በአደባባይ መዘባረቅ መብት አይደለም! ቁልቁለቱን ለብቻ
ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም
ከአጼ ኃይለ ሥላሴ ወዲህ የመጡት ገዢዎች የታሪክ አዋቂዎች ለመምሰል የሚጥሩ ናቸው፤ ምክንያቱን በኋላ እናየዋለን፤ በቅርቡ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ትግላችን የሚል ትልቅ መጽሐፍ አሳትሞአል፤ እዚህ ደሞ አቶ ስብሐት ነጋ አክሱም ለተንቤንና ለአጋሜ ምኑ ነው በማለት አዲስ የኢትዮጵያ ታሪክ ነግሮናል፤ የጎሠኛነት አስተሳሰብ እየጠበበና እያጠበበ መሄዱ የታወቀ ነው፤ እስቲ ስብሐት ተናገረ የተባለውን ፍሬ-ገለባነትን ትተን ያስተሳሰቡን አድማስ ቆንጠር አድርገን እንየው፡፡
‹‹ታሪክና የፖለቲካ አቋም ይለያያል፡፡ የተናገርኩት እኔ የማውቀውን ታሪክ ነው፡፡ ታሪክ አውቃለሁ የሚል ደግሞሊ ያጣራው ይችላል፡፡ ታሪክ የፖለቲካ አቋም ስላልሆነ ተነቦሊስተካከል ይችላል፡፡እኔ እንደሚመስለኝ የአክሱም መንግሥት በመጀመሪያ ደረጃ የከተማ መንግሥት ይመስለኛል፡፡እንደነ አቴንስ እንደነ እስፓርታ የከተማ መንግሥትይመስለኛል፡፡›› ሰንደቅ የካቲት 14፣ 2004
እነዚህ ስድስት ዓረፍተ ነገሮች አቶ ስብሐት ነጋ በተጠቀሰው ጋዜጣ ላይ የተናገራቸው ናቸው ተብለው የወጡ ናቸው፤ ዛሬ ሁለት ሳምንት ሊሆነው ነው፤ ስብሐት ነጋ አላስተባበለም፤ አንዳንዱን ዓረፍተ ነገር ለየብቻው እንየው፤--
1. ታሪክና የፖለቲካ አቋም ይለያያል፡ ፡ እስማማለሁ፤ ምንም ቅሬታ የለኝም፡፡
2. የተናገርኩት እኔ የማውቀውን ታሪክ ነው፡፡ ችግር አለ፤
ሀ)ስብሐት ነጋ የሚያውቀው ታሪክ ወላጆቹ ከሚያውቁትና እኛ ከምናውቀው ታሪክ እንዴት ተለየ? እኛ ተማሪ ቤት አልሄድንም፤ ወይ እሱ ተማሪ ቤት አልሄደም፤ ወይ የእኛ እውቀት በልፋት የተገኘ ሲሆን የእሱ በመንፈስ ኃይል የተገለጠለትና የታየው ነው፤ ወይ ስለጉዳዩ የተጻፉትን መጽሐፍት አላነበበም፤
ለ)የተናገርሁት እኔ የማውቀውን ነው ማለት ምን ማለት ነው? አንድ ሰው አራትና አራት ስድስት ነው ከአለ በኋላ የተናገርኩት እኔ የማውቀውን ሂሳብ ነው ቢለን ምን እንለዋለን? ድንጋይ ቢበሉት ያጠግባል ብሎ ከተናገረ በኋላ የተናገርኩት እኔ የማውቀውን ነው ቢለን ምን እንለዋለን?
3. ታሪክ አውቃለሁ የሚል ደግሞ ሊያጣራው ይችላል፤ አውቃለሁ ያለው ስብሐት ራሱን መጠራጠር የጀመረ ይመስላል፤ በታሪክ እውቀት ከስብሐት የሚበልጥ ሰው ከአለ ጉዳዩን እንዲያጣራው ፈቃድ ይሰጣል፤ በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ሰው ከአነበበና ከተመራመረ ስብሐት ወደደረሰበት መደምደሚያ ሊያደርስ ይችላል ማለቱ ይሆናል፡፡
4. ታሪክ የፖለቲካ አቋም ስላልሆነ ተነቦ ሊስተካከል ይችላል፤ የአስተሳሰብ ችግሩ ምንጭ እዚህ ላይ ነው፤ ይህ ዓረፍተ ነገር በቅርጹም በይዘቱም ፉርሽ ነው፤ ሊስተካከል የሚችለው ታሪክ ነው? ወይስ የፖለቲካ አቋም? በስብሐታዊ አስተሳሰብ የፖለቲካ አቋም አይነቃነቅም፤ አይለወጥም፤ ታሪክ ግን ሊለወጥ ይችላል፤ በስብሐታዊ አስተሳሰብ የፖለቲካ አቋም ሃይማኖት መሆኑ ነው፤ ስለዚህ አይለወጥም፤ ይችላል፤ ለስብሐት ከራራንለት ስለታሪክ
የሚያነብ ሰው የበለጠ ሲያውቅ ራሱን ያስተካክላል ብለን እንተረጉምለታለን፤ ለስብሐት ካልራራንለት ደግሞ ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት የሆነውን ታሪክ እናስተካክለዋለን ማለቱ ስለሆነ ልክ አይደለም እንላለን፤ በሌላ አነጋገር ታሪክ በስብሐት አስተሳሰብ ይስተካከላል፤ በጣም ግልጽ ለማድረግ፣ ስብሐታዊ አስተሳሰብ የሚለው ያለፈውን፣ ያላየነውንና በቀጥታ የማናውቀውን መለወጥ እንችላለን፤ የወደፊቱን፣ ያልደረስንበትን፣ እኛ ራሳችን እየሰራን ያለነውን ግን ልንለውጠው አንችልም!
5. እኔ እንደሚመስለኝ የአክሱም መንግሥት በመጀመሪያ ደረጃ የከተማ መንግሥት (City state) ይመስለኛል፤ እዚህ ላይ ታሪክን ወደተረት የመለወጥ ዝንባሌ መጣ፤ አክሱምን እንደነገሩ እንኳን የማያውቅ ሰው ባሕር ተሻግሮ ስለአቴንስና ስለስፓርታ እንደነገሩ እንኳን የማያውቀውን ቢጨምርበት ወደታች እንጂ ወደላይ የሚወስድ መንገድ አያገኝም፤ የየጁ ደብተራ ቅኔ ቢጎድልበት ቀረርቶ ሞላበት እንደሚባለው የማይገናኙ ነገሮችን ማገናኘት ነው፤ ወይም በአፈር ቡኮ ቂጣ ለመጋገር አይቻልም፡፡)
አንድ ሰው እንኳን ሳይገደድ ተገዶስ ቢሆን የማያውቀውን ነገር ለምን ይናገራል? አንድ ጊዜ ግቢ በአስቸኳይ ድረስ ተብዬ ሄድኩና ጃንሆይ ፊት እጅ ነሥቼ ስቆም፣ ‹‹የት›› ስለሚባል ኦጋዴን ውስጥ ያለ መንደር ጠየቁኝና እንደማውቀው ከተናገርሁ በኋላ በ‹‹የት›› የሚገኘው የውሃ ጉድጓድ በቀን ስንት በርሜል ውሃ ይወጣዋል? ብለው ጠየቁኝ፤ ‹‹ጃንሆይ አላውቅም፤›› አልሁ ደጋግመው ግምት ጠየቁኝ መልሴ ያው አላውቅም ሲሆንባቸው ‹‹ሂድ ውጣ!›› አሉኝ፤ የማላውቀውን ለምን ልዘባርቅ የኢትዮጵያን ታሪክ አጥርቶ ሳያውቅ ጭራሹኑ ወደማያውቀው ወደ ጥንቱ የግሪክ ታሪክ ምን አስኬደው!
ታሪክ በአጥንትና በደም የተገነባ መቅደስ ነው፤ ታሪክ የስንትና የስንት ትውልዶች የተጋድሎ፣ የፍቅርና የቃል ኪዳን፣ የኩራትና የክብር፣ የመብትና የግዴታ ገድል ነው፤ ታሪክ መዝገብ ነው፤ ምስክር ነው፤ ታሪክ የህልውና መሠረት ነው፤ ማንነት ነው፡፡
በአለፉት አርባ ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ታሪክ ከፋሺስት ኢጣልያ ዘመን ያላነሰ ውርደት ደርሶበታል፤ አምባ-ገነኖች ታሪክን የሚያነሡት የወደቀውን ለመቅበርና ሁልጊዜም በግልጽ እንደሚሉት ‹‹በመቃብሩ ላይ ለመቆም›› ነው፤ ከዛሬ በፊት የነበረውን ሁሉ በማራከስ፣ በማጥላላት፣ በማናናቅ፣ በማፍረስ ታሪክ ነገ እንደሚጀምር የተስፋ ዳቦ መጋገር ለአለፉት አርባ ዓመታት የተለመደ ሆኖ እያሰለቸን ነው፤ የትናንቱ ታሪክ በትንንሽ ሰዎች እንደማይደመሰስ ሁሉ የነገውም ታሪክ በትንንሽ ሰዎች አይገነባም፡ ፡
ትናንትን ያላግባብ እያራከሰ ለመቅበር የሚጥር ሁሉ ዛሬን ትናንት ያደርገዋል፤ ትናንትንና የትናንትን ኃይል ከነድካሙ በትክክል ያልተገነዘበ የሚቆምበት መሬት አያገኝም፤ የሚንደረደርበትም ሆነ የሚንደረደርለት ዓላማ የለውም፤ ከሆዱ በቀር የሚሞትለት ወይም የሚሞትበት ዕዳ የለውም፤ እንደእውነቱ ከሆነ ግን ሁላችንም የታሪክ ዕዳ አለብን፤ ጥንት ከተለያዩ ቄሣራውያን ኃይሎች ጋር አባቶቻችንና እናቶቻችን የፈጸሙትን ተጋድሎ እንርሳው፤ ከሰባ አምስት ዓመት በፊት ከፋሺስት ኢጣልያ ጋር ለተደረገው ትግል የተከፈለውን መስዋዕትነት እንርሳው፤ ለመቋቋም የተከፈለውን መስዋእት እንርሳው፤ የቅርቡን የባድመን እንዴት ልንረሳው እንችላለን? በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች የጅብና የአሞራ ምግብ ሆነው የቀሩት በእውነት ለቁራጭ መሬት ብቻ ነው? የአድዋ ክብርና ኩራት፣ የማይጨው ውርደት የለበትም? እንደስብሐት ነጋ ያለ በትልቅ የኃላፊነት ቦታ ላይ ያለው ሰው ይህንን ይስታል ለማለት ያስቸግራል፤ ስሕተት ካልሆነ ታሪክን በጎሣ ማጥበብ ዓላማው ምንድን ነው? አደጋ ሲመጣ እንኳን ከተምቤንና ከአጋሜ ጋር ከቦረናና ከኦጋዴንም ጋር የታሪክ ዝምድና መቁጠር አስፈላጊ ይሆናል፡፡
በወላጆቻችን የምናፍርበት ምክንያት ቢኖርም መንፈሳዊ ወኔያችንን አጠንክረን ህመማችንን ልንጋፈጠው ይገባል እንጂ ታሪካችንን በሙሉ በማራከስ ከሐፍረታችን አንድም፤ የአንድ ሰው ታሪክ የአንድ ሰው ታሪክ ነው፤ የአንድ ቤተሰብ ታሪክ የአንድ ቤተሰብ ታሪክ ነው፤ የአንድ አገር ታሪክ ደግሞ የተለየ ነው፤ የሁሉም ነው፤ ኩራትና ክብሩ የጋራ ነው፤ ውርደትና ሐፍረቱም የጋራ ነው፤ የግል ቁስልን አክካለሁ ብሎ አገርን ማቁሰል ተገቢ አይደለም፡፡
ትናንት ለዛሬው ሕይወት የሕይወት ዋጋ የተከፈለበት ነው፤ ዛሬ የትናንትን ውለታ ተሸክሞ የቆመ ነው፤ ይህ ሸክምና ውለታ ለእንደ ስብሐት ነጋና መሰሎቹ አይሰማቸውም፤ እነሱ የሚያውቁት የዛሬውን ምቾትና ጉልበተኛነት ነው፤ እነሱ የሚያውቁት የዛሬውን ማናለብኝነት ነው፤ አቶ ስብሐት ስለአክሱም ታሪክ የተናገረው (መናገሩን የማውቀው ባለማስተባበሉ ነው፤) በትምህርትም ሆነ በንባብ ያገኘው ነው ለማለት ይከብዳል፤ አለማወቁን የነገረን ስለአክሱም ብቻ ሳይሆን ስለከተማ ሀገረ-መንግሥቶችም (City state) ነው፤ በእርግጥ ለስብሐት አዲስ የሚባል ነገር ተናግሮአል፤ የተለየ ነገር የሚያውቁ ካሉ ያስተምሩ፤ ይናገሩ፤ በማለት ፈቅዶአል! ስለዚህ ልንጨክንበት አይገባም፤ ነገር ግን አንድ ጥያቄ ለመጠየቅ እንገደዳለን፤ ከመጠምጠም ትምህርት ይቅደም፤ የሚባለውን ስብሐት ሳይሰማ አይቀርም፤ ስለዚህ የማያውቀውንና እርግጠኛ ያልሆነበትን ዓቢይ የአገር ታሪክ ሞሽልቆ ራቁቱን አስቀርቶ በአደባባይ በጋዜጣ ለመናገር እንዴት ደፈረ? የማያውቁትን ነገር ለማወቅ መድኃኒቱ መጠየቅ ነው፤ ጥያቄ በመጠየቅ የሚወቀስ የለም፤ የማያውቁትን በአደባባይ መዘባረቅ ግን ከማስወቀስ አልፎ ያስንቃል፡፡
የአክሱምን ሀገረ-መንግሥት የአረብ፣ የኢጣሊያ፣ የፈረንሳይ፣ የእንግሊዝ፣ የሩስያ… ሊቃውንት ለረጅም ጊዜ አጥንተው ጽፈውበታል፤ እኔ በእጄ ስላሉ የጥናት ውጤቶች ለመናገር ነው እንጂ በጀርመንና በሌሎችም ቋንቋዎች ጥናቶች ይኖሩ ይሆናል፡፡
ታሪክ የቡና ቤት ወሬ አይደለም፤ ማን ጠያቂ አለብኝ በማለት አፍ እንዳመጣ እየተናገሩ ታሪክን ማወላገድ ለወጣቶችና ለትንንሾቹ ልጆች አለማሰብ ነው፤ አንድ ሰው ስለአክሱም ሀገረ- መንግሥት የምን ያህል ጊዜ ጥናት አድርጎ፣ የእነማንን ጥናት አንብቦ የአክሱምን ታሪክ በድፍረት ለመናገር ቻለ የሚለውን ጥያቄ ማንሣቱ ዋጋ የለውም፤ ምክንያቱም አንድ ነገር ወይም አንድ ሰው ከባሕርዩ ውጭ ሌላ ሊሆን አይችልም፤
ታሪክ ሰዎችን ለማስደሰት ወይም ለማዝናናት የሚነገር ተረት አይደለም፤ ምን ዓይነት ጥላቻና ጎሠኛነት ነው በድንጋይ ላይ የተጻፈውን ታሪክ ለመካድ የሚያስገድድ? እንደስብሐት ሥልጣንን እውቀት አድርገው ለሚገምቱ ሰዎች በ1996 በታተመው የክህደት ቁልቁለት መጽሐፍ ውስጥ የተለያዩ ሊቆች፣ የፈረንሳይና የአረብ፣ የኢጣልያም ሆነ የእንግልጣር ሳይቀር፣ ስለአክሱም የጻፉትን ጠቅሼ በአራት ገጾች ላይ ጽፌ ነበር፤ ሌላው ሁሉ ቀርቶ ያንን እንኳን ያላነበበ ሰው አንብቦ ስለማጣራት ይነግረናል፤ በተለያዩ ምክንያቶች የተጠቀሱትን መጽሐፍት ለማንበብ የማይችል ሰው ባይሆን ጥቅሶቹን አንብቦ ሌላውን ከማሳሳት መዳን ይችል ነበር፤ ሥልጣን አለኝ ተብሎ አለማወቅን በአደባባይ ማወጅ፣ ሕዝብን፣ በተለይም ወጣቱን ከጥንት ታሪኩ ጋር ለማቆራረጥ መሞከርና ማሳሳት ሊያሳፍር ይገባል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ሥልጣን በእውቀት ላይ ያለውን የበላይነት በግልጽ የሚያሳየን ከሠላሳ ሁለት ዩኒቨርስቲዎች (ዶር. ዳኛቸው እንዳለው ይህንን ያህል ካሉ) ውስጥ አንድም የታሪክ ሊቅ ለሙግት ብቅ አላለም፤ ሌላው ቀርቶ የኢትዮጵያ መካነ ጥናትም ትንፍሽ ሲል አልሰማሁም! ሁሉም በሆዱ ተሰንጎአል! እዚህ ላይ የስብሐት ድፍረት ይጠቅማል፤ ስብሐት ቢጠየቅ ስለጳጳሳቱ ያለውን ስለሊቃውንቱ ይደግመው ነበር፤ በመሀከላቸው አንድ ሰውም የለባቸውም እንደሚል አልጠራጠርም!

Comments
Anonymous (not verified)
Mon, 03/12/2012 - 16:28
Permalink
I love this guy! WAW I
I love this guy! WAW I appreciate the way u see things! Long live prof.!!!!!!!!!
to u (not verified)
Mon, 03/12/2012 - 17:11
Permalink
comment
does Sibhat know queen of sheba(she is from tenben) read the book the "queen of sheba and king solomun. not only this Axum empire is the owner of Tigray, Amara, eritra and else. pls it is not politics. Axume empire is the owner of Ethiopia, Yemen, somalia, Djibuti, sudan, -------
for u (not verified)
Mon, 03/12/2012 - 17:19
Permalink
comment
I have no words than to say 'INTERESTING'. Now days we need such a courageous scholars who cares no about economic and other related benefits.Shame to those who hold ph.D in history but kept quiet to gain EPDRF'S coin and cheap popularity.
Bekalu (not verified)
Mon, 03/12/2012 - 21:37
Permalink
you are our compass
WE BELIEVE IN PROFESSOR MESFIN WELDEMARIAM!!!!!!!!!
true always (not verified)
Tue, 03/13/2012 - 00:31
Permalink
axum
we know more then ever our leaders
ayke (not verified)
Tue, 03/13/2012 - 04:44
Permalink
A man of no equal!
Professor Mesfin is a man of no equal of his contomporaries. May the almighty gives you long life and good health!
Professor (not verified)
Tue, 03/13/2012 - 23:38
Permalink
comment
OMG, may God bless Professor Mesfin!!
Haftom (not verified)
Wed, 03/14/2012 - 15:00
Permalink
thanks
thanks professor. Long live!
Haftom (not verified)
Wed, 03/14/2012 - 15:00
Permalink
thanks
thanks professor. Long live!
jerusalem (not verified)
Wed, 03/14/2012 - 20:52
Permalink
Thanks professor
What a precise and intellectual analysis !!! Professor has always the courage to bring facts on the table. I admire him. He is trying to save our history from distortion and individual interests. His writings are very simple and easy to understand. Ethiopia is not a country which is built overnight. History tells us that there have been many up and downs and we shouldn't have the nerve to see our identity to fade and wiped. Thanks Professor for your relentless effort to educate our new generation.
sammy (not verified)
Thu, 03/15/2012 - 05:59
Permalink
thank you professor Mesfin
I salute you professor Mesfin. You always stand on truth no matter what and that is what we need these days more than ever. Specially, given the current situation our country is in the hands of anti Ethiopian’s like Sibhat and melese. They need to know that Ethiopia still have genuine sons and daughters and undoubtedly, professor Mesfin is one of them. “Esat beanklafa geleba gobegnew” so, those of you who know history you should step up and sate the record straight when some ignorant like Sibhat talking garbage.
As always good job professor!
Ethiopiawenet (not verified)
Fri, 03/16/2012 - 13:54
Permalink
Let us tals solutins
Ethiopia's all rounded master mind Pro. Mesfin is struggling still public ambition to be true but the rest of us are busy at reading his marvelous writings but the info we still have are good enough now let us talk/discuss about the way to solve the problems we already have, let us find a new way to to freed ourselves this lead us to take action.
Teddy (not verified)
Sun, 03/18/2012 - 23:43
Permalink
am bowing down professor..for the truth.
History is not a story that one can maneuver. Sebhate's illogical stand on ethiopian History is nothing but adding another fabricated or politically orchestrated propaganda, i would say, to their(EPRDF) ethnic based politics. i salute you Professor for shading light to this evil deeds.
Anonymous (not verified)
Mon, 03/19/2012 - 03:59
Permalink
It is really professional
It is really professional comment.
Hadush (not verified)
Mon, 03/19/2012 - 11:18
Permalink
I am proud of you Mesfine
Professor I am proud of you! On the contrary ...... To day's Ethiopian rulers are not only interested to capture the present generation they have also a zeal interest to shape the past generation in their own imagination. Thank a lot Proffesor we tghe young generation of ethiopia should have follow the foot step of a true proffesionals like you
Ahmed Ali (not verified)
Mon, 03/19/2012 - 22:17
Permalink
love and respect
As usual my hats off to my life long idol! One of our countries biggest tragedy is that there is no one on the horizon who is going to replace this great thinker of our time. I feel blessed and honoured to have had the opportunity to listen to this genius person while giving a lecture to the Swedish Socialdemocratic party leaders in Stockholm. I remember how proud i was watching him the way he was enlightning the Swedish leaders with the ABC of the contemporary history of the horn of Africa and the middle east. One of the organizers of prof. Mesfins visit to Sweden, a high profile of the party, still call him " my idol, the pro" . Professor Mesfin is the fearless, the courageous, the intellectual giant and the ever shining star of that poor but beloved country of ours. GOD BLESS YOU, PROFESSOR!!
Anonyms (not verified)
Tue, 03/20/2012 - 20:48
Permalink
I am proud of you Prof., long
I am proud of you Prof., long live to you
ፍሥሓ (not verified)
Wed, 03/21/2012 - 08:42
Permalink
ሚዛን ያለው ሰው አያሳጣን
"ይበል" ለማለት ልቤ ፈቅዶ ሳለ አእምሮየ ከለከለኝ፤ "በየትኛው ዐቅምኽ?" ብሎ። እንዲያው በድፍኑ "እንዲህ ሚዛን ያለው ሰው አያሳጣን" ከሚል ጸሎቴ ጋር ዐሳቤን በጥቂቱም ቢኾን ልግለጥ።
የዕውቀት ወይም የችሎታ ዘርፉ ብዙ ነው። ነውና አያ ስብሐት እንደወጠጤ ወይም እንደ ሙክት ሊታይበት የሚችል ዘርፍ ይኖር ይኾናል (ለምሳሌ፦ ጕህሉት፣ ጽልሑት፣ እከይ)። በታሪክ ዘርፍ ግን ግልገል ነው።
እኔን የሚቆጨኝ፤ በውዴታ የማከብርዎ ፕሮፌሶር፦ ሰው ሳይጠፋ (ነው ወይስ ጠፍቷል?!) ይቺ ታላቅ አገር፣ ታላላቅ ሊቃውንቷ፣ ምሁራኗ እና ዐርበኞቿም የገላግልት መጫወቻ መኾናችኹ!!!
Tsnat Bekalu (not verified)
Thu, 03/22/2012 - 20:15
Permalink
Awesome analysis!
I guess, Prof is the right person to talk about Ethiopian history.
Girma (not verified)
Thu, 03/22/2012 - 22:21
Permalink
Thank you
Thank you, Professor Mesfin Woldemariam, for keeping on fighting against the enemies of Ethiopia to the best of your ability even in these very late years of your life just to preserve our history and represent our country in the only the way it deserves it.
malaku (not verified)
Mon, 03/26/2012 - 17:46
Permalink
Great comment and expression
Great comment and expression!
ቁንቡሩስ (not verified)
Thu, 03/29/2012 - 12:22
Permalink
ኣስተያየት
በሀገር ታሪክ ደግሞ ዝሙት ጀመሩ!
dokile (not verified)
Fri, 03/30/2012 - 14:09
Permalink
Thank you
proff.nothing to say other than GOD BLESS U!!!
Add new comment