‹‹ይቅርታ›› የኢህአዴግ ቃጭል? ወይስ…
1998
አዲስ አበባ በለውጥ ፍላጐት ከአፍ እስከ ገደቧ ታጥናለች። እዚህም እዚያም የፖለቲካ ወግ ይጠሰቃል። በቡድን ሆነው፣ በስሜት ተውጠው በፖለቲካ ጉዳይ የሚከራከሩ በርክትዋል፡ ፡ ለዓመታት የፖለቲካ ጉዳይ ‹‹ፆም›› የሆነባቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሳይቀሩ ጎራ ለይተው በሚከራከሩ ሠራተኞቻቸው ተፈስገዋል፡፡ ‹‹ቅንጅቱ መንግሥት ለመመስረት የሚያስችል ድምፅ አግኝቷል›› ይላል አንዱ። ‹‹ቢሆንም ኢህአዴግ ይገግማል!›› ሲል ይመልሳል፤ ኢህአዴግ በምርጫ ስልጣን አይለቅም የሚል አቋም ያለው ተከራካሪ፡ ፡
…የጋዜጦች እትሞች ከምርጫው በፊት ከነበረው ቅጂ ከሶስት እስከ አምስት እጥፍ ድረስ ጨምረዋል። ማንበብ የሚችለውም፣ ማንበብ የማይቻለውም ቋሚ የጋዜጣ ሸማች ሆኖአል-እድሜ ለምርጫው። በኢትዮጵያ ‹‹መንግሥት…›› ሲባል የተቃወመውን በሙሉ የሚገድል እንደሆነ ከልምድ የተገነዘቡ ወላጆች ለልጆቻቸው በመስጋታቸው ጭንቀታቸው ጨምሯል፡ ፡ እነዚህ ኩነቶች የድህረ ምርጫ 1998 ዓ.ም. ዋነኛ መገለጫዎች ነበሩ፡፡
እንዲህ ውጥረት በነገሠበት አንድ ቅዳሜ ከቅንጅቱ ዋነኛ አመራሮች አንዳቸውን በአካል ልተዋወቅ ወደ ቀጠሮ ቦታ እየሄድኩ ነው-መስከረም 28 ቀን 1998 ዓ.ም.፡፡ በምርጫው ላይ የጎላ ተሳትፎ የለኝም። የየትኛውም ፓርቲ አባል አይደለሁም። ድምፄንም ለማንም አልሰጠሁም። ነገር ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ እልፍ አእላፎችን ከጎኑ ማሰለፍ ከቻለው ‹‹ቅንጅት›› መሪዎች አንዳቸውን ልተዋወቅ ነው። የሚያስተዋውቀኝ ደግሞ በእጅጉ የማከብረውና የማደንቀው የጋራ ወዳጃችን አብይ ተክለማርያም ነው። ያኔ ተወዳጇ አዲስ ነገር ጋዜጣ አልተመሰረተችም። አብይ የሚያዘጋጃት ‹‹መዝናኛ›› የተባለች በድህረ ምርጫ እየገነነች የመጣች ጋዜጣ ግን ነበረች። ቀጠሮአችንም ጋዜጣው ቢሮ ውስጥ ነው። ልተዋወቅ እየሄድኩ ያለሁት የቅንጅቱ ምክትል ሊቀመንበር ሆና ከተመረጠች 14 ቀናት ብቻ ካለፋት ከብርቱካን ሚደቅሳ ጋር ነው፡፡ (እርግጠኛ ባልሆንም ብርቱካን ቀድማኝ የደረሰች መሰለኝ) …በጥቂት ደቂቃ ልዩነት ውስጥ ዝናዋ በአጭር ጊዜ ከናኘው እንስቷ ፖለቲከኛ ብርቱካን ጋር ተገናኘን። ከዚህ ቀደም እንደሚተዋወቁ ወዳጆች የሞቀ ሰላምታ ተለዋወጥን፡፡ ዛሬ ፋይሏ በተዘጋው በመዝናኛ ጋዜጣ ቢሮም ለአንድ ሰዓት ያህል አወራን። ብዙ ነገሮችን አነሣን፣ ብዙ ነገሮችን ጣልን። ኢህአዴግ እየተፍረከረከ እንደሆነ ግምቷን ነገረችኝ። ከኢህአዴግ አመራር ውስጥም ሙሉ በሙሉ መሸነፋቸውን የተቀበሉ ሰዎች እንዳሉ ተነጋገርን፡፡ አንዳች ለውጥ እንደሚኖርም አብዝተን ተስማማን፡፡ ከቆይታችን በእጅጉ የሳበኝ ግን በውስጧ ያለው ጥንካሬ እና ብርቱ የትግል መንፈስ ነው። ‹‹ዳኛ እና ዐቃቤ ሕግ ሆኜ ሰርቻለሁ›› አለችኝ በስሜት ተውጣ። ራሴን ላይና ታች በማወዛወዝ እያዳመጥኩ መሆኑን አረጋገጥኩላት። ቀጠለች ‹‹ነገር ግን እነዚህን ቀናት (ከተመረጠችበት ጊዜ በኋላ ያሉትን ነው) እንደኖርኩት አይነት ደስተኝነት ተሰምቶኝ አያውቅም።›› ንግግሯ በደስታ ሞላኝ። ኢትዮጵያውያን ወንዶች ብቻ ሳይሆኑ፣ ኢትዮጵያውያን ሴቶችም የለውጡ ፊት መሪ ሊሆኑ እንደተዘጋጁ እርግጠኛ ሆንኩ። …ብርቱካን እየተናገረች ነው። እኔም እየሰማሁ ነው ‹‹በየደረስኩበት የሚያገኘኝ ሰው ያበረታታኛል። ጣቱን እያሳየ ድጋፉን ይገልፅልኛል። ለዚህ ሕዝብ ዛሬ ብታሰርም አይቆጨኝም›› አለች ቀልብን በሚገዛ ድምፅ።
‹‹እታሰራለሁ ብለሽ ትሰጊያለሽ?›› እንደዋዛ የጠየኳት ጥያቄ ነው። ‹‹አዎን!›› ስትል በቀላሉ መለሰች፡ ፡ ግዙፉን ቦርሳዋን እየነካካችም ‹‹መቼ እንደምታሰር ባላውቀውም ዛሬ ብታሰርም ዝግጁ ለመሆን ሻርፕና ቀላል ልብሶችን በዚህ ቦርሳ ይዤ ነው የምንቀሳቀሰው›› አለችኝ መለስተኛ ሻንጣ የሚያክለውን የእጅ ቦርሳዋን መነካካቷን ሳታቋርጥ። ደነገጥኩ። ተገረምኩም። እንዴት አይነት ቁርጠኝነት ነው? ይህ አይነቱ ድፍረትስ ‹‹ተራራን ከማንቀጥቀጥ›› በምን ያንሳል? ለራሴ ያቀረብኩት ጥያቄ ነው።…እንዴት ደስ ይላል ለሀገር ወገንተኛ መሆን፤ ለህዝብ ማድላት!
የሆነ ሆኖ ኢህአዴግ እንደቀድሞ በቀላሉ የማያንበረክካቸው እና የማያስፈራራቸው መሪዎች እየተፈጠሩ እንደሆነ ገመትኩ። ከእነዚህ ውስጥ ብርቱካን ሚደቅሳ አንዷ ለመሆኗ ደግሞ እርግጠኛ ሆኛለሁ። ማን ነበር ‹‹እንስቷ ነብር›› ያላት? ብቻ እንጃ።
ከሶስት ዓመት በኋላ
…ብርቱካን ሚደቅሳን ጨምሮ ሁሉም የቅንጅት አመራሮች ታስረው በይቅርታ ተፈተዋል። ቴዲ አፍሮም
‹‹ሆ በል ክራር፣
ሆ በል ማሲንቆ
ስታይ ሰው ታርቆ…››
የሚል ነጠላ ዜማ ለቆ በየመዝናኛ ቦታው አዋቂዎችንም፣ ወጣቶችንም… ዕቅል አሳጥቶ እያዘለለ አስጨፍሯል። ይህ ከሆነ አንድ አመት በኋላ አንድ ነገር ተከሰተ። ‹‹በሶስት ቀን ውስጥ የብርቱካን ሚደቅሳ ይቅርታ ሊነሳ ነው›› የሚል ወሬ መላ ሀገሪቱን ናጣት። ‹‹ምክንያቱ ምንድር ነው?›› የሚሉ ጠያቄዎችም እልፍ አዕላፍት ሆኑ። በስዊድን ሀገር ለደጋፊዎቿ ‹‹(የቅንጅት አመራሮች) የተፈታነው በሕዝብ ጫና ነው ስላለች ነው›› የሚሉ ድምፆች በረከቱ። ብዙዎች ግራ ተጋቡ። ‹‹ታዲያ ይህ ምን ወንጀል ነው?›› ሲሉም ጠየቁ። ‹‹ኢህአዴግን አስኮረፈ!›› አሉ እናውቃለን የሚሉ። ፖለቲካ ገብቶናል ያሉ ደግሞ ‹‹መጀመሪያውኑም ሲፈቱ ይቅርታ የተደረገላቸው በቅድመ ሁኔታ ነው›› ሲሉ ተነተኑ።
በዚህ መሀል ያ ሶስት ቀን አለፈ። ብርቱካንም ‹‹ቃሌ›› ስትል በሰጠችው መግለጫ የጣሰችው ሕግ እንደሌለ፣ ጉዳዩ በይቅርታ እንዲያልቅ ሸምጋይ በነበሩት ሽማግሌዎች ስምምነት ከተፈጠረ ‹‹የፓርቲው መሪዎች ያለ ምንም ገደብ የፓርቲውን ስራ እንደሚቀጥሉ›› ጠቅላይ ሚንስትሩ ቃል መግባታቸውን መናገራቸውን ገልፃ፣ ማስተባበልም ካስፈለገ በሚል ስሜት ይመስለኛል ‹‹…በእርግጥም በዚህ ሰነድ ላይ እኔም እንደ አንድ ታሳሪ መፈረሜን ክጄ አላውቅም፡፡ በሽማግሌዎቹም የዕርቅ ማግባቢያ መንፈስ መሰረት በፖለቲካ የተቀሰቀሰውን ክስ ፖለቲካዊ ዕልባት ለመስጠት በማሰብ ለዕርቅ ስል ከሌሎች የፓርቲው መሪዎች ጋር ተስማምቼ ሰኔ 11 ቀን 1999 ዓ.ም በተጻፈው ሰነድ በሽማግሌዎች አማካኝነት መንግስትን እና የኢትዮጵያ ህዝብን ይቅርታ ጠይቄአለሁ፡፡ ብፈልግም ልለውጠው የማልችለው ሐቅ ነው፡፡›› ስትል በይቅርታ መፈታቷን እንዳልካደች ገለፀች። መንግስት ሆዬም ‹‹ቃሌ›› የሚለው የማስተባበያ ቃል በቂ አይደለም አለና አሰራት። አንዳንድ ታዛቢዎችም ‹‹የታሰረችው ቀጣዩ አመት ምርጫ ስላለ፣ ሊቀመንበር ተደርጋ የተመረጠችበት አንድነት ፓርቲ በምርጫው ለኢህአዴግ ከባድ ተገዳዳሪ ሊሆን ይችላል›› ተብሎ ስለተሰጋ ነው ሲሉ ፃፉ፤ እድል ባገኙት ሚዲያም አፅንኦት ሰጥተው ተናገሩ።
…ጠቅላይ ሚኒስትር መለስም ብርቱካንን ካልፈታችሁ ብለው ጫና ለመፍጠር የሚፈልጉ ዕርዳታ ሰጪ ሀገራት እንዳሉ በገደምዳሜ ከነገሩን በኋላ በዚህ ምክንያት ብርቱካንን እንደማይፈቱ አስረድተው ሲያበቁ ‹‹ከጣማቸው ይቀበሉ፤ ካልጣማቸው በሊማሊሞ ያቋርጡ›› የሚል ይዘት ያለው መልስ ሰጡ። ብርቱካንም ለዕድሜ ልክ እስራት አሰቃቂው ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ገባች። ይህን ጊዜም ብዙዎች ከይቅርታው ጀርባ አንዳች ጋኔን እንዳለ ጠረጠሩ፡፡ ጠርጥረው ሲያበቁም ህዝብ የሚያውቀው ‹‹ይቅርታ›› እና መንግስት የሚጠቀምበት ‹‹ይቅርታ›› በትርጉም ለየቅል እንደሆኑ ተረዱ፡፡
2003
ብርቱካን ሚደቅሳ ለድጋሚ እስር ከተዳረገችበት እስር ቤት፣ በድጋሚ ይቅርታ የተለቀቀችበት ዓመት ሆነ። በዚህ ይቅርታ ላይም ‹‹… አሮጊት እናቴን መርዳት ልጄን ማሳደግ ሲገባኝ፤ ዘላለማዊውን ኢህአዴግ ከስልጣኑ እንዲወርድ መሞከሬ እግዜርን የመቃወም ያህል ርኩሰት ነው›› አይነት ያለው ትርጓሜ ያዘለ ይቅርታ እንድትጠይቅ መገደዷን ሰማን፡፡ ዘግየት ብሎም መንፈሰ ፅኑዋ ብርቱካን ሚደቅሳ የአዲሱ የፖለቲካ ስልት ‹‹ሰለባ›› እንደሆነች ገባን።
2004
…የአውራምባው ዳዊት ከበደ፣ በ1999 ዓ.ም መጨረሻ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት በይቅርታ ተፈቶ ሲያበቃ ‹‹አውራምባ ታይምስ›› የሚባል ጋዜጣ መስርቶ የመንግሥትን ገመና የሚገልጡ የተለያዩ ፅሁፎችን ማተም ጀመረ። ሀገሪቱ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ታመራ ዘንድም የቻለውን ያህል አስተዋፅኦ አበረከተ። አድሎአዊ አስተዳደርን፣ የተዛቡ ፍትሆችን፣ የመብት ረገጣዎችን… ተቃወመ-በብዕሩ። ይህንን አበርክቶት ከግምት ያስገባው ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ድርጅትም (CPJ) ‹‹የ2011 ዓለም አቀፍ ተሸላሚ›› አድርጎ መረጠው። …ይህ ከሆነ ከወራት በኋላም ዳዊት ከበደ ‹‹(ያ የፈረደበት) ይቅርታ ሊነሳብኝ እንደሆነ አስተማማኝ መረጃ አገኘሁ›› ብሎ ከሀገር ተሰደደ። ሌላ ‹‹ሰለባ››ም ይሏችኋል ይህ ነው፣ ሌላ አይደለም፡፡ …እነሆም ማሰር፣ ከአሰሩ በኋላ በይቅርታ መልቀቅ፤ ከለቀቁ በኋላ ደግሞ ይቅርታን አንስቶ መልሶ ማሰር የሚባል ‹‹ፖለቲካ›› ስራ ላይ ከዋለ ድፍን አምስት አመት ሞላው። ይህ አይነቱ ፖለቲካም ውሎ አድሮ ‹‹የሚያከስር›› ወይም ‹‹የሚያተርፍ›› ተወራራጅ ሒሳብ ያለው የገዥው ፓርቲ ‹‹ተቀማጭ›› ሆነ፡፡ አንዳንዶችም ‹‹በይቅርታ ተቀባዩ አንገት ላይ ተንጠልጥሎ ቀሪ ዘመንን በሞላ ‹ኪል፣ ኪል…› የሚል ‹ቃጭል› ነው›› ሲሉ ምክንያታዊ ትንታኔ አቀረቡ፡ ፡ …እኛም በቀጣዩ አንቀጽ የይቅርታ ይህ መግላሊቷን አጀንዳ አድርገን እንያት፡፡
የፖለቲካው መንፈስ
የዚህ ትውልድ ፖለቲካ አንድምታ፣ ከያ ትውልድ የፖለቲካ አንድምታ እንደወረደ የተተገበረ ነው፡፡ በመጠፋፋት ሳጋ እና ማገር የቆመ ማለቴ ነው፡፡ ሀቅ ነው! ያ ትውልድ ከፍ ሲል በርዕዮት አለም ልዩነት እርስ በእርሱ ተጠፋፍቷል፡፡ ዝቅ ሲልም ‹‹በቃላት አጠቃቀም›› ተገዳድሏል፡፡ ለምሳሌ አንዱ ‹‹ወዛደር›› ሲል ሌላኛው ‹‹ላብአደር ነው የሚባለው›› ብሎ ጦርነት ሲያውጅበት አይተናል፡፡ ‹‹ኢህአፓ›› የተሰኘው ነውጠኛ ድርጅት ‹‹እናቸንፋለን!›› ሲል በመፈከሩ ብቻ፣ መኢሶን የተባለ ሌላ ነውጠኛ ‹‹አብዮተኛ ‹እናሸንፋለን!› እንጂ ‹እናቸንፋለን› አይልም›› ሲል በፈጠረው የሆሄያት ልዩነት ወደጎዳና ላይ መገዳደል መሸጋገራቸው የትላንት ታሪክ ነው። በነገራችን ላይ የኢህአዴግ መሪዎችም እንደ ታሪክ ተጋሪዎቻቸው በዛ ዘመን መንፈስ የተቀኙ ናቸው። መፍትሄያቸውም እንደዚያው ዘመን ነው፤ ‹‹ወይ ከኛ ጎን ቁም፤ አሊያም ጥፋ!›› ለዚህም ነው እግዜሩ ‹‹ኑ እንውረድ ሰውን በምሳሌያችን እንፍጠር›› እንዳለው በራሳቸው (በኢህአዴግ) አምሳያ የተፈጠሩ ማህበራትን እንደእንጉዳይ ያፈሉት፡፡ የኦሪቱ ቃልንም በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ቀይረው እንዲህ ያሉት ‹‹ኑ እንታገል ኢትዮጵያውያንንም፣ ኢትዮጵያንም በምሳሌያችን እንፍጠር››፤ እነሆም ቃሉን የሰሙ፣ ሰምተውም በልባቸው ያሳደሩ ‹‹የሰራተኛ ማህበር፣ የመምህራን ማህበር፣ የሀኪሞች ማህበር፣ የጋዜጠኞች ማህበር፣ የነጋዴዎች ማህበር፣ የአርቲስቶች ማህበር፣ የሸማቾች ማህበር…›› ተፈጠሩ፡፡ ለዚህም መሰለኝ የዛሬ ሃምሳ አመት የነበረው ‹‹የዲሞክራሲ›› እና ‹‹የሰብአዊ መብት›› ጥያቄ ዛሬም ዋነኛ አጀንዳ ሆኖ ሀገሬን ያሉ እየታገሉለት ያለው። በጥያቄው ላይ ያለው ልዩነት ‹‹የአፄ ኃይለ ሥላሴ የብዝበዛ አገዛዝ…›› የሚለው ‹‹የአቶ መለስ ዜናዊ አምባገነናዊ አስተዳደር…›› በሚል መተካቱ ብቻ ነው። ከዚህ ባሻገር የማይካደው ልዩነት ይህ ትውልድ እንደ ‹‹ያ ትውልድ›› በፖለቲካ ልዩነት አውሮፕላን አይጠልፍም፤ ለሃሳብ ተቃርኖም ነፍጥ አያነሳም። ይህ ማለት ግን ስርዓቱ ተቀናቃኙን በትውልዱ የትግል ስልት እየገጠመው ነው ማለት አይደለም። እንዲህማ ልንል አንችልም። ምክንያቱም ከ‹‹ቀይ ሽብር›› ማፋፋም አንስቶ ‹‹አሸባሪ›› ብሎ በፍርድ ቤት ወንጅሎ ቃሊቲ እስከ ማውረድ የሚደርሱ መንግሥታዊ ምላሾችን እያየን ነውና።
እዚህ ጋ መነሳት ያለበት ቁም ነገር አለ፡፡ ይኸውም ተቀናቃኝ ወይም ተቃዋሚ ላይ የአፄው መንግሥት የተሻለ ርህራሄ እንደነበረው ነው፡፡ አፄው ግዙፍ ተቃውሞዎችን ሳይቀር ለረጅም ጊዜ ታግሰው አልፈዋል፡፡ አንዳንዴም በ‹‹አስለቃሽ ጢስ››፤ አልፎ አልፎም ‹‹ዱላ›› ብቻ በያዘ ፖሊስ ችግሩን ለመፍታት ይሞክሩ ነበር። በአፄው ላይ ተማሪዎችን እና ሠራተኞችን ካነሳሱት ውስጥ አንዱ የሆነው የመላው ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን) መስራች እና ዋና ፀሀፊ የነበሩት አንዳርጋቸው አሰግድ ‹‹በአጭር የተቀጨ ረጅም ጉዞ›› በሚል ርዕስ በፃፉት መጻሕፍ ላይ፡-
‹‹በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን ‹ምኅረት፣ ግዞት፣ የቁም እስር፣ አምባሳደርነት ሾሞ መላክ፣ ከሹመት አግልሎ ማቆየት…› የፖለቲካ ተቃዋሚዎች አያያዝ መንገዶች ነበሩ። እርሳቸውን የተኩት ሁለቱ መንግሥቶች ወሬውንም የሰሙ አይመስሉም፡ ፡ ብቻ ደግሞ ‹ምኅረት…ወዘተ› የመንግሥት ጥንካሬ ምልክት ተደርጎ መታየት የለበትም፡፡ የሚያመላክተው ተቃራኒውን ነው። ሆኖም ግን እንደዚያ ያለው መንግሥት ከገዳይና በእስር ከሚያበሰብስ መንግሥት ይሻላል›› ሲሉ የሰጡት ምስክርነት አንድ ማሳያ ሊሆን ይችላል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ፕሮፌሰር አንድሪያስ እሸቴም ባለፈው ቅዳሜ ከሸገር ራዲዮ ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ ላይ ‹‹አፄ ኃይለሥላሴ ተቃዋሚዎቻቸውን ልጆቼ ናቸው ብለው ያስቡ ነበር›› ያሉት ሌላ ማረጋገጫ ሊሆን ይችላል። በእርግጥ አንዳርጋቸው አሰግድ ‹‹ሁለቱ መንግስታቶች ወሬውንም የሰሙ አይመስሉም›› ሲሉን፤ ወሬውን የሚያውቁት አንድሪያስ እሸቴ ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ሆነው እያለ ‹‹ተቃዋሚዎችን እንደ ልጆችህ ተመልከት›› ብለው አለመምከራቸው በፕሮፌሰሩ ላይ ያለውን ምፀት ይበልጥ ያጎላዋል። የኩነናው ባለድርሻም ያደርጋቸዋል፡፡
ይቅርታ ወይስ…
በ1996 ዓ.ም ወርሃ ሚያዚያ የወጣው ‹‹ነጋሪት ጋዜጣ›› የይቅርታን አዋጅ የሚመለከት እንደሆነ ይገልፃል፡፡ ነገር ግን አዋጁ በክፍል 3፣ አንቀጽ 16 ላይ ‹‹የይቅርታ ዓላማ የህዝብን ደህንነትና ጥቅም ማስከበር ነው›› ከማለቱ ውጭ ስለይቅርታ ምንም አይነት ማብራሪያ የለውም፡፡ የሚያተኩረውም በይቅርታ አቀራረብ ሥርዓት ላይ ነው፡፡
ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ በሚወጡ አዋጆች ላይ ካሉ መሠረታዊ ችግሮች አንዱ ይህ ነው። ያልተብራሩ ወይም ግልፅ ያልሆኑ ሀሳቦችን አጭቆ ማቅረብ፡፡ ይህ ደግሞ ለትርጉም አሻሚ ይሆንና ብዙ ክፍተት ይፈጥራል። በይቅርታ አዋጁ ላይም ‹‹ይቅርታ›› ማለት ምን ማለት እንደሆነ አልተገለፀም፡ ፡ ወይም ይቅርታ የተደረገለት ሰው ሊነፈግ ስለሚችለው መብት አልተዘረዘረም። ለዚህም ነው በኢትዮጵያ በተለይም ከፖለቲካ ጋር በተያያዘ ታስረው በይቅርታ የሚፈቱ ዜጐች፣ የተሰጣቸው ይቅርታ ሙሉ ነፃነትን የሚያጎናፅፍ ሳይሆን፣ በተንቀሳቀሱ ቁጥር ‹‹ኪል፣ ኪል…›› እያለ ‹‹ቀይ መስመር›› መኖሩን የሚያስታውስ ባንገት የሚጠለቅ አስደንባሪ ‹‹ቃጭል›› እንዲሆን ያደረገው። ልክ በምርጫ 2002 ዕለት ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው ‹‹ምርጫው እየተጭበረበረ›› ለመሆኑ ማስረጃ እንደደረሳቸው ተናግረው ሳይጨርሱ፣ በምርጫ 97 ማግስት የተጠለቀላቸው ‹‹ቃጭል›› መደወሉን ተከትሎ በኢቲቪ ያስተባበሉት አይነት ማለት ነው፡፡ አዲሱ ምህዳር ማጥበቢያ- የይቅርታ ፖለቲካ ማለትም ይህ ነው፣ ሌላ አይደለም፡፡
ይቅርታ ማለት ምንድር ነው?
የ‹‹ከሳቴ ብርሃን ተሠማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት›› ይቅርታ ለሚለው ቃል አቻ ትርጉም ‹‹አንድ ነገር ሲሳት ወይም በንግግር ማኻል አንድ ነገርን ጣልቃ ከተደረገ በኋላ ለማድረግ ይቅርታ ማለት ነው›› ይላል።›› መቼም ለዕድሜ ልክ ፍርደኞች የተሰጠው ይቅርታ በዚህ የሚገለፅ ነው ባንልም ‹‹ይቅርታ›› የምትለዋን ቃል ግን ትንሽ ሰፋ ያደርጋታል። ምክንያቱም በሀገራችን ይቅርታ በገዥዎችም፣ በተገዥዎችም መካከል የነበረ እና ሀገሪቷን ከመፈራረስ አግዶ ያቆየ ባህል ነው፡፡
እናም ‹‹ይቅርታ›› እንዲህ በአዳዲስ ብልቶች ተከፋፍሎ ትርጉሙ ከመየቀሩ በፊት የቆየ ባህል ነበር። ይህ አንድ እውነት ነው፡፡ ኢህአዴግን መደገፍ መብት የሆነውን ያህል፣ አምባገነንነቱንና ሙሰኛነቱን መቃወም መብት መሆኑ ደግሞ ሌላ እውነት ነው፡ ፡ ስለዚህም ገና ለገና ‹‹የአይናቸው ቀለም አላማረኝም›› እየተባለ አንዱን ‹‹ሽብርተኛ›› ሌላውን ‹‹ተላላኪ›› እያሉ ወንጅለውና ፈርደው ሲያበቁ ‹‹ይቅርታ›› በሚባል እጥን አጥኖ ማንነትንም ሆነ ሞራልን ማምከን፤ ቀን ከሌሊት እንቅልፍ አሳጥቶ የሚያሳድረውን ያንን ‹‹የቁጣ ቀን›› መምጫ ዕድሜ ከማሳጠር ባለፈ ጠቀሜታ የለውም። በይቅርታ የሚለቀቅ እስረኛም በገደብ እንደተለቀቀ ተደርጎ ‹‹ይቅርታህ ሊነሳ ነው›› የሚለው ጨዋታም አትራፊ አይደለም፡ ፡ ምንአልባት አገሪቱም ፖለቲካውም የኢህአዴግ ነው ወደሚል ግልፅ አምባገነንት ካልተሄደ ማለቴ ነው።
የሆነ ሆኖ በኢትዮጵያ አብዮታዊ ዴሞክራሲን ‹‹እንደግል አዳኝ›› አድርጎ ለመቀበል አይነተኛ መፍትሄ ሆኖ እየወጣ ያለው ተቃዋሚዎችን እና ነፃ ጋዜጠኞችን ማሰር፤ ከአሰሩ በኋላ ደግሞ ፍርድ ቤት ማመላለስ፣ ማመላለስ፣ ማመላለስ… ዳኛ መሣይ፣ ዐቃቤ ሕግ መሣይ፣ ምስክር መሳይ፣ ማስረጃ መሳይ… ብዙ መሣይ ነገሮችን ማዘጋጀት። በመጨረሻም እድሜ ልክ ወይም አስራአምስት እና ሃያ ዓመት እስር መፍረድ፡፡ ከፍርዱ በኋላም ‹‹የይቅርታ ጠይቅ›› ግፊትን እንደደራሽ ውሃ በር ተቆልፎበት በተዳከመ እስረኛ ላይ መልቀቅ፡፡ አስከትሎም በግፊቱ ለወደቀው አዲሱን ማህተም (ቃጭል) በአንገት አስጠልቆ ቀሪ ዘመንን ለሀገሩ እንግዳ፣ ለሰዉ ባዳ ማድረግና ከሁለት አማራጭ ጋር ፊት ለፊት ማላተም። የመጀመሪያውም አማራጭ ሀገር ለቆ መሠደድ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ኢህአዴግ ሲዘፍን እስክስታ እያስወረዱ አጃቢ አድርጎ ማስቀመጥ ይሆናል ማለት ነው።
በአናቱም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል በፅንፈኝነት የሚናወዝ፣ አቻቻይ ለሆነ አማካይ መንገድ ትዕግስት የሌለው እንደሆነ ይታወቃል። ፖለቲካዊው ስነ-ልቦና ስርዓቱን የሚቃወሙ ዜጐች በታላቅ መከራ ውስጥ ቢያልፍም በገዢው ቡድን ተገደው እንኳን የሚስማሙባቸውን ጭብጦች ለመረዳት ዕድል አይሰጥም። የተቃወሙትን ይቅርታ መጠየቅ የተንበርካኪነት ተመሳስሎ ተደርጎ ይወሰዳል። ኢህአዴግ ይህን በሚገባ የተረዳ የሚያስመስለው፣ በግፍ ያሰራቸውን ዜጐች በተለያዩ መንገዶች አንገታቸውን እንዲሰብሩ ካደረገ በኋላ በይቅርታ እንዲፈቱ ማስገደዱ ነው። በይቅርታው የሚወጡት ፖለቲከኞችም የደጋፊዎቻቸው መሰረት እንደሚላላ ኢህአዴግ በሚገባ የተረዳው ይመስላል። ፓርቲው ራሱ በብክለቱ ውስጥ የተሳተፈበትን የፖለቲካ ተለምዶት በዚህ መልክ ሊያተርፍበት እንደሞከረ ከላይ የቀረቡት ትርክቶች በበቂ የሚያሳዩም ይመስለኛል፡፡
መቼም ኢህአዴግ በዚህ አያያዙ እስር ቤት ባሉ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች፣ እንዲሁም እንደ ሰሞኑ ወሬ ከሆነ ደግሞ የ‹‹ቃጭል›› ማህተም የሚያስሩ ወይም እንዲያስሩ አስገዳጅ አማራጭ የሚቀርብላቸው ዜጐች ቁጥር ከኢኮኖሚ ‹‹እድገቱ›› በላይ መናሩ አይቀሬ ነው። ሁኔታውን አንዳንዴ ሳስበው፣ ሳስበው አቶ መለስ ፓርቲያቸው ለ40 እና 50 ዓመት በስልጣን ላይ እንዲቆይ እየሰሩ ያሉት ሠርክ እንደሚነግሩን ‹‹ልማታዊ መንግሥት›› ሆነው ሳይሆን ‹‹ተቺዎቻቸው››ን እና ‹‹ተቀናቃኞቻቸው››ን በሙሉ እያሰሩ፣ በይቅርታ እየፈቱ ቃጭል አንጠልጥለውባቸው በማሸማቀቅ ይመስለኛል።
የሆነ ሆኖ ከዚህ በኋላ የሚኖረው ትግል ‹‹ቃጭል›› በማሰር እና ‹‹ቃጭል›› አላስርም በሚሉ የነፃነት ፍናወጊዎች መካከል መሆኑ አይቀሬ ነው። ጎበዟ ርዕዮት አለሙ ከቃጭሉ ይልቅ ‹‹ይግባኙን›› መርጣለች። ምንአልባት ‹‹እምቢይ ባይነት›› እየመጣ ለመሆኑ ይሄ አንድ ምልክት ሊሆን ይችላል። ሌሎችም አሉ ‹‹ኪል፣ ኪል፣ ኪል…›› የሚል የቃጭል ድምፅን መስማት የማይፈልጉ፡ ፡ …ብርቱዎቹ እየመጡ ይሆን? ማን ነበር ‹‹ቆንጆዎቹ ገና አልተወለዱም›› ያለው?
ከእንዲህ አይነቱም ‹‹ብቅል›› እና ‹‹ጌሾ›› የሚዘጋጅ ፅዋ ‹‹አውዳሚነት›› በሚጎነጨው ብቻ የሚገደብ ነው ማለቱ ከታሪክ አለመማር ነው፡፡ አፄውን የበላው የወጣቶች ጎርፍ ነው፡፡ ደርጉንም ያንኮታኮተው ‹‹ወታደራዊ ሳይንስ የማያውቁ›› ተብለው ሲተቹ የነበሩ ተማሪዎች እና አርሶ አደሮች ናቸው፡፡ መቼም ከዚህ በላይ ይግባኝ የሌለው የታሪክ ብያኔ የትም የለም፡፡ ለዚህም ነው ጋዜጠኞቻችን ‹‹ዜና መዋዕል›› ከመፃፍ ወይም ከማይታይና ከማይዳሰሰው ‹‹ልማት›› የተጣባ ዜናቸው ባለፈ ሀገራዊ ጥቅምን ያቀነቅኑ ዘንድ ግድ የሚላቸው።
መቼም ለሀገራዊ ጥቅም እቆማለሁ ተብሎም፣ መስዋዕትነትም ተሸሽቶ የሚሆን ነገር አይደለም። በተቀረ ከይቅርታው ደብዳቤ ጀርባ በደን እንደተዋጠ ተራራ የተደበቀ አንዳች እንቆቅልሽ ለመኖሩ ግልፅ ነው። ሆኖም ዛሬ ይህ እንቆቅልሽ እንዲፈታልን አንጠይቅም። ነገ ግን ሌላ ቀን ነው። ምናልባትም ነገሩ ሁሉ ‹‹የነጋበት ጅብ ታሪክ››ን መልሶ ሊያመጣ ይችልም ይሆናል፡ ፡ ማን ያውቃል? ድሮ ድሮ በያ ትውልድ የትግል ዘመን፣ ትግላችን በሚባለው መጽሔት ላይ እንዲህ የሚል ግጥም ሠፍሮ ነበር።
‹‹ጐበዝ ዝም አትበሉ
ዝምታ ለበግም አልበጃት
አስራ ሁለት ሆና አንድ ነብር ፈጃት።››
ይህም እምቢይ ባዮች እልፍ እየሆኑ መሄዳቸው አይቀሬ ለመሆኑ ምሳሌ ነው፡፡ እውነትም ነው፡፡ መኢሶኖች ‹‹የየካቲቱ ገጣሚ›› እያሉ የሚንቆለጳጰሱት ያ ምርጡ ገጣሚ ዮሐንስ አድማሱ ያለውም፡-
‹‹አሉ ቁጢጥ ቁጢጥ፣
በሰማይ ደመና
ከእንግዲህ ቀረች
እንቅልፍና ጤና
መንግስት ብረት እንጂ አይገዛም ልቦና››ም እንዲሁ እውነት ነው፡፡ ...ቀጣዩን የከርሞ ሰው ካለን የምናየው ይሆናል።

Comments
Zman (not verified)
Sun, 07/08/2012 - 23:16
Permalink
ተመስገን ....
በሶስት ነገሮች እርገጠኛ ነኝ .... በዚህ ዘመን እውነተኛ የነጻነት ብርሃን ስለመሆንህ : እልፍ አእላፍ ተተኪወች ከኋላህ ስለመሰለፋችን : ወያኔወችም እንደማይተኙልህ ::ሁልጊዜም ያንተን ጽሁፍ ካነበብኩ በኋላ ፈጣሪን አመሰግነዋለሁ ... ተመስገን !
Ethiopia (not verified)
Mon, 07/09/2012 - 10:34
Permalink
Let's unit
Wake up stand up stand up 4 ur right
wogayehu (not verified)
Mon, 07/09/2012 - 10:49
Permalink
To all Ethiopian please this
To all Ethiopian please this message keep it at the bottom of your heart.
long live for the Editor.
i have a dream (not verified)
Mon, 07/09/2012 - 11:23
Permalink
teme yezemenu jegena neh
teme yezemenu jegena neh betam enakeberehalen
runescape money (not verified)
Mon, 07/09/2012 - 17:47
Permalink
You have a nice blog!
Hi, My name is Daniel Berman and I am a TV series creator, producer/director, DP, editor, photographer and founder of the Mobile Photo Awards.
Enjoy reading your post! Keep on doing good!
cheapest runescape accounts
washeraw (not verified)
Mon, 07/09/2012 - 18:58
Permalink
YIQRTA
I hear you saying "dictatorship will take us all to the abyss. Please think about the future our generations." Is there a more direct way of transmitting this message? I don't think so.
Thank you Temesgen.
Maco (not verified)
Mon, 07/09/2012 - 21:05
Permalink
Alen....
Alen ke gonachew nen,,,
Debebe (not verified)
Tue, 07/10/2012 - 14:23
Permalink
Wasting time
Don't you think you are over focused on Meles? The people of Ethiopia as a whole are corrupt who love their tribe and money more than Ethiopia. So everyone needs to look at themselves? I think there is selfish virus in the country- no elite part of society who will die for the truth and honest - all running after money.
Anonymous (not verified)
Tue, 07/10/2012 - 15:05
Permalink
The center of fabrication
The center of fabrication Fitih and the expert of fabrication Temesgen! Both think the country accourding their intrest! This should get its end! The solder of derg was kill b/s of his bad poletical intrest. so u should be in prison at least at most...!
እድሜ (not verified)
Wed, 07/11/2012 - 04:30
Permalink
የአምላክ ክንድ ይጠብቅህ ተሜ ጀግናው-እኛም አለን ከጎንህ!
ተሜ አንበሳው! ሰላም ሰነበትክልን ጀግናው!
the center of fabrication: ተሜን በመቃወም የሚተፉ "ግርዝ ጭንቅላቶች" ናቸው።! ደም ፍላታም መንደርተኞች ናቸው-ሳር ቅጠሉ ያውቃቸዋል።።
solo (not verified)
Tue, 07/10/2012 - 19:53
Permalink
ewneten anfera
አገሪቱም ፖለቲካውም የኢህአዴግ ነው ወደሚል ግልፅ አምባገነንት ካልተሄደ ማለቴ ነው።ena kezam alfe ehadalehu EPRDF yemibal neger yelem hulun yeyazew tplf new:: yan demo hulum yakal
Anonymous (not verified)
Tue, 07/10/2012 - 19:56
Permalink
JEGNA(U R MY HERO)
Jegnan endet belo meglets yechal yehon?yehe yene yehul geze tiyakeye new. yeferhatin kaba gefo yetalelin lemenorih wastina belelh gizena huneta(woyane lerasu yamechachewun) yelebachinin meshat yegebaw gebtotin yedefere jegna etiopiawi new lene!! geta yehenin ayeta kehagerih hizb wuleta yemisefrlih ansitoh amogesoh Jegnaye belo yemiyasbih gize yemita. U r my hero.....
zee (not verified)
Wed, 07/11/2012 - 06:00
Permalink
May the good God protect you
It is too much to handle for weyane. May the good God protect you & our beloved country.You are in my prayer. You and Teddy afro are impressed me beyond and above my imagination.Thank you again
tb (not verified)
Fri, 07/13/2012 - 05:24
Permalink
yesew edmiew sint new?yemeleses?
Sew mechem hulem bezih mider lay yeminorebet gize acher mehonun kaweke esu tilek sew new bene edmie tadiya bezich beacher edmew lesewoch melikam serto ayemerow selam endiyagegn kemadereg yilik sewen selam asatito rasunim selam nesto menorin lemin yimertal "ye yikirtam debdabie"yibelew sew hulu ewenet bimeselew ena biyaminew enkuan weshet mehonun gin rasun liwash ayechilim tadiya sew lemin rasun edme likun eyewashe yinoral...mot layeker becha enkwanim yesewoch edmie achir hone ye achiru seweyeachinim chimir...Egzier weshetamochun hulu yimarilen!!!!temesgen berta ye ethiopia amilak yitebikih!!!
`Tesfaye (not verified)
Fri, 07/13/2012 - 20:48
Permalink
What a woderful message!!!!!
Temesgen!!!
First, let me take this opportunity to express my profound admiration for you and extraordinary determination fighting against this stupid, recist and selfish woyane government.
You are really making history, no doubt about it. We are really …really …really proud of you!!!!!!
Your a real son of Ethiopia!!!
dagawi (not verified)
Fri, 07/13/2012 - 21:29
Permalink
you are the great man.
you are the great man.
beljig (not verified)
Sun, 07/15/2012 - 13:10
Permalink
ቆንጆዋን ልጅ በተሰበረ መነጽር
ቆንጆዋን ልጅ በተሰበረ መነጽር
በልጅግ ዓሊ
በተከታታይ ተመስገን ደሳለኝ በፍትህ ጋዜጣ ላይ የሚያቀርባቸውን ጽሁፎች አነባለሁ። በብዙዎቹ ብስማማም በመሃል ጣልቃ በሚያስገባቸው አንዳንድ ትንታኔዎች ላይ አልስማማም። አለመስማማትም ሳይሆን መታረም አለባቸው የሚል እምነት አለኝ።
ተመስገን <<የኔ ትውልድ>> የሚለውና <<ያ ትውልድ>> የሚለው ነገር አለው። ከብዙ ጽሁፎቹ እንደምንረዳው “የእሱ ትውልድ” ከቀይ ሽብር በኋላ የተፈጠረው ሲሆን፣ “ያ ትውልድ” የሚለው ደግሞ ከቀይ ሽብር በፊት ያለው ይመስላል። ብዙውን ትንታኔው የሚያተኩረው “ያ ትውልድ” ሞኝ፣ ለማይረባ ነገር መስዋትነት የከፈለ፣ ቅራኔዎችን በሚገባ ባለማያዙ የተጋደለ አስመስሎ ያቀርብና . . . የእሱ ትውልድ ግን “አርቆ አሳቢ ፣ በእንቶ ፈንቶ የማይጣላ፣ ቅራኔን በበሰለ ሁኔታ የሚመለከት” አድርጎ ለመሳል ይሞክራል። ይህ የእሱ ትንተና ከእሱ ጽሁፍነት አልፎ እውነት ቢሆን በጣም አስደሳች ነበር። እውነቱ ግን ሌላ ነው።
የተመስገን ትውልድ በአብዛኛው በእኔ ትንታኔ <<የድጋፍ ወረቀት ሠራዊት>>ነው ። ይህ ደግሞ ካለ ምክንያት አይደለም። በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ትግል የግል ጥቅም ከፖለቲካ መድረክ ላይ ማጋበስ የተጀመረውም ከቀይ ሽብር በኋላ ሆኖ እናገኘዋለን። ቀይ ሽብር በኅብረተስብ ውስጥ የፈጠረው ፍርሃት ዜጎች የፖለቲካ ጥያቄ ቢያነሱ ሊደርስባቸው የሚችለው አሰቃቂ ሥቃይ በእውን እንዲያዩት ስለተደረገ ሃገርን ከሚመለከት ማናቸውም ጉዳይ መራቅን የመርጠ ትውልድ ነው። ይህንንም አያይዞ ለግል ጥቅም መሮጥ በሰፊው ተጀመረ። ከቀይ ሽብር በኋላ ለሃገር መሞት ማስከበሩ ቀርቶ፣ የድህንነት ሠራተኛ፣ የአየር በአየር ነጋዴ፣ “የሕዝባዊ ድርጅቶች” (የአኢወማ፣ አኢሴማ ፣ መኢሠማ . . .ወዘተ) መሪ ሆኖ መመረጥ ወይም መሳተፍ ጥቅም እንዳለው እየታወቀ መጣ።
በዚህም ምክንያት አብዮታዊ አስተዋፆ የሥራ፣ የትምህርት(በሃገርም ይሁን በውጭ )፣ አልፎም ተርፎ ሕይወትን ለማሰንበት አስፈላጊ ሆነ። አብዮታዊ አስተዋፆ የማይጠየቅበት ቦታ ቢኖር ብሔራዊ ውትድርና ነበር። ለዚህም ነው በዘመኑ የነበሩ ወጣቶች ለጦላይ (ብሔራዊ ወታደር ማሰልጠኛ ጣብያ ) የድጋፍ ወረቀት አያስፈልግም ብለው የተሳለቁት። ለሃገር፣ ለሕዝብ፣ ለዴሞክራሲ መሞት የተዋረደውና ለግል ጥቅም መሮጥ በሰፊው የተጀመረው ያኔ ነው።
ይህ “የድጋፍ ወረቀት ሠራዊት” በደርግ አብዮቱ ውስጥ የሚያደርገው ተሳትፎ እየታየ የሚያገኘውን ጥቅም ከሃገር ፍቅር ይበልጥ ሲያሳድድ የነበረ ነው። አልፎ ተርፎ ንቅዘቱ በሠራዊቱ ውስጥ ሳይቀር በጉልህ ይታይ ነበር። ታላላቅ የጦር መኮንኖች በተራ አለብላቢ ካድሬዎች ይታዘዙ እንደነበር የሚረሳም አይደለም። ከዛም አልፎ የሃገሪቷን ጥቅም በገንዘብ የለወጡ ስንት ናቸው? ታሪክ ይፍረደው!
ከዚህ የግል ጥቅም ሩጫ ጋር ለሃገሩ የተስውትን ጅግኖች ማዋረድ በደርግ እንደ አብዮተኝነት ሲያስቆጥር በሌላ በኩል ደግሞ ለግል የሞራል ማካካሻ፣ በሃገር ላይ የሚደረገውን ክህደት ማሳመኛ ሆኖ ማገልገል የጀመረው ከቀይ ሽብር በኋላም ቢሆን እስከ አሁን በሰፊው እንደቀጠለ ይገኛል። ለዚህ ነው የዘንድሮ ፖለቲከኛ በአንድ ወገኑ ኢንቨስትር በሌላው የተቃዋሚ ድርጅት መሪ ሆኖ የምናገኘው። አስረጅ የምጠየቅ አይመስለኝም። <<ሞኝ ያለቀው በቀይ ሽብር>> በሚል መፈክር ላይ ተነስቶ የዛን ትውልድ ያበረከተውን ከፍተኛ አስተዋፆ ማጣጣል የተጀመረው በደርግ ወቅት ቢሆንም አሁንም በሰፊው እንደቀጠለ ይገኛል። ለዚህ ደግሞ በቂ ምክንያት አለው።
በዚህ ወቅት በአብዮታዊ ተሳትፎ ጥቅም ያጋባሱ ግለሰቦች ከቀይ ሽብር ማግስት ያ ቆራጥ ትውልድ ያለቀው አልቆ የተረፈው በእሥር ተንገላቶ፣ ሞራሉ በቀይ ሽብር ተጎድቶ፣ እንዳይሰራ፣ እንዳይማር ያጠቆርከው የአብዮት ሸማ እጠብ እየተባለ የድጋፍ ወረቀት ተክልክሎ በነበረበት ወቅት አብዮታዊነታቸውን በማሳየት ጥቅም ያገኙ ግለሰቦች፣ በተሰጣቸው ሰፊ የትምህርት እድል በመጠቀም ዛሬ ምሁራን እየተባሉ ይገኛሉ። እነዚህ ግለሰቦችም ይህንን <<ሞኝ ያለቀው በቀይ ሽብር>> የሚለውን መፈክራቸውን ለመሸጥ በሚያደርጉት ጥረት የዛን ትውልድ የዴሞክራሲ ትግል ወደ ታች በማውረድ የቃላት ጦርነት እንደነበር ሲያስረዱ ይታያሉ። ሌሎችም ይህንን የተሳሳተ አመለካከት ይዘው ያስተጋቡ። ሃቁ ይህ አይደለም ሊላቸው የሚችለው ትውልድ ግማሹም ከመቃብር በታች ነው። ሌላውም በሃገር ውስጥ ስደት የድጎማ መምህር ሆኖ ቀርቷል። የተረፈው ደግሞ ከድርጅት ድርጅት እየቀያየረ ያንን ትውልድ መስደብ የፖለቲካ አዋቂነት መጀመሪያ አድርጎ ሲመጻደቅ ይታያል።
እውን ያ ትውልድ የተሰዋው በቃላት ልዩነት ነበር?
ተመስገን “‹‹ይቅርታ›› የኢህአዴግ ቃጭል? ወይስ…” በሚለው ጽሁፉ ውስጥ
“ የዚህ ትውልድ ፖለቲካ አንድምታ፣ ከያ ትውልድ የፖለቲካ አንድምታ እንደወረደ የተተገበረ ነው፡፡ በመጠፋፋት ሳጋ እና ማገር የቆመ ማለቴ ነው፡፡ ሀቅ ነው! ያ ትውልድ ከፍ ሲል በርዕዮት አለም ልዩነት እርስ በእርሱ ተጠፋፍቷል፡፡ ዝቅ ሲልም ‹‹በቃላት አጠቃቀም›› ተገዳድሏል፡፡ ለምሳሌ አንዱ ‹‹ወዛደር›› ሲል ሌላኛው ‹‹ላብአደር ነው የሚባለው›› ብሎ ጦርነት ሲያውጅበት አይተናል፡፡ ‹‹ኢህአፓ›› የተሰኘው ነውጠኛ ድርጅት ‹‹እናቸንፋለን!›› ሲል በመፈከሩ ብቻ፣ መኢሶን የተባለ ሌላ ነውጠኛ ‹‹አብዮተኛ ‹እናሸንፋለን!› እንጂ ‹እናቸንፋለን› አይልም›› ሲል በፈጠረው የሆሄያት ልዩነት ወደጎዳና ላይ መገዳደል መሸጋገራቸው የትላንት ታሪክ ነው።”
ዛሬ ተመስገን በ”ላ” በ “ቸ” ፊደሎች ተላለቁ ብሎ የሚሳለሰቅባቸው ወጣቶች የተሰውበትን ራዕይ በዘንድሮ የነጻ ገበያ ፖለቲካ አንጻር( የግል ጥቅም የለውምና) ለማይረባ ነገር የተደረገ መስዋዕትነት ተብሎ ሊታይ ይችላል። ውስጡ ለነበሩት ግን ምን ያህል ከግል ጥቅም በላይ የሃገር ፍቅር ጎልቶ ይታይ እንደነበር እውነትና ታሪክ ይመሰክራሉ።
በኢሕአፓና በመኢሶን መካከል የነበረውን ልዩነት ወደ ቃላት አውርዶ፣ ጉዳዩን አልከስክሶ መተንተን የሚሰጠውን ጥቅም (ከሞራል ማካካሻ ባሻገር) ሊገባኝ ባይችልም፣ ከተራ የፖለቲካ ትንተና በላይ ሊሆን እንደማይችል እረዳዋለሁ። ይህን ትንተና ሄዶ ሄዶ ለሃገራቸው የተሻለ ሥርዓትን እናመጣለን ብለው <<ጊዜያዊ ሕዝባዊ መንግሥት ፣ የዴሞክራሲ መብት ያለገድብ . . . >> ሌሎች መፈክሮችን አንግበው የተሰውቱን ወጣቶች በ“ቸ” ና በ”ሸ” ልዩነት ተላለቁ ብሎ መደምደም ተገቢ አይደለም።
ዛሬ ከወያኔ ጋር መስራትና አለመስራት የሚለው ጥያቄ ጉልህ እንደሆነ ሁሉ ከደርግ ጋር መስራት አለመስራት የሚለውም በዚያ ወቅት ገሃድ ነበር። ዛሬ ሕዝባዊ መንግሥት የሕዝብ ጥያቄ እንደነበር ያኔም የወጣቱ መፈክር ነበር ፣ ያኔ የዴሞክራሲ አለገደብ ጥያቄ ያስገድል ያሳስር እንደ ነበር ዛሬም አያሸልምም። ያኔ ደርግን የሚቃወሙትን አናርኪስት ፣ ፀረ ሕዝብ ተብለው ይገደሉ እንደነበር ዛሬም አሸባሪ ፣ ፀረ ሰላም . . . እየተባሉ አይለቀቁም። እንዲህ ከሆነ ታዲያ የዛን ወቅት ትግል ለቃላት የዘንድሮውን ለዴሞክራሲ የሚደርገው ምኑ ነው? ምንአልባት ትግል ነውና የተሠሩ ስህተቶች ይኖራሉ። እንዚያን በትክክል ካልተተነተኑና ያንን ትውልድ ለመውቀስ ብቻ ሲባል <<ጽንፈኛ>> የሚል ቃል መጠቀም ቆንጆዋን ልጅ በተሰባበረ መነጽር ተመልክተው አስቀያሚ ነች ከማለት ተለይቶ አይታይም።
ዛሬ ለሃገሩ ቆሞ የሚታገል እያነስ በመጣበትና የግል ጥቅም ጎልቶ የሚታይበትን ምክንያት አበጥሮ ማየት ያስፈልጋል ። ከሁሉም በላይ ደግሞ ለሃገሩ ሟች ትውልድ ለማፍራት ከተፈለገ ቀደም ለሃገራቸው በንጽሁ ዓላማ የተስውትን ጀግኖች ታሪክ የጠጅ ቤት የአግዳሚ ወንበር ጨዋታ አለማድረግ አስፈላጊ ነው። እኔ በማምንበት በጀግኖች ታሪክ ላይ ጀግንነት ይፈጠራል። ጀግኖችን አዋርዶ ፣ የሞቱበትን ግዙፍ ዓላማ አጣጥሎ በቃላት ልዩነት እንደሆነ አድርጎ መተንተን ነገም ለሃገር የምንሰዋበት ምክንያት ሊጣጣል እንሚችልና እንደ ዘንድሮ ደልቃቃ ፖለቲከኛ <<ሞኝ ያለቀው በቀይ ሽብር>> በሚል መፈክር ሥር ተሰባስቦ አነስተኛ የሆነውን መስዋትነት ለመክፈል አለመዘጋጀትን ያመጣል። ተመስገን ከላይ በጠቀስኩት ጽሁፉ እንደገለጸውም መታሰርን እንደ ታላቅ መስዋእትነት ተቆጥሮ በወያኔ የፊርማ ስነ ሥርዓት ውስጥ ተካቶ በራስ ላይ የእንጥልጥል ፍርድ አስፈርዶ መፈታትንም ያስከትላል። ለሃገር፣ ለሕዝብ መሞት ከገለባ የቀለለ ለግል ጥቅም መቆም ደግሞ ከተራራ የገዘፈ ሲደረግ እንዲዚህ ነው።
ውድ ታናሽ ወንድም ተመስገን . . . ለዓላማ መሞት ከባድ ነው። መሣሪያ ይዞ ሊገድል የቆመን ፋሽሽት ጊዜያዊ ሕዝባዊ መንግሥት ፣ የዲሞክራሲ መብቶች አለገደብ እያሉ መሞት <<ቸ ቸ ቸ>> ወይም <<ላ ላ ላ>> እያሉ መሞት አይደለም። የመጻፍ መብት ስትከለከል “ አደፍርስ “ የሚባል የማባዣ መሣሪያ ሠርቶ በድብቅ የሚያምኑበትን ጽፎ መበተንና ከዚያም ተይዞ መገደል “ቸ” ና የ”ላ” ትግል ውጤት አይመስለኝም። የተገፈፉትን ነጻነት በትግል የማግኘት የዴሞክራሲ ጥያቄ እንጂ!
በእነዚያ የዴሞክራሲ ጥያቄ አንግበው በተስዉ ጀግኖች ልቦና ውስጥ ምን እንደነበረ ከኢዲስ ዘመን ወይም ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተገኘም ንቃት አይተነትነውም። ያንን ለመገንዘብ በእነሱ ቦታ ራስን ማስቀመጥ ያስፈልጋል። ዛሬ በቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች ብዙ ቅጽል ስም ከመንግሥት ደጋፊዎች ይወጣላቸዋል። ይህንን ስም ማጥፈት የሚያምኑ ይኖራሉ። ከሁለት አስርተ ዓመታት በኋላ አንድ የደላው ጋዜጠኛ በአሁኑ ወቅት ያለው ትግል “ዓባይ ይገደብ አይገደብ ነበር” ብሎ ቢጽፍ የዘንድሮውን ሁኔታ ተነተነ ማለት አይቻልም። እነሽብሬም ፣እነ ተስፋዬም ፣ እነ አስፋ ማሩም፣ እነ ጋይምም በዚህ ምክንያት ተሰዉ ማለት አይደለም። ትግል ሙሉውን ሳይሆን በቅንጣቢ መተንተን የሚመጣው ስህተት ይህንን ይመስላል።
ጽሁፌን ለማጠቃለል ያህል ታላቁ ደራሲ ዩሐንስ አድማሱ ከዚህ ዓለም የተለየው በእድገት በኅብረት መጀመሪያ ወቅት ላይ ነበር። ከዚህ ከሚባለው ክፍፍል በፊት በመሆኑ እድለኛ ነው። እዚህ ውስጥ በቃላት አጠቃቀምም ቢሆን እንኳን ለመዶል መሞከሩም አስፋላጊ አይደለም። ይህም ቢሆን ቁንጽል የሆነ ጽሁፍ ጠልቆ ታሪኩን ለማያውቅ ግለስብ ሌላ ትርጉም ይሰጣል። ዮሐንስ አድማሱን ለመጥቀስ ከተፈለገ ውብ የሆኑ ሥራዎችን ከዚህ ክፍፍል ውጭ ለብቻቸው አንስቶ መወያየትን በግሌ እመርጣለሁ።
ስለ ያ ትውልድ የሚያስብ ሁሉ በሰላም ይክረም !
በልጅግ ዓሊ
Beljig.ali@gmail.com
Add new comment