ያስፈራል፤ ግን ኢትዮጵያ አትፈርስም!

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም
ይቺ ኢትዮጵያ የምትባል አገር ስንት የመከራ ወንዞችን ተሻግራለች! ገና ስንት ትሻገራለች! ስንት የግፍ ተራራዎችን አቋርጣለች! ገና ስንት ታቋርጣለች! ስንት የበደል ሰይፎችንና ጦሮችን አምክናለች! ገና ስንት ታመክናለች! ስንት የውጭ ኃይሎችን አሳፍራለች! ገና ስንቱን ታሳፍራለች! ስንት አምባገ- ነኖችን እያለቀሰች ቀብራለች! ገና ስንቱን ትቀብራለች! ጭቆና ከኢትዮጵያውያን ደም ሙልጭ ብሎ ወጥቶ በነፃነት፣ በእኩልነት፣ በዳኝነት በጠራ ደም እስቲተካ ድረስ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ዘርግታ ትጸልያለች! እግዚአብሔርም ቃል ኪዳን አለበት ይሰማታል! የኃያላን ኃያል ኢትዮጵያ እንድትፈርስ አይፈቅድም!
የኢትዮጵያን መፈራረስ የሚመኙ ግለሰቦችም መንግሥቶችም ሞልተዋል፤ ኢትዮጵያ እንድትፈራርስ የሚመኙ ጭንጋፍ ልጆችም አሏት፤ ማኅጸንዋ እየደማ እየረገማቸው ሰላምና እንቅልፍ አጥተው አብጠው ይፈነዳሉ፤ የኢትዮጵያን መፈራረስ የሚመኙ መንግሥቶች ሁሉ ከዚህ በፊት ቀድመው ፈራርሰዋል፤ ወደፊትም ይፈራርሳሉ።
የአገራቸው ፍቅር፣ የእርስበርሳቸው ዝምድና፣ የተራራውና የሸለቆው፣ የሜዳውና የገደሉ፣ የበረሀውና የለምለሙ፣ የዝናቡና የወንዙ፣ የዓየሩና የነፋሱ፣ የበዓላቱና የድግሱ፣ ያለውን አብሮ መቋደሱ፣ ተዝካሩ፣ ሙታዓመቱ ለሞቱ፣ መላእክቱ፣ ቅዱሳቱ፣ ሰማዕታቱ፣ እየተሸከሙ ያደረሱት ጸሎቱ፣ ለምዕተ-ዓመታት የተከማቸው እምነቱ፣ ሃይማኖቱ፣ በዚህ ሁሉ የተገነባው ኅብረቱ እንዴት ይፈርሳል! ማን ችሎ ያፈርሰዋል! አፍራሾች ቀድመው ይፈርሳሉ!
አንዳንዶች ቢጨነግፉም፣ አንዳንዶች ቢክዱም፣ አንዳንዶች ሆዳም ቢሆኑም፣ አንዳንዶች ቢወላውሉም፣ ኢትዮጵያ ልጆች አሏት፣ አሁንም የሚሞቱላት፣ ያልበሏት፣ የሚሳሱላት፤ ያልሸሿት፤ አፈሯን የሙጢኝ ብለው አፈርሽ እንሁን የሚሏት፣ ደሀነትም ሆነ ጭቆና ካንቺ አይለዩንም የሚሏት፣ ኢትዮጵያ ዛሬም ልጆች አሏት ስትፈርስ ቆመው የማያዩ፣ ሲያማት ነፍሳቸውን ዘልቆ የሚያማቸው፣ ሳልፈርስ አትፈርስም ነው ቃል ኪዳናቸው።
ቱርክና ግብጽ መጥተው ሄደዋል፤ ፖርቱጋል መጥቶ ሄዷል፤ እንግሊዝ መጥቶ ሄዷል፤ ኢጣልያመጥቶ ሄዷል፤ ጠላቶች እየመጡ በመጡበት ተሸኝተዋል፤ ወዳጆች በጨዋነት ተስተናግደው ተዋኅደዋል፤ ቤተ ሙሴ፣ ቤተ ክርስቲያን፣ ቤተ እስልምና ኢትዮጵያዊ ሆነዋል፤ ዛሬ እንግዳ አይደሉም፤ ዛሬ ባዕድ አይደሉም፤ ኢትዮጵያ በፍቅር ለመጣ ፍቅር ነች፤ ምቹ ነች፤ በጠብ ለመጣ እሾህ ነች፤ ትዋጋለች።
ኢትዮጵያ፣ ነቢዩ ኢሳይያስ ለአንቺ የተናገረው ይመስለኛል፤ ‹‹ብርሃንሽ መጥቶአልና፣ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ፤ አብሪ፤ እነሆ ጨለማ ምድርን ድቅድቅ ጨለማም አሕዛብን ይሸፍናል፤ ነገር ግን በአንቺ ላይ እግዚአብሔር ይወጣል፤ ክብሩም በአንቺ ላይ ይታያል፤ አሕዛብም ወደብርሃንሽ፣ ነገሥታትም ወደመውጫሽ ጸዳል ይመጣሉ።
ዓይኖችሽን አንስተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ፤ እነዚህ ሁሉ ተሰብስበው ወደአንቺ ይመጣሉ፤ ወንዶች ልጆችሽ ከሩቅ ይመጣሉ፤ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃ ላይ ይሸከሙአቸዋል፤ በዚያን ጊዜ የባሕሩ በረከት ወደአንቺ ስለሚመለስ፣ የአሕዛብም ብልጥግና ወደአንቺ ስለሚመጣ አይተሽ ደስ ይልሻል፤ ልብሽም ይደነቃል፤ ይሰፋማል፤ የግመሎች ብዛት የምድያምና የጌፌር ግመሎች ይሸፍኑሻል፤ ሁሉ ከሳባ ይመጣሉ፤ ወርቅንና ዕጣንን ያመጣሉ፤ የእግዚአብሔርንም ምስጋና ያወራሉ፤ የቄዳር መንጎች ሁሉ ወደአንቺ ይሰበሰባሉ፣ የነባዮትም አውራ በጎች ያገለግሉሻል፤ እኔን ደስ ሊያሰኙ በመሠዊያዬ ላይ ይወጣሉ፤ የክብሬንም ቤት አከብራለሁ።›› (60/1-7)
ኢትዮጵ ትወድቅ ይሆናል፤ ግን ያለጥርጥር ትነሣለች፤ በፊትም ወድቃ ተነሥታለችና፤ ኢትዮጵ ትሰነጠቅ ይሆናል፤ ግን ያለጥርጥር ትገጥማለች፤ በፊትም ተሰንጥቃ ገጥማለችና፤ ለኢትዮጵያ በጎ የማይመኙላት የአየሉ ቢመስሉም የንስሐ ጊዜ ስትሰጣቸው ነው፤ ኢትዮጵያ ዕብሪተኞችንም ትሕትና ታስተምራቸዋለች፤ ዕብሪተኞች ከነዕብሪታቸው በራሳቸው እሳት ቀልጠው እስቲያልቁ ኢትዮጵያ ትእግስትዋ አያልቅም፤ ኢትዮጵያ ትእግስት ነችና።
በበጎ መንፈስ እስከተመራን ድረስ፣ ፍርሃትንና አለመተማመንን፣ ጥላቻን፣ ጠብንና ድብድብን፣ ሊዘሩብን ከሚፈልጉ ርኩሳን መናፍስት ከራቅን ኢትዮጵያችን አትፈርስም፣ የደፈረሰውም ቶሎ ይጠራል።

Comments

ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ዘርግታ ትጸልያለች! እግዚአብሔርም ቃል ኪዳን አለበት

Yes Ethiopia will stay forever! This is real prophecy that has been given through Prof.Mesfin

ፕሮፌሰር

ሃቅ ነው ... እውነት ነው ... አሜን !!

እወደወታለሁ .... አከብረወታለሁ ... የሰላም አባት ነወት ... የነጻነት ነቢይ !

እንደርስዎ ያለ ሺህ ይወለድ! ይወለድና ዕድሜ ይጥገብ! ሃይማኖት-የለሽ፣ ለዛ-የለሽ፣ ከሃዲው ግን፦ ሲኾን አይፈጠር፤ ከተፈጠረ ደግሞ ለይኩን "ከመ-ሣዕረ-አንሕስት ዘይየብስ ዘእንበለ-ይማሐውዎ።"

ኢትዮጵያችን አትፈርስም!!!!!

.....በበጎ መንፈስ እስከተመራን ድረስ፣ ፍርሃትንና አለመተማመንን፣ ጥላቻን፣ ጠብንና ድብድብን፣ ሊዘሩብን ከሚፈልጉ ርኩሳን መናፍስት ከራቅን ኢትዮጵያችን አትፈርስም፣ የደፈረሰውም ቶሎ ይጠራል።---Amen

One of the very very few Optimist volition of Professor Mesfin. Thank you Prof!

OH,PROFESOR! tilk &rejim edme yistewot.awq ethiopia atfersim.ersewo ethiopia eyeferesech zim blo yemiyaye lij yelatim kaluachew wotatoch ene andu negne.ene atse TEWODROS yemotulaten hager manim bihon ayafersarim.LONG LIVE ETHIOPIA!!!!!

Endet senebetu Prof. Tesfachin Fetariachin new.

Oh God...am getting crazy! Long Live Prof.!!!!!!!!.....

Ene abate beye beterawot yemifekidulegn yemeselegnal..be ergit ene yerso lij lemebal tinish enkuan wene yelelegn sew behonim, enam erso bezih zemen Ethiopiawinet,ye ewenet sew,yetemare sew min malet endehone endenayebot egziabeher behiwot yakoyelin sew nowet ...le erso edmie legna wene egziabeher yisten...egziabeher yayal ena hizebachewen litebikut sigeba eyasechenekut lalutim lib yistachew!!!!

we have very few people like professor mesefen in ethiopia todaY,edema le tplf wey beferhat afachew tezegetowal wey kager wetewal

እድሜ ይስጠዎት፡ የኢትዮጵያንም አንድነትና ነጻነት አብሮ ያሳየን:: ተስፋ እየቆረጥኩ በመምጣቴ የአገሬን መፍረስ ባይኔ ላለማየት ጠላቷን አጥፍቶ መጥፋት ይሻል ይሆን እያልኩ ሳመነታ መጽናኛ ይዘውልኝ ብቅ አሉ። ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።
በኢትዮጵያና በህዝቦቿ ደም የሚቀልድ በደም ነቀርሳ ይሞታል።!

I am speechless

God bless Ethiopia.

ብዙዎች ሲያፈርሱ፣ ሲፈርሱ፤ ሲያደቡ ሲደበደቡ ኖረዋል፡፡ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር እያንዳንዱ መከራና በደል ተሠፍሮና ተቆጥሮ ለባለጊዜው መከፈሉ የማይቀር ነው፡፡ የኢትዮጵያ አንድነትና ኢትዮጵያዊነት ግን ከፍርሃት ዋሻ እየወጣ በሕዝቦች መተመመንና መተባበር የሚፈጠርበት ሥዕል ጥርት እያለ እየታየ ነው፡፡ እናም አፍራሹ ግብረ ኃይል መዶሻው ብርቱና ከእጁ የማይፈለቀቅ ቢመስለውም፤ እያየን ያለነው ተቃራኒውን ነው፡፡ እናም እንደ ፕሮፌሰር መስፍን ምክር ራሳችንን ከጥላቻና ከቂም በቀል በማጽዳት "ቆይ ነገ ወያኔ ሲወርድ ዛቻን" ተወት አድርጎ አብሮነትን በዘላቂነት ማሰቡ ጠቃሚ ነው፡፡

Prof. They try to destroy Ethiopia but they couldn't and they wouldn't too. Any ways we will get our history back soon by peoples like u. Long live Prof.

አውነቶን ፤ ነው፤ ፕሮፊሰር፤ አግዘር ፤ አላት ፤ኢትዮጵያ ፤ሁሉንም፤አናየዋለን፤

Ethiopia has been a prison for other peoples except for Amharas and Tigrians. And it should be dimemembered like Soviet Unions. The southern nationalites, Oromia, Ogaden and Afar should have their own separate homelands. They have nothing in common to bind them to Semetic people. We are nothing in the Ethioipian Empire but slaves. Therefore, we keep pushing until the empire is dismantled and create our separate homelands.

May God bless you Professor Mesfin. May he grant you more healthy days so that we learn the truth from you!

May also God our beloved Ethiopia!

God Bless the Heroic Professor...we also ask God to bless crazy and racists like Hordofaa ! Because, people like Hordofaa are driven by the poisonous woyane agenda. The regime has to be hled responsible for pushing these people to the edge. It is also true that our best minds and heroes have been chased, jailed, murdered or harassed to shut their mouth by woyane...!! Where are our youth, where is our courage, where is our spirit from 2005..??? Don´t you think it is time we question ourselves for all the failures...this is a critical time in Ethiopia´s history. GOD WILL NEVER LEAVE ETHIOPIA, it is true prof...!

Add new comment

Filtered HTML

  • Web page addresses and e-mail addresses turn into links automatically.
  • Allowed HTML tags: <a> <em> <strong> <cite> <blockquote> <code> <ul> <ol> <li> <dl> <dt> <dd>
  • Lines and paragraphs break automatically.

Plain text

  • No HTML tags allowed.
  • Web page addresses and e-mail addresses turn into links automatically.
  • Lines and paragraphs break automatically.