ፍትህ በጫና እና በማስፈራሪያ የሚዝሉ ክንዶች፤የሚሰደዱ እግሮች የሏትም!
አሁን አደገኛ ሁኔታ ላይ ተደርሷል፡፡ ፍትህን ወደ መቃብር ለመክተት በተቀናጀ እና በተደራጀ መልኩ የሚሴረው ሴራ እና የሚሸረበው ተንኮል ስጋና ደም ለብሶ እነሆ ከበር ቆሟል፡፡ ከዕሮብ (11/04/04) ጀምሮ በጋዜጣው ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ፤እንዲሁም በአዘጋጆቹ ሙሉነህ አያሌው እና ኃይለመስቀል በሸዋምየለህ ላይ መፈናፈኛ የሚያሳጣ ክትትል እየተደረገ ሲሆን፣ ይሄ ርዕሰ አንቀጽ እየተዘጋጀም (13/04/04) የጋዜጣው ቢሮ በክትትል ቀለበት ውስጥ እንደሆነ ነው፡፡
በዚህም የተነሳ የመስራት ነፃነትን ብቻ ሳይሆን የመተንፈስ ነፃነትንም በሚያፍን መልክ በአዘጋጆቹ ላይ እየተደረገ ያለው ጫና ፍፁም ህገወጥ እንደሆነ ለማስገንዘብ እንፈልጋለን፡፡እናም እነዚህ የደህንነት ሰራተኞች በጠራራ ፀሐይ የዜጐችን የመዘዋወር እና በነፃ የማሰብ ህገ መንግስታዊ መብት እንዲያፍኑ የላካቸው አካል ህገ-መንግስቱን እየናደው እንደሆነ ህዝብ ሊያውቀው ይገባል፡፡ እነዚህ ሰዎች የጋዜጠኛ ኃይለመስቀልን ሲም ካርድ በነጠቁበት ጊዜ የደህንነት ሰራተኞች እንደሆኑ ቃል በቃል ከነገሩት በኋላ ከባድ ማስፈራሪያ ከተከበረው የጋዜጣው ቢሮ በር ላይ አድርሰውበታል፡፡
በፍትሕ እምነት ይሄ ሀገር የእናነት /የገዥዎቻችን/ እንደሆነ ሁሉ፤ የእኛም ነው፡፡ በእንደዚህ አይነቱ የደህንነት ጫና እና ማስፈራሪያ የምንለውጠው አቋምም ሆነ የምንሰደድበት ሀገር የለም፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ ነችና፡፡ ደግመን ደጋግመን እንደምንለው፤ ዛሬም እንላለን በወከባ እና በማስፈራሪያ በሀገሪቱ ቁጥር አንድ ተነባቢ የሆነችው ፍትህ ጋዜጣ የሚያጎነብስ አንገት እንዲኖራት አንፈቅድም፡፡ ለስደት የተዘጋጀ ልብ የላታም፡፡ ምንጊዜም የህዝብ ድምጽ፣ የህዝብ አንደበት እንደሆነች ትቀጥላለች፡፡ ከዚህ በተረፈ አፋኙን የፕሬስ ህግ ጨምሮ የተለያዩ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ስላለ፣ ጥፋት ካለ በህግ መጠየቅ እንጂ፤ ለሀገር ደህንነት እና የህዝባችንን (እኛን ጨምሮ) ሰላም ለመጠበቅ የሰለጠኑ የደህንነት ሰራተኞች አላስወጣ አላስገባ እንዲሉን እንዲያደርጉ ማሠማራቱ ዛሬ ምናአልባት ሰማይ አይታረስ… ቢሆን እንኳ ነገ በህግ ያስጠይቃል፡፡ይህንንም ከታሪክ መማር ብልህነት እንደሆነ በዚህ ስራ የተሳተፋችው ሁሉ እንድትገነዘቡት አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
እንደሚታወቀው ፍትህ በወጣቶች የምትዘጋጅ ጋዜጣ ነች፡፡ በተቃራኒው ደግሞ በእድሜ ከእኛ ጋር የሚቀራረቡ ወንድም እና እህቶቻችን (የደህንነት ሠራተኞች) ትእዛዝ እየሰጣችሁ ስራችንን እንዳንሰራ እንቅፋት መፍጠሩ፤ ጉዳቱ ለሀገርም ጭምር ነው፡፡ የሆነ ሆኖ ግን በእነዚህ የእድሜ አቻዎቻችን ላይ አንዳች ቅሬታ የለንም፡፡ ቅሬታችን ለሀገር ጥቅም ሊውሉ የሚገባቸውን የደህንነት ሰራተኞች ሰላማዊ ዜጐችን እንዲያፍኑና እንዲያሰፈራሩ በመደቡት ላይ ነው፡፡ ይህ በይጊዜው ታገልንለት፣ ተሰዋንለት የምትሉትን ህግ-መንግስት መናድ ነው፡፡ ግልፅና አደገኛ ወንጀል እንደሆነ ልታውቁት ይገባል፡፡
ከዚህ ውጪ የመጣውን መከራ ለፕሬስ ህልውና ስንል እስከመጨረሻው እንቀበለዋለን፡፡ በእርግጥ ይሄ የእኛ የአለማ ፅናት ነው፡፡ ነገር ግን ቀጣዩ ጊዜ አስፈሪ እና አደገኛ ሊሆን እንደሚችል ይገባናል፡፡ ሆኖም ባመንበት አላማ ላይ ቆመን የመጣውን ከመቀበል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደማይኖረን ለመንግስት፣ ለህዝብ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት ፍትህን በኢትዮጵያ ከሚገኙ የፕሬስ ውጤቶች በህትመት ብዛት አንደኛ ትሆን ዘንድ ላደረጉ አንባቢዎቻችን ግልፅ ማድረጉ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ እናም የፍትህ አንገት በአቋም ለውጥ ሊቀለበስ እንደማይችል እና ለስደት የተዘጋጁ እግሮች እንደሌሏት ዛሬም ደግመን ደጋግመን እናረጋግጥላችኋለን፡፡

Comments
Kinfe (not verified)
Sun, 12/25/2011 - 18:12
Permalink
Ayzon
I understand what is going on, it is so worrisome and disdaining. Ayzon!! Let God be with you. Keep up the good work.
elsa (not verified)
Sun, 12/25/2011 - 19:59
Permalink
Ayzon
Ayzon tem
ኮራሁባችሁ (not verified)
Sun, 12/25/2011 - 21:28
Permalink
You and your friends are a
You and your friends are a shooting star for our country. You just lighten the sky once in a while. በርታ::
abebe (not verified)
Mon, 12/26/2011 - 00:28
Permalink
great job
when I read the challnges you are passing through and patraiotic articles, I just proud of you. I did not know that this country has such patriots till now. you are making history. The rulers could force you close the paper and exile . God be with you!
kuraz (not verified)
Mon, 12/26/2011 - 02:49
Permalink
BERTA
Hulme yalfal< berta yagerlege>...good work thanks.
krazu (not verified)
Mon, 12/26/2011 - 02:53
Permalink
berta
hulum yalfal good work thanks !!!
justice 4 all (not verified)
Mon, 12/26/2011 - 05:00
Permalink
ለፍትህ አዘጋጆች በሙሉ ለናንተ ያለኝን ልባዊ
ለፍትህ አዘጋጆች በሙሉ ለናንተ ያለኝን ልባዊ ክብር ለመግለጽ እወዳለሁ
በመቀጠል በምታስነብቡን ሚዛናዊ ዜና ከሆድ አደሮች ለሚደርስባችሁ ዛቻና
ማስፈራሪያ ምን ጊዜም ቢሆን ፍትህ ያጣው የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎናችሁ
እንደሚቆም ላፍታም ቢሆን አትጠራጠሩ,,,የኢትዮጵያ ህዝብ ስለ ፍትህ
ብሎ በነቂስ የሚወጣበት ጊዜና ሰዓቱ ደርሷል,,,በርቱ,,,
እግዚዓብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ
tt (not verified)
Mon, 12/26/2011 - 10:18
Permalink
አይዟችሁ!!
አይዟችሁ!!
we (not verified)
Mon, 12/26/2011 - 12:43
Permalink
love
Ayzowachew yehe yetigile baherywe new ye dekiki Estfanosene ena YeEskinder Negane mekerana tegisti asibu BAndirawene Terekibachewalena Bertu,
Ewedachewa lew
100 birr (not verified)
Mon, 12/26/2011 - 12:59
Permalink
Ante becha?
ante becha sathon egnam abren engafetalen le sedet yemihon egir yelenim !!!
kibatu (not verified)
Mon, 12/26/2011 - 19:07
Permalink
be
ayzogn feteh kegonachuh nen
anonymus (not verified)
Mon, 12/26/2011 - 19:11
Permalink
Please don't give up my
Please don't give up my brothers and sisters! for me, Feteh is the top, among the other few 'independent' ones, well articulated and so balanced newspaper! this tyrrant junata is doing everything to survive. I know you are having a very difficult time these days, especially. Please stay strong. You are making an Erasable history! God bless you!
netsanet (not verified)
Mon, 12/26/2011 - 22:04
Permalink
ጀግና
እናንተ ጀግና ናችዉ በቃ
Anonymous (not verified)
Tue, 12/27/2011 - 01:33
Permalink
We Ethiopians are with you !
We Ethiopians are with you !!
Anonymous (not verified)
Tue, 12/27/2011 - 09:39
Permalink
Ayizoa'chu and lenatu yehonen
Ayizoa'chu and lenatu yehonen press medegef gidetachin new. Sinaneb enkuan mesakek bejemernibet bezih seat yenante tinikare-koranibachu
ለሜሳ (not verified)
Tue, 12/27/2011 - 10:36
Permalink
አታሹፉ
ዝም ብላችሁ አታካብዱ
ኢትዮጵያዊ (not verified)
Wed, 12/28/2011 - 12:01
Permalink
ጽኑ
የእናንተ ጽናት በዚህ ትውልድ ልቡና ለዘላለም ይዘከራል፡፡
Anteneh (not verified)
Thu, 12/29/2011 - 14:05
Permalink
don't give up the mass is with you
I think EPRDF is making mistake because they may close fetehe but that will not end their mission rather it inspires many to write and disclose the downsides of EPRDF as a government. brothers and sisters don't hesitate to write as you were doing till this day. you are patriots. don't never ever give up, the mass is with you.
God bless you!!!
Reply (not verified)
Thu, 12/29/2011 - 20:01
Permalink
Enanetem
Enanetem tesedachehu ye addis zemen ena ye etv mekeleja endatadergwn bertw beakuamachehw senw!
Add new comment