ጊዜ መጨነቁ አይቀሬ ነው፡፡ እናም ከዚህ ተነስተን ‹‹ቀጣይ የሀገሪቱ ዕጣ ፈንታ›› ምን ሊሆን እንደሚችል ለመወያየት ያህል ሁኔታውን ከአስተዳደር ዘይቤአቸው ጋር እያነፃፀርን እንፈትሽ።
መነሻ አንድ
የፀረ-ደርግ ትግሉን በበላይነት የመራው ህወሓት ከምስረታው ጀምሮ ለሁለት እስከተከፈለበት 1993 ዓ.ም. ድረስ ይመራ የነበረው በ“Collective leadership” (በጋርዮሽ አመራር) እንደነበረ ይታወሳል፡፡ በዛም ዘመን ‹‹ግለሰብን ማምለክ›› ከግምገማም አልፎ በተፃፈ ህግ እስከመቀጣት የሚያደርስ ጥፋት ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን ‹‹ውድብ (ድርጅት) ወስናለች›› የምትለው አገላለፅም የህወሓት ቀኖና ነበር ማለት ይችላል- እስከ 1993 ዓ.ም። በትግሉ ዘመን ሌላው ቀርቶ ከዩኒቨርሲቲ በወጡት ምሁራን እና እርሻቸውን ትተው በረሃ በገቡት አርሶ አደሮች መካከል የሚታይ ልዩነት እንዳይኖር ህወሓት አጥብቆ ይቆጣጠር እንደነበር የኋላ ታሪኩ ይነግረናል። ሆኖም አሁን ያ ዘመን አልፎአል። ያ ህግም የኦሪት ህግ ሆኖአል። ምክንያቱ ደግሞ ዛሬ ግለሰብን ‹‹ማምለክ›› የህወሓት መለያ በመሆኑ ነው።
መነሻ ሁለት
‹‹ህወሓት››ን የመሰለ አክራሪ ብሔርተኛ እና ኮሚኒስት ድርጅት ውስጣዊ አደጋ ሲገጥመው የቆመበት የፖለቲካ ባህልም ሆነ መተዳደሪያ ደንብ መናዱ ከሌሎች ተመሳሳይ ድርጅቶች ተሞክሮ ስንነሳ የሚጠበቅ ነው። ልዩነቱ የናዳው ጉዳት ላይ ነው፡፡ ከዚህ አኳያም በ93ቱ ክፍፍል ህወሓት በአደገኛ ሁኔታ የቆሰለ (የተጎዳ) ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ድርጅቱ ሙሉ በሙሉ ወደ አንድ ሰው መዳፍ ጓዙን ጠቅልሎ የገባው ከዚሁ ጊዜ ጀምሮ ነውና። ህወሓትን ለተከታተለም ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊም እንዲሁ ‹‹ያ አንድ ሰው›› መሆናቸው የሚጠበቅ ነው።
የማይካደው ነገር በ1981 ዓ.ም አቶ መለስ ዜናዊ የድርጅቱ ሊቀመንበር ተደርገው የተመረጡት ከህወሓትም ሆነ ከኢህአዴግ የአመራር አባላት በርዕዮት አለም ትንተና የተሻሉ እና የተራቀቁ በመሆናቸው ነው፡፡ በአናቱም የብልህነትን ፀጋ ተላብሰዋል፡፡ ከአለፉት ስርዓት እና ከኒኮሎ ማኪያቬሊም የገነጠሏቸውን ‹‹ገፆች›› በማሻሻል የራሳቸው ማድረግ ችለዋል። ይህ በወንበሩ ዙሪያ ሊያደፍጡ ይችሉ የነበሩትን ‹‹እሾሆች›› ለመንቀል ጠቃሚ ቢሆንም-ጉዳትም አለው፡፡ በተለይ ‹‹ተተኪ›› እንዳይኖር ከማድረግ አኳያ ማለቴ ነው፡፡ ለምሳሌ ‹‹አጼ ኃይለሥላሴ ‹‹ፀሐዩ ንጉስ›› በሚል መወደስ ወደ መለኮታዊነት ለመቀየር ሩብ ሲቀራቸው ነው ድንገት ‹‹የምርጥ መኮንኖች›› የወታደር ‹‹ጫማ›› የደረሰባቸው፡፡ አፄው ‹‹ፀሐዩ ንጉስ›› ሲባሉ ሊመሰጠር የተፈለገው ግልፅ ነው፡፡ ፀሐይ ለአለም ብቸኛዋ የብርሃን ምንጭ እንደሆነችው ሁሉ አፄውም የኢትዮጵያ መተኪያ የሌላቸው እና ተፎካካሪ የማይገጥማቸው የብርሃን ምንጭ ናቸው የሚል የግለሰብ አምልኮ ጣሪያን ማመልከት ነው፡፡
በእርግጥ አፄው ‹‹ፀሐዩ…›› ይባሉ ዘንድ ዙሪያቸው በ‹‹ከዋክብት›› እንዳይከበብ ከሀገርኛው የፖለቲካ ባህል እና ከማኪያቬሊ ስልት ተደባልቆ በተቀመረ ‹‹ፎርሙላ›› የቻሉትን ያህል ጥረዋል። ለዚህም ነው ከጣሊያን መባረር በኋላ መንግስታቸውን፣ ከአርበኛ ይልቅ ለጠላት ባደሩ ግለሰቦች ያዋቀሩት። የዚህ ምክንያት ደግሞ ህዝቡ ‹‹ንጉሱ ከሌሉ እነዚህ ባንዳዎች ሀገሪቱን መልሰው ለጣሊያን አሳልፈው ይሰጧታል›› በሚል ስጋት መዋጡ አይቀሬ በመሆኑ ለንጉሱ ስልጣን ቀናኢ ይሆናል የሚል ነው። ማኪያቬሊም ይህን ይመክራል ‹‹ችግር (ጉድለት) ያለበትን እየመረጥክ ሹም››፤ አፄውም መለስም ይስማሙበታል። (በነገራችን ላይ አጼ ኃይለሥላሴም የኒኮሎ ማኪያቬሊ ቀንደኛ ተከታይ ነበሩ) እናም አፄው ብቸኛው ፀሐይ ይሆኑ ዘንድ ብዙ ፀሐዮችን አጨለሙ። የዚህ ውጤትም ነው የ66ቱ አብዮት ፈንድቶ ‹‹ደርግ›› ፊቱን ወደ ቤተ-መንግስቱ በመለሰ ጊዜ ከልዑላኑም ከሹመኞቹም አማራጭ ‹‹ፀሀይ›› እንዳይገኝ ያደረገው፡፡ በወቅቱ ደርግ አማራጭ በማጣቱ ደራሲ አዲስ አለማየሁን ሳይቀር ‹‹ጠቅላይሚንስትር›› ይሆኑ ዘንድ እስከመጠየቅ የደረሰበት ሁኔታ ነበር፡፡…ይህ ከሆነ ከ38 ዓመት በኋላ ደግሞ ‹‹መለስ ከሌለ ሀገሪቱ ትበታተናለች›› የሚል ስጋት በእያንዳንዳችን ልቦና እንዲያድር መደረጉን ተከትሎ ‹‹የሚተካቸው ሰው›› አሳሳቢ ሆኗል። በእርግጥ በተለይም በግንባሩ የታችኛው ካድሬ ውስጥ ያለው ሁኔታ ፈረንሳይ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ ከገጠማት ችግር ጋር የሚመሳሰል ነው። በወቅቱ የ1789 ዓ.ም. አብዮትን ተከትሎ ወደ ስልጣን የመጣው Robespierre (ሮብስፒር) እ.ኤ.አ በ1794 ሲገደል፣ ጦረኛው Napoleon Bonaparte ስልጣን ላይ ወጣ። ናፖሊዮንም የፈረንሳይ አጎራባች ሀገራትን በመውረሩ በእንግሊዝ መሪነት የተባበሩት ሀገራት አሸንፈውና ከስልጣን አውርደው በኤልባ ደሴት ባሰሩት ጊዜም ሆነ ህይወቱ ካለፈ በኋላ በርካታ ፈረንሳዊያን ‹‹ናፖሊዮን አይሞትም!›› በሚል ተስፋ ተመልሶ እንደሚመጣ ይጠብቁ ነበር።
በኢህአዴግ ካድሬ ውስጥ ያለውም አስተሳሰብ የዚህ ግልባጭ ይመስላል፡ ፡ ‹‹መለስ አይሞትም!›› እናም ከዚህ አኳያ አንዳች ነገር ቢፈጠር ከአመራሩ ውጭ ያለው ካድሬ ለመቀበል የተዘጋጀ አይመስልም። ይህ ደግሞ ሌላ የዶግ አምድ ሊፈጥር መቻሉ አያጠራጥርም፡፡ (ለዚህም ነው ሁለቱም ተወራራሽ የአገዛዝ ባህሪያት አላቸው እያልኩ ያለሁት)
ሁለቱም ከፊታቸው ሊቆም የሚችል ‹‹ተገዳዳሪ›› በተነሳ ጊዜ በአደባባይ እየተቹ ወይም እያስተቹ ያሸማቅቁታል፡ ፡ አንገቱን እንዲሰብር ያደርጉታል። ለምሳሌ እውቁ የማራቶን ጀግና አበበ ቢቂላ የዚህ አይነቱ ፖለቲካ ሰለባ ነው፡፡ አቤ በሁለት ኦሎምፒክ ማሸነፉን ተከትሎ አለም አቀፍ ዝናን አገኘ። ይህን ጊዜም የምዕራብ ሀገራት ሚዲያ ኢትዮጵያን ሲያነሱ ‹‹የአፄ ኃይለሥላሴ ሀገር…›› የሚሉበትን ተቀጽላ ‹‹የአበበ ቢቂላ ሀገር…›› በሚለው ቀየሩት። በሁኔታው የተከፉት ንጉሱም ሌላ ‹‹ፀሐይ›› እየወጣ እንደሆነ አልተሰወራቸውም፡፡ ስለዚህም አትሌቱን በአደባባይ (በሚዲያ) መተቸቱን አጀንዳ አደረጉት፡፡ እናም ከዕለታት በአንዱ ቀን ‹‹…እጅግም መታበይ ደግ አይደለም። የዚህ ሁሉ ፈቃጅ እግዚአብሔር መሆኑን አስታውስ›› አሉና አጣጣሉት። …በአንድ ወቅት ታጋይ አርከበ እቁባይ የአዲስ አበባ ከንቲባ ነበሩ። በዘመነ ከንቲባነታቸውም ከተማዋን ካንቀላፋችበት ‹‹የሚቀሰቅስ›› የሚመስል ነገር ለማድረግ ሞከሩ። በዚህም የከተማው ዕድገት በሚያሳስበው ነዋሪ ዘንድ የአርከበ ስም ተደጋግሞ ይነሳ ጀመር። ይህ ከአቶ መለስ የሚሰወር አይደለም። ከእነዚህም ‹‹የአርከበ መብቂያ›› ወራት በአንደኛው ቀን አቶ አርከበ የኤች አይ ቪ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ ለመቀስቀስ በአርአያነት ራሳቸው ተመረመሩ። ተመርምረው ሲያበቁም ደማቸው ለናሙና ሲወሰድ የሚያሳይ ምስል በትልቅ ቢልቦርድ ተሰርቶ በከተማው እምብርት እንዲሰቀል አደረጉ። ይህ በሆነ ማግስትም የአርከበን ምስል የያዘው ግዙፉ ቢልቦርድ ‹‹መኪና ገጨው›› ተብሎ ወደቀ፡ ፡ ከወደቀም በኋላ እንደፈረሰው የሌኒን ሀውልት ከቦታው ተነስቶ ተወረወረ። ይህ ብቻም አይደለም፣ ራሳቸው አቶ መለስ ምርመራ ማድረጋቸውን አስመልክቶ ከጋዜጠኛ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ‹‹ተመርምሬአለሁ። ነገር ግን ለገበያ አላቀረብኩትም›› አሉና በዘወርዋራ ለአቶ አርከበ ‹‹ልታይ ልታይ ማለት ደግ አይደለም›› የሚል መልዕክት አስተላለፉ።
ሌላ ተመሳስሎ ልጥቀስ። አፄው በበርካታ ቦታዎች ስልጣን የሚሰጡት (ከባንዳ በተጨማሪም) በጨካኝነታቸው እና በስግብግብነታቸው ለታወቁ መኳንንቶች እንደሆነ ይነገራል። ምክንያታቸው ደግሞ እነዚህ መኳንንቶች በጨካኝ አስተዳደራቸው ህዝቡን ያስለቅሳሉ፣ ያማርራሉ፡፡ ይህ አካሄድ በመጨረሻ ጉዳዩ ወደ እሳቸው ሲደርስ ትንሽ መፍትሄ ለመስጠት እና መጠነኛ ማስተካከያ ለማድረግ እንዲያመቻቸው ነው። ይህን ጊዜም ህዝቡ ‹‹ንጉሡ እኮ ሩህሩህ እና ቅን አባት ናቸው። ጨካኞቹ መኳንንቶቹ ናቸው›› ሲል ቁጣውን ከስርአቱ ወደ አስፈፃሚው ያወርዳል። እንዲሁም ከንጉሱ ውጭ አማራጭ እንደሌለው ያስባል፡፡ የንጉሡም ፍላጐት ይህ ነው፡፡ ምህረት እና መልካም አስተዳደር የሚፈልቀው ከእኔ ብቻ ነው የማለት። የአቶ መለስ የአለፉት የአስራ አንድ ዓመታት ጉዞም ይህንኑ ነው የሚተርክልን፡፡
ሌላ አይደለም፡፡ ይህ አይነቱን ስልት አምባገነን ገዥዎች ብቻ ሳይሆኑ ‹‹ሆሊውድ››ም ይጠቀምበታል። ሆሊውድ በሚያዘጋጃቸው በርካታ ፊልሞች ላይ የመሪ ገፀ-ባህሪዋን ቁንጅና ለማጉላት በመልከ ጥፉ አክተሮች አጅቦ ያሳየናል። አይኖች ሁሉ፣ ጆሮዎች ሁሉ ወደ ዋናዋ አክትር እንዲያተኩር፡፡ ይህ ቴክኒክ ከፊልም ወደ ፖለቲካ ሲገለበጥ ደግሞ ተቀባይነት የሌላቸው እና የአቅም ችግር ያለባቸው ግለሰቦች ወደ ስልጣን እንዲወጡ የሚደረግበት ስልት ሆኖ እናገኘዋለን። የጠቅላይ ሚኒስትሩን ‹‹ፀሐይነት›› ይበልጥ ለማድመቅ ማለት ነው፡፡ በአናቱም ባለስልጣናቶቻቸው ከኢትዮጵያውያን ስነ ልቦና በተቃራኒ እንዲቆሙ የሚያደርጉ ጨዋታዎችን አብዝተን እንድንመለከት የተደረግንበት ጊዜ አንድና ሁለት ብቻ ተብሎ የሚቆጠር አይደለም። ለምሳሌ ለተደጋጋሚ ጊዜ ባለስልጣኖች የተሳተፉበት የእግር ኳስ ውድድር ተደርጓል። በውድድሩ ላይ ግን አንድም ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አልተሳተፉም። ይህ የሆነው ከፀጥታ ጉዳይ እና ካለመመቸት ጋር ተያይዞ ብቻ አይደለም። ሆን ተብሎ ነው። አቶ መለስ የኢትዮጵያውያንን ስነ ልቦና ያውቁታል። ሀበሻ ሱሪውን አውልቆ ኳስ የሚራግጥ ባለስልጣን ላይ እምነት ጥሎ እንደመሪ እንደማይከተልም ጠንቅቀው ያውቁታል። ለዚህም ነው እነ አቶ አባዱላ ገመዳ እና ሌሎች ባለስልጣናቶች እንዲያ እንዲሆኑ የሚደረገው። ከዚህ በተጨማሪም የስልጣን መሠረታቸው እንዳይናጋ ከብቃት ይልቅ ታማኝነትን እንደ መስፈሪያ ይጠቀሙበታል። ለምሳሌ አጼው ‹‹ጋብቻ››ን ዋና የፖለቲካ መጠበቂያ ያደርጉት ነበር። ይህ አካሄድም ከንጉሡ የዘር ማንዘር ጋር የተጋባ ባለስልጣን ሁሉ ከ‹‹አማቹ›› ውጪ የሚቀርበው ስለማይኖር የንጉሱን ስልጣን መጠበቅ የህልውና ጉዳይ ይሆንበታል። የ‹‹ጋብቻ ፖለቲካ›› አቶ መለስ ጋ ሲደርስ ደግሞ ‹‹በአውራጃ ትስስር›› እና ‹‹በታማኝነት›› ተለውጦ እናገኘዋለን፡፡ በዚህ አይነት የፖለቲካ ጨዋታ ለዓመታት ታሽቶ ያለፈው የአቶ መለስ መንግስት ከአቶ መለስ ጤንነት ጋር በተያየዘ አደጋ ተጋረጦበታል፡፡ የሰሞኑ ‹‹አራት ኪሎ›› ባልተለመደ የፖለቲካ ትኩሳት መጋልም የዚህ ምክንያት ነው፡ ፡ በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ በጥርጣሬ ሲታይ የነበረው የጠቅላይ ሚንስትሩ ‹‹የመተካካት ፖሊስ››ም ከጊዜው በፊት የደረሰ ይመስላል፡፡ በጠና መታመማቸውን ተከትሎ ማለቴ ነው፡፡ በእርግጥ ሀገሪቱ በዴሞክራሲያዊ ስርዓት የታነፀች ብትሆን ኖሮ በእንዲህ አይነት ጊዜ ‹‹ወንበሩን›› ለመያዝ በሚፈልጉ ተፎካካሪዎች መሀከል ውጥረት አይፈጠርም ነበር፡፡ ምክንያቱም ጠቅላይ ሚንስትሩ ህይወታቸው ቢያልፍ ወይም ከባድ የጤና መታወክ
ቢገጥማቸው የሚተካቸው ሰው ማን እንደሆነ አስቀድሞውን ‹‹በሚተገበር›› ህግ በግልፅ ተደንግጓል፡፡ የኢትዮጵያ ግን ከዚህ ይለያል፡፡ ጉዳዩን ይበልጥ ግልፅ ስናደርገው ከአገልግሎት ዘመናቸው በፊት ጠቅላይ ሚንስትሩ በድንገተኛ ሁኔታ ከስልጣን ቢነሱ እሳቸውን ለመተካት የህግ ድጋፍ ያላቸው ‹‹የምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ሹመት›› በማይተገበር ህግ የታነፀ የፖለቲካ ጫወታ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ እናም የወንበሩ ይገባኛል ጥያቄ ከሀገሪቱ ህግ ይልቅ የፖለቲካ ጉልበት በማሰባሰብ ወደ ሚደረግ ‹‹ስልጣን የመነጣጠቅ ትግል›› ያመዝናል ማለት ነው፡፡ ይህ አይነቱ ፉክክሩም ሄዶ ሄዶ አንድ አሸናፊ ሊያወጣ ስለማይችል ‹‹የስልጣን ክፍተት›› (Power Vacuum) መፍጠሩ አይቀርም፡፡ እንዲሁም ከአቶ መለስ ዜናዊ ‹‹የአንድ ሰው አስተዳደር›› ዝቅ ስንል ፓርቲያቸው ከውስጡ ለመነጨ አደጋ ተጋልጦ እናገኘዋለን። ምክንያቱም የተወሰኑ ኢህአዴግ አመራር አባላት ግንባሩ አሁን ባለበት ሁኔታ ደስተኛ አይደሉምና። ለፓርቲው ቅርበት ያላቸው ሰው የነገሩኝ በቀጣዮቹ ወራት ድርጅቱ የመሰንጠቅ አደጋ ሊያጋጥመው እንደሚችል የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በቢሮአቸው ያለመገኘት ጋር ተጋምዶ በፖለቲካው ላይ አዲስ ምዕራፍ ሊከፈት የሚችልበት ዕድል መፍጠሩ አይቀሬ ነው። ከዚህ አንፃርም ጥቂት የቢሆን ስሌቶችን (Scenarios) ብናይ ጠቃሚ ይመስለኛል፡፡
የግንባሩ አባል ፓርቲዎች ፍላጎት
ግንባሩ የአራት ብሄርን ማዕከል ያደረጉ ፓርቲዎች ጥምረት ከመሆኑ አኳያ ከላይ ያየናቸው አደጋዎች በቀረቡት ጊዜ ነጥሮ የሚወጣው በግርግሩ የተናጥል ፓርቲን ተጠቃሚ የማድረግ ፍላጎት ነው። በተለይ ደግሞ አብላጫ ቁጥር ያለውን ብሔር እንወክላለን የሚሉት ኦህዴድ እና ብአዴን በዚህ አይነቱ ‹‹ሽሚያ›› ዕድሜ ጠገብ ቅራኔዎች እና መገፋቶችን እያነሳሱ ዋነኞቹ ተሳታፊዎች ሆነው በአዲስ ‹‹አቁማዳ›› ብቅ ሊሉ ይችላሉ። እዚህ ጋር ምንአልባት የህወሓት ነባር ሰዎች ከሚጠብቃቸው ፉክክር ለማሸነፍ አዲስ ነገር ሊያመጡ ይችላል። እስከዛሬ የነበረውን የብሔር ኮታ ስልጣን የመከፋፈል አሰራርን ‹‹ብቃትን መሀከል ያደረገ›› በሚል ቀይረው ማለቴ ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ ዞሮ ዞሮ በሚኒስትር ማዕረግ በተመደቡበት ቦታ የተሻለ እየሰሩ ነው ተብሎ የሚታሰቡት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም የህወሓት ቀጣዩ ‹‹ጆከር›› ሊሆኑ ይችላሉ። ረጅም ጊዜ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የሰሩት ብርሃነ ክርስቶስም ሌላኛው ‹‹ጆከር›› ሊሆኑ ይችላሉ። ከዚህ ሌላ ደግሞ በቅራኔ ወይም ቁስል በመነካካት ላይ የተመሰረተ ጨዋታን ከጀመሩ አቶ መለስና ጓደኞቻቸው ያስተዋወቁት የብሄር ፖለቲካን በከፍተኛ ግፊት ያጠናክረዋል። የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪው ሌሎች ብሄሮችን ጨቁኗል የሚለው የፖለቲካው አተናተን፣ ይህም በተለየ መልኩ የተነገራቸው በራሱ በኢህአዴግ ውስጥ ያሉ የኦሮሞ ልሂቃን “በታሪክ የተፈፀሙ” የሚሏቸውን ጭቆናዎች ለማወራረድ ‹‹አሁን ጊዜው የኦሮሞ ነው›› የሚል ባንዲራ ይዘው ወደ ስልጣን መተጋገሉ ሊመጡ ይችላሉ።
እንዲሁም ምንም እንኳን የቀድሞ ጥንካሬው የከዳው ቢሆንም ደርግን ለመጣል በተደረገው ትግል ‹‹የአንበሳውን ድርሻ›› የሚይዘው ህወሓት ‹‹የአቶ መለስ ብቸኛ ወራሽ›› ለመሆን የሚያደርገው ትግልም በቀላል የሚታይ ላይሆን ይችላል።
ከዚህ ባለፈ ብዙም የ‹‹ፖለቲካ ጉልበት›› የሌለው ወይም የ‹‹ፖለቲካውን ሻጥር›› ከህወሓት እና ብአዴን እኩል ሊያዳውረው የማይችለው ‹‹ደኢህዴን››፣ መሪዎቹን እና ወሳኝ ካድሬዎቹን ከጎናቸው ለማሰለፍ ሶስቱም ድርጅቶች ከሚያደርጉት ትንቅንቅ ባለፈ ‹‹በራሱ ለመቆም›› የሚያደርገው ትግል ላይኖር ይችላል። ደኢህዴን በዋናነት በራሱ ሊቆም የማይችልበት ዋናው ምክንያት ፓርቲው በትግሉ ዘመን ያልነበረ መሆኑና፤ አብዛኛው የፓርቲው አመራር በፓርቲው ካድሬ ድጋፍ ሳይሆን በአቶ መለስ ምርጫ ወደ ላይ የወጣ በመሆኑ ነው። ስለዚህም ከአቶ መለስ ‹‹አደገኛ የጤና መታወክ ጀርባ›› የሚኖረው የግንባሩ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል፡፡ የፖለቲካ ተንታኞች ደጋግመው የሚነግሩን ደግሞ በግንባር ደረጃ በተለያዩ ፓርቲዎች በተመሰረተ ድርጅት ውስጥ የዚህ አይነቱ ውጥረት ፈንቅሎ ሲወጣ ድርጅቱ ችግሩን ከመፍታት ይልቅ ሙሉ በሙሉ ሊከፋፍል ወይም ሊፈርስ የሚችልበትን ዕድል እንደሚያሰፋው ነው።
የሸዋ ፖለቲካ
አፄ ምንሊክ ከሞቱ በኋላ ስልጣናቸውን ወደራሳቸው ‹‹ሰዎች›› ለመሳብ በሹማምንቱ (በእቴጌ ጣይቱ በንጉስ ሚካኤል አሊ እና በእነ ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ) መካከል የሶስትዮሽ ፉክክር እንደነበር ያለፈው ዘመን ትርክት ይናገራል፡፡ የታሪክ ተመራማሪዎች እንዲህ አይነቱን በጥሎ ማለፍ ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ጨዋታ በተለምዶ ‹‹የሸዋ ፖለቲካ›› ይሉታል።
በዚህ ዘመንም በስርዓቱ ላይ ‹‹የሸዋ ፖለቲካ›› መከሰቱ አይቀሬ እንደሆነ የሚጠቁሙ ምልክቶች እየታዩ ነው፡፡ በዚህ ጨዋታ ላይም አብዛኛው ሚኒስትሮችን፣ እንዲሁም ወሳኝ የብአዴን እና የኦህዴድ ካድሬዎችን ከጎናቸው ሊያሰልፉ ይችላሉ ተብለው የሚታሰቡት አቶ በረከት ስምኦን ከተገዳዳሪዎቹ አንዱ ሊሆኑ ይችላሉ። በረከት ስምዖን (በወሬ ደረጃ እየተነገረ ያለውን) ‹‹ዶ/ር ቴዎድሮስ አደህኖም አቶ መለስን ተክተው እየሰሩ ነው›› የሚለውን ንግርት ላይቀበሉት ይችላሉ። ዶ/ሩ ለግንባሩ የድል አጥቢያ አርበኛ መሆናቸውን ‹‹በማደማመቅ›› በአናቱም የራሳቸውን የትግል ታሪክ በማግነን ‹‹የመስራች ታጋይነት መብቴን አስከብራለሁ›› ሊሉ ይችላሉ፡፡ (ዶ/ሩ የአቶ መለስ ተተኪ እንደማይሆኑ አንድ ለፓርቲው ቅርብ የሆኑ ሰው ነግረውኛል። በዚህ ወቅትም ብዙ ስራዎችን እየሰሩ ያሉት ዶ/ሩ ሳይሆኑ ከመንግሥት ስራ በጡረታ የተገለሉት አቶ አዲሱ ለገሠ እንደሆኑ ይነገራል)
በተለምዶ ‹‹የእነ ተወልደ ቡድን›› የሚባለውም (ከህወሓት በ1993 ዓ.ም. የወጣው አመራር) በዚሁ አጋጣሚ ‹‹አላዛር›› ለመሆን የሚሞክርበት እድል አለ። ይህ ከሁለት አንፃር ነው የሚታየው። የመጀመሪያው በራሳቸው በአቶ መለስ ፍላጐት ‹‹ህወሓትን ለማዳን›› በሚል ጥቅሻ የቀድሞውን ቅያሜ ‹‹ይቅር ለፖለቲካ›› በማለት ህወሓትን ለማዳን በጋራ ሊሰለፉ መቻላቸው ሲሆን፤ ሁለተኛው ግን ቡድኑ በተናጠል በተለይም ስዬ አብርሃ፣ ገብሩ አስራአት፣ አረጋሽ አዳነ… ከህወሓት ከወጡ በኋላ ከተቃዋሚዎች ጋር አብረው መስራታቸው የተሻለ የተደማጭነት እድል ሊፈጥርላቸው የመቻሉን አጋጣሚ በማስላት ዕድላቸውን መሞከራቸው የሚጠበቅ ነው። ምንአልባት ይህ ቡድን ነባር ታጋዮችን እና ከኢህአዴግ ጋር ባለመግባባት በጡረታ የተገለሉትን አቶ ተፈራ ዋልዋን ሊያካትት ከቻለም የብአዴንን ድጋፍ ከአቶ በረከት ሊነጥቅ የሚችልበትተጨማሪ የዕድል ቁጥር አለው።
አባይ ፀሐዬ፣ ስዩም መስፍን፣ አርከበ ዕቁባይን የመሳሰሉ አንጋፋ አመራሮችም ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ‹‹ልሞክረው›› ሊሉ የሚችሉበት አጋጣሚም ሌላኛው የጫረታው ተሳታፊ ያደርጋቸዋል። እነዚህ የቀድሞ የህወሓት ነፋስ-አባቶች በ1997ቱ ምርጫ ቅንጅትን እናሳንስበታለን በሚል ሊጠቀሙበት የሞከሩትን ‹‹ትግራይን ከሌሎች ጥቃት የማዳን›› መሰል መፈክሮችን ተሸክመው መሰባሰብ ከጀመሩ፣ ወንበሩን ለመያዝ የሚደረገውን ፍትጊያ እጅግ አደገኛ መዘዝ ወደሚያስከትል ‹‹ጫወታ›› ሊቀይሩት የሚችሉበት ዕድል ይሰፋል።
እንግዲህ ከላይ የተጠቀሱት (ኦህዴድ፣ ብአዴን፣ ህወሓት እና ግለሰቦቹ) ‹‹በሸዋ ፖለቲካ›› ስልት ሙሉ በሙሉ ወደ ፉክክር ከገቡ በሀገሪቱ ያለመረጋጋት እና የእርስ በእርስ ግጭት ሊከሰት የሚችልበትን ቀዳዳ ያሰፋዋል። ይህ ትንተና ነው፡፡ ሆኖም አደጋውን ለመከላከል ሁለት አማራጭ የአለ ይመስለኛል።
አማራጭ አንድ
ራሳቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን ባሉበት ደረጃ ለሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች፣ እስረኞች እና ስደተኞች ምህረት አድርገው የታሰሩትን መፍታት፣ የተሰደዱትም ወደሃገራቸው እንዲገቡ መፍቀድ፡፡ እናም አንድም ጊዜ ከወቀሳ አምልጦ የማያውቀውን ምርጫ ቦርድ በትነው በቅንነት እና በታማኝነት በሚሰሩ ሰዎች እንደአዲስ ማወቀር። የፓርላማውንም የስራ ዘመን ክረምቱን እንዳይዘጋ በማድረግ ለዴሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ እንዳይጎለብት ‹‹አፋኝ›› የሆኑትን (የፀረ-ሽብር፣ የመያድ፣ የፕሬስ…) አዋጆች እና ሕጎች እንዲሽሩ በማድረግ፣ የምርጫውን ጊዜ ሳይጠብቁ ሁሉንም ወገን የሚያሳምን ምርጫ እንዲደረግ ማመቻቸት አደጋውን በቀላሉ ከማሰወገዱም አልፎ ገዥውም ተቃዋሚውም፣ ሌላውም ኢትዮጵያዊ የሚወዳትን ሀገር ወደአዲስ የታሪክ ምዕራፍ ያሸጋግራል። ነገር ግን በአቶ መለስ ቦታ ከላይ የጠቀስኳቸው ድርጅቶችና ግለሰቦች ወይም ዶ/ር ቴውድሮስ አድህኖም ወደ ስልጣን እንዲመጡ ከተደረገ በአሮጌ አቁማዳ አዲስ ወይን ከመተካት ውጭ ለውጥ የለውም፡፡ እንዲያውም በግልባጩ ህዝባዊ አመፅ ሊቀሰቅስ ይችላል፡፡
ምንም እንኳ አቶ መለስ ከወራት በፊት የአረብ ዓለም አብዮትን አስመልክተው ለ“Pan-African magazine” በሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ “Ethiopia and much of the Sub-Sharan Africa already had its own African spring back in the 1980’s and the Arabs are latecomers to the game” (ኢትዮጵያ እና አብዛኛው ከሰሀራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት ጣጣቸውን የጨረሱት አስቀድመው በ1980ዎቹ ነው። አረቦቹ ግን ለጨዋታው አርፋጆች ናቸው) ሲሉ እኛ ለአብዮት እንግዳ አይደለንም፡ ፡ ከእነርሱ እንቀድማለን የሚል አንድምታ ባለው መልኩ የነገሩት፡፡ ለመጽሔቱ የነገሩት መተማመኛ የሚገለበጥበት እድል እንደሚኖር የተንታኞች ግምት አለ። ምክንያቱ ደግሞ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ጥያቄ የሚያነሱ ዜጐች ከቀን ወደቀን ቁጥራቸው በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መሆኑ ነው። እናም እንዲህ አይነት ኩነቶችን ተከትለው የሚመጡ የመንግስት የመዳከም ምክንያቶች ‹‹ለውጥ ፈላጊውን›› የህብረተሰብ ክፍል ወደአደባባይ መግፋታቸው አይቀሬ ነው።
አማራጭ ሁለት-የታንታዊ መንገድ
የግብፅ አብዮትን ተከትሎ ስልጣን በወታደራዊው ጂንታ እንዲገባ ካደረጉት ውስጥ ዋነኛ ሠው ናቸው-Field Marshal Mohamed Hussein Tantawi (ፊልድ ማርሻል መሀመድ ሁሴን ታንታዊ)፡፡ ታንታዊ ግብፃውያን በታህሪር አደባባይ መሰባሰባቸውን ተከትሎ ከሌሎች 18 ወታደራዊ ኦፊሰሮች ጋር በመሆን የወታደራዊውን ከፍተኛ ምክር ቤት (SCAF) መስርተው፤ ፕሬዝዳንት ሆስኒ ሙባረክን ለፍርድ በማቅረብ (በፖለቲከኞቹ አነጋገር ‹‹ለአብዮቱ በመሰዋት››) ግብፅን ያረጋጉበት ጥበብ ነው-‹‹የታንታዊ መንገድ››
ምንአልባት ከላይ ባየነው ድንገቴ ፉክክር የተነሳ ሀገሪቱ በፖለቲካ ውጥረት ወደ አልታሰበ ግጭት ብትገባ የኢትዮጵያ መከላከያ ሀይል ሰራዊትም ከታንታዊ መፃሀፍ ‹‹አንድ ገፅ›› ሊገነጥል ከቻለ ለሀገሪቱ መፃኢ ዕድል የተሻለ መደላድል ሊፈጥር ይችላል። በግብፅ የመጣው ለውጥ (ምንም እንኳን አሁንም ወታደራዊው ሀይል በተወሰነ መልኩ ከመጋረጃው ጀርባ ያደፈጠበት ሁኔታ ቢኖርም) ከቀድሞ መንግስት አስተዳደር በእጅጉ የተሻለ ነው። የፖለቲካ ተንታኞች አሁን ያለውን አይነት የታንታዊ መንግስት ጥቂት የኢኮኖሚ ጥያቄዎችን መልሶ ሌሎቹን መሰረታዊ የፖለቲካና የሲቪል መብቶችን የሚጨፈልቅን መሪ ‹‹Benevolent Dictator›› (ደግ አምባገነን) ሲሉ ይጠሩታል፡፡
ከዚህ ባለፈም የካውንስሉ አባል የሆኑት ሜጀር ጄኔራል መሀመድ ሰዒድ አል-አሰር ባለፈው ሳምንት ለታተመው ‹‹Time›› መጽሔት እሳቸውና ጓደኞቻቸው ለአብዮቱ ስላደረጉት አስተዋጾ ሲናገሩ “We have done the best we can for our country. We saved the revolution” (ለሀገራችን የቻልነውን ያህል የተሻለ አድርገናል። አብዮቱንም ታድገነዋል) ምንአልባት ይሄ ገፅ ከነታንታዊ በአማርኛ ቢገነጠል ሀገር ሊታደግ ይችል ይሆናል፡፡

Comments
መልከ (not verified)
Sat, 07/14/2012 - 19:04
Permalink
አትፍሩ
ምንም ይምጣ መጀመሪያ መለስ ይሙት። ሀገራችን እንኳን አሁን ከዚህ በፊት እጅግ መከራና አስከፊ ዘመናት እንኳ በሽማግሌና በጎበዝ አለቃ እራሷን መርታለች። ካልደፈረሰ አይጠራም ነውና እንዴውም ከስህተታችን የምንማርበትና ማንነታችንን የምናውቅበት ዘመን ይመጣ ይሆናል።
abebe (not verified)
Sat, 07/14/2012 - 19:58
Permalink
poletics tentenawe betame
poletics tentenawe betame teru new !!! bihoneme mene ayenet honita endmifetre berget megmet yekbedal betkarniwe degmo bifetre asefri honita ligetmene endmichel egmetalehu ! gen tekuami parti yet gebtew new endmftehi yalneshachew?????
lema (not verified)
Sat, 07/14/2012 - 21:44
Permalink
Tebarek
Dear Teme MedihaneAlem Yenaniten Hagerawi simet temelikito tiru neger Yametal.
Ayizoh Yene Anebesa.
zman (not verified)
Sat, 07/14/2012 - 22:57
Permalink
ተመስገን ...
24 ስዓት ጥብቅ ክትትል እየተደረገብህ መሆኑን አንብቢ በጣም ተጨንቄ ነበር :: ተመስገን .. እግዚአብሄር ከመለስ ይገላግለን እንጅ የተሻለ ቀን እንደሚመጣ ተስፋ አደርጋለሁ :: የመለስ ህልም እንደ ሃገር መሪ ሳይሆን እንደ አንድ ተራ የለት ጉርሱን ናፋቂ ግለሰብ ስለሆነ ከሱ ብቻ ይገላግለን ::
የነገሰው ይበለን !
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
Anonymous (not verified)
Sat, 07/14/2012 - 23:28
Permalink
superficial
superficial
A (000 1) (not verified)
Sun, 07/15/2012 - 01:44
Permalink
You are special.
You are creative and talented writter.I apreciate and have agreat respect for you. you have done the thruth of jornal proffesions.please write always then protect your self from MEGAGNA(In amharic) or dictators. Thank you
አለም (not verified)
Sun, 07/15/2012 - 04:17
Permalink
አገር ወዳድ አርበኛ አይፈለግም
ውድ ተመስገን፣ጥሩ ትንተና ነው። ሁለት የምጨምረው ነጥብ አለኝ። አንድ፣ በአፄ ምኒሊክ፣ ኃይለ ሥላሴና ደርግ ዘመናት ኢትዮጵያዊነት እንጂ እንደ ዛሬው በዋነኛነት ጎሠኛ ፖለቲካ የመንግሥት አመራር አልነበረም። ከትግራይ ውጭ ተተኪ ሊኖር የማይችለው ለዚህ ነው። ሁለተኛ፣ መለስንና ጓዶቹን ሥልጣን ላይ ያወጡት አሜሪካና እንግሊዝ ናቸው። የመለስንም ተተኪ የሚያቀርቡልን እነርሱው ናቸው። በአፍሪቃ ለሚያካሄዷቸው እንቅስቃሴዎች የሚላላካቸውን ነው የሚፈልጉት። መለስ ንጹሐንን ሲያስሩ ሕገ መንግሥት ሲቀይሩ ተቃዋሚ እንዳይኖር ሲያደርጉ የሕዝብ ንብረትና የእርዳታ ገንዘብ ሲመዘበር አሜሪካኖች እያዩ ዝም የሚሉት ጥቅማቸው ብቻ ለማስከበር ከመፈለግ ነው። ቻይና እያንዣበበና አርባ ምንጭ ላይ "ድሮን ቤዝ" አቋቁመው እያለ ማንንም አገር ወዳድ አርበኛ ሥልጣን ላይ ያኖራሉ ማለት ዘበት ነው። የኢትዮጵያውያን ምርጫ በሁለተኛና በሦስተኛ ደረጃ የሚታይ ነው። እንደ ግብጽ ሕዝብ ሆ ብሎ ከተነሳ ብቻ ነው የሕዝብን ድምጽ ከቁም ነገር ለመቁጠር የሚገደዱት። ሕዝቡስ በቅቶታል፤ ለዚህ የሚያበቃ መሪ እንጃ ይኖራል ትላለህ?
dokle (not verified)
Sun, 07/15/2012 - 04:48
Permalink
ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ!!!
ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ!!!
Abay (not verified)
Sun, 07/15/2012 - 07:53
Permalink
Revolution without loss human life
no one daed we need revolution. it is very hard, but we do we did it. After meles
ገብርዬ፡ዘብሔረ፡ኢትዮጵያ (not verified)
Sun, 07/15/2012 - 08:58
Permalink
"የሸዋ፡ፖለቲካ፡" የሚለው፡አነጋገር፡ባትጠቀመው፡የተሻለ፡ነበር!"
ተመስገን፣
ካለንበት፡ወቅት፡በመነሳት፡ያደረግኸው፡እይታ፡ከብዙ፡አንጻር፡ለመወያየት፡ይጠቅማል፡፡
አሳብህ፡ሁሉ፡ለኢትዮጵያ፡በጎ፡እንደሆነ፡ግልጽ፡ነው።
ስለ፡ወታደራዊው፡የመጨረሻው፡አንቀጽህ፡ብዙም፡ስላላልክበት፡ተዳፍኖ፡ቀርቷል።ሊከሰቱ፡
የሚችሉትን፡ሁኔታዎች፡በሙሉ፡ለመተንበይ፡አዳጋች፡ነው።የ"ሊሆን፡ይችላል"አስተሳሰብንም፡ከመላ፡ምት፡አነጋገር፡በላይ፡አድርጎ፡መውሰድ፡ያስቸግራል።
የኢትዮጵያና፡የሕዝቧ፡የወደፊት፡በአርቆ፡አሳቢዎችና፡በእርቀ፤እግዚአብሔር፡በሚያምኑ፡እስካልሆነ፡ድረስ፣ውጤቱ፡በስልጣን፡ታሻሚዎች፡መካከል፡ለኢትዮጵያና፡ለሕዝቧም፡በማይበጅ፡መንገድ፡የሚወሰን፡ይሆናል።
"የሸዋ፡ፓለቲካ"ያልከውን፡ባለፉት፡ሃያ፡አንድ፡ዓመታት፡ውስጥ፡ኢትዮጵያ፡ውስጥ፡ከተከሰተው፡ዓይን፡ያወጣ፡የጎሣ፡እና፡የመንደር፡ፖለቲካ፡ጋር፡ለማዛመድ፡ወይም፡ለማነፃፀር፡መሞከር፡ስህተት፡ነው።ከአፄ፡ምኒሊክ፡በኋላም፡የነበረው፡ፖለቲካ፡ከምኒሊክ፡ሸዌነት፡በስተቀር፣ኢትዮጵያዊ፡ፖለቲካ፡እንጂ፡"የሸዋ፡ፖለቲካ"ሊያስኘውስ፡የሚችለው፡ከምን፡ማስረጃ፡በመነሳት፡ነው?ራስ፡ጎበና፡ዳጬ፣ፊትአውራሪ፡ኃብተ፡ጊዮርጊስ፣ደጃች፡ባልቻና፡ሌሎችም፡ምኒሊካዊ፡የኢትዮጵያ፡ፖለቲካ፡ታሪክ፡አዕማዶች፡እናስትውስ።ለወሬና፡ለጥላቻ፡ተረቶች፡አንበገር!
በኢትዮጵያ፡አንድነት፡ላይ፡የጸኑ፡የታሪክ፡እውነታዎቻች፡ሊዘነጉ፡አይገባም፡፡ማንም"ሊለውጣቸው"አይችልም!እስከዛሬም፡ተሞክሮ፡ያልተሳካው፡ይኸው፡ክህደት፡ነው።ወደፊትም፡አይሳካም!ታሪካዊ፡እስነታዎቻችንና፡አለኝታዎቻችን፡የኛነታችን፡መስታወቶች፡ሆነው፡ይኖራሉ!!!ለጊዜ፡ፈጠርና፡ፀረ-ሸዋ፡አሻሚ፡ንግግር፡ሲባል፡እንዳልነበሩ፡ሊገፉም፡አይገባም።
ሸዋ፡ላይ፡ብዙ፡ሐሰትና፡ጥላቻ፡ስለተነዛ፡እንደውነት፡ተቆጥሮ፡ከማይመሳሰለውው፡አውዳሚ፡ታሪክ፡ጋር፡ማነፃፀሪያ፡አድርጎ፡ማቅረቡስ፡ለምን፡አስፈለገ?ያለንበትን፡ወቅታዊና፡በሃያ፡አንዱን፡ዓመታት፡የጎሣ፡አገዛዝ፡ሥርዓት፡የደረሱብንን፡ለመግለጽ፡የማይገባ፣ጥንት፡ከነበረው፡የአገራችን፡ሥርዓት፡ጋር፡አንዳችም፡ተመሳሳይነት፡ወይም፡ተዛምዶ፡የሌለውን፡የጎሣ፡ሥርዓት፡የወደፊት፡መተንበያነት፡መቅረብ፡የማይገባው፡አስተሳሰብ፡ነው።
ዛሬ፡በስልጣን፡ታሻሚ፡የጎሣ፡አገዛዝ፡ሥርዓት፡ውስጥ፡ስለምንገኝ፣የዚህን፡ከኢትዮጵያ፡ታሪክ፡ውጭ፡የሆነ፡ክስተት፡በራሱ፡ተለምዶና፡ተሞክሮ፡መመዘንና፡ማነፃፀር፡ይበልጡን፡ሊረዳ፡ይችላል።
ስለ፡"ሸዋ፡ፖለቲካ"መነጋገር፡አስፈላጊ፡ከሆነ።ከአድዋ፡እስከ፡ማይጨው፡ጦርነቶች፡ድረስ፡የሸዋን፡ለጠላት፡አልገዛም፡ባይነት፣የእኛ፡ሰው፡ያለውን፡ሳይሆን፡ጣልያኖች፡ያሉትንና፡የጻፉትን፡እየጠርቀስን፡መነጋገር፡እንችላለን።ያን፡ግን፡እርግጠኛውና፡ጠላት፡አይገዛንም፡ባዩ፡ኢትዮጵያዊው፡የ"ሸዋ፡ፖለቲካ"ብሎ"መናገር፡ይቻላል።
የዛሬውን፡ፖለቲካ፡ባይሆን፡በደደቢት፡እንጂ፡በሸዋ፡መመንዘር፡አይቻልም።የ"ደደቢትን፡ፖለቲካ"የወደፊት፣በማይገባው፡"የሸዋ፡ፖለቲካ"፡ተምሳሌት፡መመዝንና፡ማየት፡አይቻልም!!!
የሸዋ፡ፖለቲካ፡መሠረት፡ኢትዮጵያ፡ስትሆን፣የደደቢት፡ግን፡ኢትዮጵያን፡የመገንጠልና፡የማስገንጠል፡መሆኑን፡አንቀጽ፡39ን፡የቸሩን፡ገዢዎቻችን፡ባደባባይ፡ስለነገሩን፡ሁላችንም፡የምናውቀው፡ነው።
እግዚአብሔር፡ኢትዮጵያንና፡ልጆቿን፡ከታለመለን፡ጥፋት፡ሁሉ፡ያድነን።አሜን።
ገብርዬ፡ዘብሔረ፡ኢትዮጵያ።
ገብርዬ፡ዘብሔረ፡ኢትዮጵያ። (not verified)
Sun, 07/15/2012 - 12:14
Permalink
"የሸዋ፡ፖለቲካ፡" የሚለውን፡አነጋገር፡ባትጠቀመው፡የተሻለ፡ነበር!"
ተመስገን፣
(ከላይ፡ያለው፡ስለተቆራረጠ፡በዚህኛው፡ይተካ)
ካለንበት፡ወቅት፡በመነሳት፡ያደረግኸው፡እይታ፡ከብዙ፡አንጻር፡ለመወያየት፡ይጠቅማል፡፡
አሳብህ፡ሁሉ፡ለኢትዮጵያ፡በጎ፡እንደሆነ፡ግልጽ፡ነው።
ስለ፡ወታደራዊው፡የመጨረሻው፡አንቀጽህ፡ብዙም፡ስላላልክበት፡ተዳፍኖ፡ቀርቷል።ሊከሰ
ቱ፡የሚችሉትን፡ሁኔታዎች፡በሙሉ፡ለመተንበይ፡አዳጋች፡ነው።የ"ሊሆን፡ይችላል"አስተ
ሳሰብንም፡ከመላ፡ምት፡አነጋገር፡በላይ፡አድርጎ፡መውሰድ፡ያስቸግራል።
የኢትዮጵያና፡የሕዝቧ፡የወደፊት፡በአርቆ፡አሳቢዎችና፡በእርቀ፤እግዚአብሔር፡በሚያም
ኑ፡እስካልሆነ፡ድረስ፣ውጤቱ፡በስልጣን፡ታሻሚዎች፡መካከል፡ለኢትዮጵያና፡ለሕዝቧም፡
በማይበጅ፡መንገድ፡የሚወሰን፡ይሆናል።
"የሸዋ፡ፓለቲካ"ያልከውን፡ባለፉት፡ሃያ፡አንድ፡ዓመታት፡ውስጥ፡ኢትዮጵያ፡ውስጥ፡ከተከ
ሰተው፡ዓይን፡ያወጣ፡የጎሣ፡እና፡የመንደር፡ፖለቲካ፡ጋር፡ለማዛመድ፡ወይም፡ለማነፃፀር፡መ
ሞከር፡ስህተት፡ነው።ከአፄ፡ምኒሊክ፡በኋላም፡የነበረው፡ፖለቲካ፡ከምኒሊክ፡ሸዌነት፡በስተቀ
ር፣ኢትዮጵያዊ፡ፖለቲካ፡እንጂ፡"የሸዋ፡ፖለቲካ"ሊያስኘውስ፡የሚችለው፡ከምን፡ማስረጃ፡በ
መነሳት፡ነው?ራስ፡ጎበና፡ዳጬ፣ፊትአውራሪ፡ኃብተ፡ጊዮርጊስ፣ደጃች፡ባልቻና፡ሌሎችንም፡
ምኒሊካዊ፡የኢትዮጵያ፡ፖለቲካ፡ታሪክ፡አዕማዶች፡እናስትውስ።
ለወሬና፡ለጥላቻ፡ተረቶች፡አንበገር!
በኢትዮጵያ፡አንድነት፡ላይ፡የጸኑ፡የታሪክ፡እውነታዎቻችን፡ሊዘነጉ፡አይገባም፡፡ማንም፡ሊ
ለውጣቸው፡አይችልም!እስከዛሬም፡ተሞክሮ፡ያልተሳካው፡ይኸው፡ክህደት፡ነው።ወደፊት
ም፡አይሳካም!ታሪካዊ፡እውነታዎቻችንና፡አለኝታዎቻችን፡የኛነታችን፡መስታወቶች፡ሆነ
ው፡ይኖራሉ!!!
ለጊዜ፡ፈጠርና፡ፀረ-ሸዋ፡አሻሚ፡ንግግር፡ሲባል፡እንዳልነበሩ፡ሊገፉም፡አይገባም።
ሸዋ፡ላይ፡ብዙ፡ሐሰትና፡ጥላቻ፡ስለተነዛ፡እንደውነት፡ተቆጥሮ፡ከማይመሳሰለው፡አውዳ
ሚ፡ታሪክ፡ጋር፡ማነፃፀሪያ፡አድርጎ፡ማቅረቡስ፡ለምን፡አስፈለገ?ያለንበትን፡ወቅታዊና፡
በሃያ፡አንዱ፡ዓመታት፡የጎሣ፡አገዛዝ፡ሥርዓት፡የደረሱብንን፡ለመግለጽ፡የማይገባ፣ጥን
ት፡ከነበረው፡የአገራችን፡ሥርዓት፡ጋር፡አንዳችም፡ተመሳሳይነት፡ወይም፡ተዛምዶ፡የሌ
ለውን፡የጎሣ፡ሥርዓት፡የወደፊት፡መተንበያነት፡መቅረብ፡የማይገባው፡አስተሳሰብ፡ነው።
ዛሬ፡በስልጣን፡ታሻሚ፡የጎሣ፡አገዛዝ፡ሥርዓት፡ውስጥ፡ስለምንገኝ፣የዚህን፡ከኢትዮጵያ፡ታ
ሪክ፡ውጭ፡የሆነ፡ክስተት፡በራሱ፡ተለምዶና፡ተሞክሮ፡መመዘንና፡ማነፃፀር፡ይበልጡን፡ሊ
ረዳ፡ይችላል።
ስለ፡"ሸዋ፡ፖለቲካ"መነጋገር፡አስፈላጊ፡ከሆነ።ከአድዋ፡እስከ፡ማይጨው፡ጦርነቶች፡ድረስ፡
የሸዋን፡ለጠላት፡አልገዛም፡ባይነት፣የእኛ፡ሰው፡ያለውን፡ሳይሆን፡ጣልያኖች፡ያሉትንና፡የጻፉ
ትን፡እየጠቀስን፡መነጋገር፡እንችላለን።ያን፡ግን፡እርግጠኛውና፡ጠላት፡አይገዛንም፡ባዩ፡ኢ
ትዮጵያዊው፡የ"ሸዋ፡ፖለቲካ"ብሎ"መናገር፡ይቻላል።
የዛሬውን፡ፖለቲካ፡ባይሆን፡በደደቢት፡እንጂ፡በሸዋ፡መመንዘር፡አይቻልም።የ"ደደቢትን፡
ፖለቲካ"የወደፊት፣በማይገባው፡"የሸዋ፡ፖለቲካ"፡ተምሳሌት፡መመዝንና፡ማየት፡አይቻል
ም!!!
የሸዋ፡ፖለቲካ፡መሠረት፡ኢትዮጵያ፡ስትሆን፣የደደቢት፡ግን፡ኢትዮጵያን፡የመገንጠልና፡የ
ማስገንጠል፡መሆኑን፡አንቀጽ፡39ን፡የቸሩን፡ገዢዎቻችን፡ባደባባይ፡ስለነገሩን፡ሁላችንም፡
የምናውቀው፡ነው።
እግዚአብሔር፡ኢትዮጵያንና፡ልጆቿን፡ከታለመለን፡ጥፋት፡ሁሉ፡ያድነን።አሜን።
ገብርዬ፡ዘብሔረ፡ኢትዮጵያ።
Workamaw (not verified)
Sun, 07/15/2012 - 16:12
Permalink
workamaw@yahoo.com
In my opinion, the possibility that individuals like Bereket coming to poer, and that on the shoulders of ANDM is quite remote. Bereket has lost all credibility in this organization. The Amhara society has never recognized ANDM as its representative, and least of all Bereket Simon. I do not either see the possibility that any of the other "member" organizations of EPRDF would play an important role. They are puppets designed to be feeble and subisive by TPLF. Any upcoming power struggle within EPRDF will be within TPLF. It is, however, a high possibility that attempts would be made to pull back the disgruntled former senior TPLF members like Siye, Gebru, Aregash, etc. This can be seen as a multifaceted strategy by anyone who is capable of crafting a longer life to TPLF.
Anonymous (not verified)
Mon, 07/16/2012 - 02:36
Permalink
i dont no
i dont no
sal (not verified)
Mon, 07/16/2012 - 10:01
Permalink
all what u write is a kind of
all what u write is a kind of extra oridinary and trash that we have bored of hearing for many years and a repeatitive! although the meles rule is dictator do u know that nothing is better than the agenda u and ur realtives are working for.
da (not verified)
Mon, 07/16/2012 - 11:37
Permalink
death is not a punishment
i see all the comment everyone wish death to melese but this is not write if he is dead then what is the profit and what lesson did he learn he must leave and see what we can do,what this youth can do and feel sorry for what he have done
Eyob (not verified)
Mon, 07/16/2012 - 11:46
Permalink
our history tells otherwise
Ere gobez, gena "wetu sayiwetewet" From our history we can clearly see that it is hard to determine who comes to power and when. starting from the time of minilik who expected hailesilasssie to come to power, who expected mengistu to come to power? so I believe we will be surprised as usual.
yaltetebqew (not verified)
Mon, 07/16/2012 - 12:26
Permalink
if
first let meles die,it might be an answer for the prayers of many ethiopians for the last 20 years.EPRDF will die with meles togather because it has no soul apart from meles.then the people will own his country for the first time in history and will decide positively what to do for the present and future of ethiopia. i hope we will no more see the so called dictators and strong man like meles and mengistu.
mela (not verified)
Mon, 07/16/2012 - 12:44
Permalink
DREAM TELLER!!
DEAR TEMESGEN
I KNOW WE ALL SAY WE NEED ETHIOPIA. IF U WANT ETHIOPIA MAKE U R PEOPLE TO STRUGGLE FOR TRUTH NOT FOR DREAM. HERE U HAVE THE SYSTEM. IF U R NOT WITH THE NATION SYSTEM THAT IS ANOTHER THING. SYSTEM MATTERS; WHO EVER COMES AND GO NOTHING WILL HARM PEOPLE. BECAUSE ETHIOPIAN PEOPLE HAS THE SYSTEM.
TEMESGEN ANDANDE NETE FELAGINETEHEN TABEZAWALWH- PLEASE THING ABOUT TRUTH. HAVE CREADIBLE SOURSE; OTHER WISE AM SURE U MAY DAMAGE UR FAMILY FIRST. AM NOT TELLING U TO FRUSTRATE SINCE U MANY TIMES TEL US THE U SCARED. ANY WAY THINK POSITIVE.
BY THE WAY . UR ARTICLE IS AS EQUAL AS WHAT TESFAYE GEBREAB WROTE IN ''YE GAZETEGNAW MASTAWESHA - PART TWO''. MANY OF U HVE ONE LUNG THAT U BREATH IN & OUT. MEDREK,FETEH. ESAT, TESFAYE GEBREAB,.....
Anonymous (not verified)
Mon, 07/16/2012 - 14:41
Permalink
But do we have an educated
But do we have an educated and far sighted Military leaders who may lead us on Tantawi road? Once the PM has said(I don't know where I got from) that educated military would suck its own leader; and Ethiopia has learnt same from her last emperor. I think such thinking has been the driving force behind the de-literating action on the military(who is the Chief of Staff of Ethiopian Military?). Hence it is a luck to have Tantawi and its colleagues.
Anonymous (not verified)
Mon, 07/16/2012 - 15:16
Permalink
It is a luck to have Tantawi
It is a luck to have Tantawi(with reservation) on such cases. Do we have military leaders that bring themselves out if we face chaos? I don't believe so as first the current military officials were not exposed to military science and are behind world politics. Once I heard that the PM himself has said that educated military would suck its leader and Ethiopia has learnt that with her last emperor. With this thinking, I believe, the PM has done its homework well ahead by de-literate its military camp successfully.(Who is the current Chief of Staff?). Second, the military itself is deeply divided with ethnic narrow mindedness, which is unlikely to unite when needed. Third, as any part of the people, the low ranking members are irritated by their leaders and are unlikely to follow orders in a discipline the time needs.Fourth, I expect they would follow the politics as they still are more faithful for their party/'leader' than their profession/country. In such time, they follow their leader/followee. So I don't expect solutions from Tantawi camp.
no one (not verified)
Mon, 07/16/2012 - 15:36
Permalink
ሀበብተት በባነናበባከክነን
ውድ ተመስገን
ጊዜህን በማይሆን ነገር ላይ ለምን እንደምታባክን አይገባኝም!!!
ያልተገለፀልኝ ነገር ካለ ቢገለፅልኝ መልካም ነው፡፡
ኑሮ መረረ (not verified)
Mon, 07/16/2012 - 16:28
Permalink
ኣስተያየት
ወንድሜ ጥሩ እይታ ነው ያለህ፣በርታ፣ኣብሺርርርር።ግን የኣቶ መለስ መሞት መዘዝ ኣለው።ቢሆንም ሃገራችን ለመከራ ኣድስ ስላልሆነች የሆነው ይሁን ።ኧረ ኣምላክ ኣንድ ነገር ይበለን።ኣሜንንንንንንንንንን።
Ethiopia (not verified)
Mon, 07/16/2012 - 18:28
Permalink
Oh
Ketlbet
C.E.O (not verified)
Mon, 07/16/2012 - 19:21
Permalink
Like that
Temesgen Desalegn!
You are a hero! you will be a legend which deserves to stand a monument while alive! you are the only Ethiopian who live alive! you challenge the "unchallengeable" elephant. What makes Meles and his blind followers alive is nothing but the poor reading culture of the Ethiopian people. i.e Only few reads compared to the number population. We will help you in reading and responding soon! I never miss fetehe each week. I fall in love with fetehe.com! long live to you and meet you in new Ethiopia which is your dream.
netsanet (not verified)
Tue, 07/17/2012 - 10:00
Permalink
my opinion
This is an interesting article.1st of all meles zenawin egziher yemarew yes le weg bahil aydelem bewnet yemarew. meles doesnt deserve death not now he should b alive 2 c what Ethiopia can b with out him. yemarew malet melso seltan yeyaz malet aydelem.2nd after meles EPRDF besu yemiteka mefelegu aykerem ega gin man yehon kemalet keahunu menegager, meweyayet,megebabat aleben! yehe eko edel new enetekemebet----lemegebabat,lemesemamat! if we r 2gether, united there is nothing we cant withstand. this is a rare opportunity 4 z opposition 2 do what should b done 2 save ETHIOPIA.3rd ye Ethiopia military derg lay abktoal.ahun be telacha yetemola bale temenga wetat nw yalew. plz listen help is not gonna come from America, England or even the Ethiopian diaspora we hold z key!that is MEGBABAT,MENEGAGER!!!look @ Egyptians.....need i say more??
Add new comment