ልማትና ጥፋት

ባለፈው ጊዜ ስለመሬት ያልሁትን በልማት ልቋጨው፤ የፋሺስት ኢጣልያ አገልጋይ የነበሩት ከበደ ሚካኤል በታሪክና ምሳሌ ውስጥ አንዱን ጣልያን ሲያናግሩት
ኃይለኛ እየሄደ ያስገብራል የትም፤
መሬት የሁሉ ናት ባለቤት የላትም፡፡
ብሎላቸው ነበር፤ በዚህ የፋሺስት እምነት የመሬት ባለቤትነት በህገ አራዊት የሚወሰን ነበር፤ ሌላ ምንም ምክንያት የለውም፤ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን መሬት የኑሮአችን መሰረት ስልሆነ የመሬት ባለቤትነት ከአገር ባለቤትነት ጋር የተቆራኘ ነው፤ ስለዚህ ስለልማት ስንነጋገር መነሻ የጋራ ሀብታችንን መሬት መሆኑን እያሰብን ነው፡፡
ስለልማት ስናስብ አብዛኞቻችን በሶስት መሰረታዊ ነጥበሆ ላይ የምንስማማ ይመስለኛል፤ አንደኛ፣ ልማት ከጥፋት ይሻላል፤ ሁለተኛው ቁሞ-ቀር ሆኖ ከመደህየት ሰርቶ መበልጸግ ይሻላል፤ ሦስተኛ፣ የጋራ ንብረታችንንና የጋራ ዓላማችንን በጋራ ህግና ስርዓት ማስተናገድ ያስፈልገናል፡፡
ልማት ማለት ከአለንበት የማያስደስተን ሁኔታ ወደሌላ ወደሚያስደስተን ሁኔታ የሚወስድ ለውጥ ነው፤ ይህም አዲሱ ሁኔታ ከበፊቱ ሁኔታ የተሻለ ሆኖ መገኘት አለበት ማለት ነው፤ በኢጣልያ ወረራ ዘመን በጊዜው የነበሩ ጥሩ ቤቶች ለኢጣልያ ሹማምንት ይደለደሉ ነበር፤ ለባለቤቶቹ ለኢትዮጵያውያኑ በሜርካቶ ኢንዲጂኖ (የአገሬው ገበያ) በተባለው ሰፈር በእንጨትና በጭቃ በቤቶችን ሰርተው ቤታቸው የተወሰደባቸውን እዚያ ያስገቡዋቸው ነበር፤ ኢጣልያኖቹ ከነበሩበት ሁኔታ ወደተሻለ ሁኔታ ስለገቡ ለእንሱ ልማት ሲሆን፣ ኢትዮጵያውያኑ ከነበሩበት ሁኔታ ወደከፋ ሁኔታ ስለገቡ ለእነነሱ ጥፋት ነው፤ ልማት አንዱን ወይም ጥቂቶቹን ለማልማት ወይም ለማበልጸግ የብዙዎቹን ኑሮ ማቆርቆዝ አይደለም፤ ይህ ጥፋት ይሆናል፡፡
ለውጥ ብቻም ልማት አይሆንም፤ ጥፋትም ለውጥ ነውና፤ ልማት የሚሆነው ማንንም ሳይጎዳ የኑሮን ደረጃ ከፍ ማድረግ ብቻም አይደለም፤ ከፍ አድርጎ ለመሻሻል ሁሌም የሚንቀሳቀስና እያደገ የሚሄድ መሆኑንም ማረጋገጥ ነው፤ በትእዛዝ ብቻ የመጣ ቆሞ-ቀር ለውጥ ልማት የማይሆነውና ከርሞ ጥጃነትም የሚለመደው ከዚህ ነው፤ ልማት የእያንዳንዱን ሰው አካል ብቻ ሳይሆን አእምሮውንና ነፍሱን መንካትና ማጎልበት ያስፈልገዋል፤ ሰውን የማይነካ ሰማይ-ጠቀስ ግንበ ልማት አይሆንም፤ በመቀሌ አንድ ሽማግሌ የነገሩኝ ይህንን ያስረዳል፤ ‹‹ለዓይናችን ለመጀመሪያ ጊዜ ፎቅ አየን፤›› አሉኝ፤ እይሳቁ፣ ‹‹ታዲያ በማየት ምኞት ያድርብዎትና እርስዎም ፎቅ ይሠሩ ይሆናል›› ስላቸው፣ ‹‹ዋይ! ዋይ! ይኸ ክፉ ምኞት ነው!›› አሉኝና አስረዱኝ፤ ፎቁን ከጉልበት ጋር አያይዘውት በዓይናቸው እያዩ ከማድነቅ በቀር ለመመኘትም አቅም እንደሌላቸው አምነዋል፤ ለእኚህ ሰው የሚያደንቁት ፎቅ ልማት አይደለም፤ አንድ የእንግሊዝ ደራሲ ‹‹የመኪና እርገት የሰው ልጅ ውድቀት›› ያለው ዓይነት ነው፡፡
ልማትም ልክ እንደደሀነት ማኀበራዊ ነው፤ ይህንን ገና ያልተገነዘቡ ሰዎች ደሀነትን እናጠፋለን ሲሉ የሚያሳዝን ቢሆንም ያስቃል፤ ከዚህ በፊት በግጥም እንዳልሁት..
ደሀነት ባለም ላይ ጭራሽ ባይፈጠር፣
ጌትነት ምን በልቶ ይጠበድል ነበር!

ጌትነትን በማጠብደል ደሀነትን የሚያጠፉ እየመሰላቸው ይለፋሉ፤ አንድ ህዝብ በጋራ ዓላማና በጋራ ሕግ እየተመራ በጋራ ንብረቱ የሚጠቀም ከሆነ የሀብት መበላለጡን አልፎ በደሀና በሀብታም መሀከል የሰፋ ልዩነት ከየት መጣ? ሥልጣንና ጌትነት ሲጋቡ ደሀነት ይስፋፋል እንጂ አይቀንስም፤ እንዴት ብሎ! እስቲ አስቡት፤ አንድ ትልቅ ሕንፃ ሲሠራ ስንት ሰዎች ደሀ ይሆናሉ? እስቲ አስቡት አንድ ኪሎ ሜትር መንገድ ሲሠራ ስንት ሰዎች ደሀ ይሆናሉ?
እንግዲህ ጥያቄው ልማት ሁሉንም ለማልማት ባይችልም ማንንም ሳያደኸይ ሊከናወን ይቻላል ወይ ነው፤ ቅን መንፈስ ካለ ይቻላል፤ ከጥቂት ዓመታት በፊት በአዲስ አበባ ውስጥ ትንንሽ ጎጆ ውስጥ የሚኖሩ ደሀዎች የያዙት መሬት ብዙ መቶ ሺህ ብር እንደሚያወጣ አያውቁም ነበር፤ በሀብት ላይ ተቀምጠው በደሀነት ይኖሩ ነበር፤ እነዚህ ሰዎች የባሰ ደሀነት ውስጥ ሳያስገቡ፣ ወይም እነዚህን ደሀዎች ከሀብታቸው ለመንቀል አዋጅ ሳያወጡ መፍትሔ ማግኘት ይቻል ነበር፤ በደርግ ዘመን አቶ አላሙዲን ሸራተን የተሰራበትን መሬት ያገኘበት መንገድ አንድ ነው፤ ከዚያም የተሻለ ዘዴ ያለ ይመስለኛል፤ ገንዘብ ያላቸው ሀብታሞች መሬት ሲፈልጉ ማዘጋጃ ቤቱ ከደሀዎቹ የመሬት ባለቤቶች ጋር ያገናኛቸዋል፤ የደሀዎቹ መብቶች ሁሉ የሚጠበቁበትን ሁኔታ፣ ሕግንና ሥርዓትን ያመቻቻል፤ ሽያጩን ያስፈጽመማል፤ የአገልግሎቱንና የደላላነቱን ዋጋ ከሁለቱም ይቀበላል፤ መንግስት በሕግም ሆነ ከሕግ ውጭ ሳይቀማ፣ ደሀነትን ሳያስፋፋ፣ ለሙስና በሩን ሳይከፍት ሀብታሙም በሀብቱ እንዲለማና ያለሥጋት እንዲሠራ፣ ደሀውም ዋጋውን አግኝቶ ባለው እንዲንቀሳቀስና ኑሮውን እንዲያሻሽል የሚያደርጉበትን ሁኔታ መፍጠር የሚቻል ይመስለኛል፡፡
ሀብታሙንና ደሀውን በቅራኔ ሳያጣምዱ፣ ሀብታሙን ለሁልጊዜ ስጋት ሳይዳርጉ፣ ደሀውን በቂምና በጥላቻ ሌላ መንግሥቱ ኃይለ ማርያምን እንዲጠብቅ ሳይገፋፉ ልማትን ያለጥፋት ለሀብታሙም ለደሀውም ማምጣት ይቻላል፤ በቅሚያና በሙስና የተገነባ ጥፋት እንጂ ልማት አይሆንም፡፡

Comments

Good

Professor Mesfin is a national treasure.

መሰጠት !!!
ውልህን አታፍርስ ……….ክፉም ሆነ ደግ
ምስክር ይሆናል…………. እውነት ሲፈለግ ፤
መሰጠት እንዲህ ነው
መኖር ማለት እውነት……እውነት ማለት ሞት፤
ጊዜ ሲወራረድ …………...ቆሞ መገኘት ፤
ጥር 15 2004

I ought to appear into this and it would be a difficult job to go more than this completely here.

vimax Vimax vimax

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ፈጣሪ ዕድሜና ጤና ይስጥዎት!የአደባባይ ምሁር ነዎት እንኮራብዎታለን!!!

Add new comment

Filtered HTML

  • Web page addresses and e-mail addresses turn into links automatically.
  • Allowed HTML tags: <a> <em> <strong> <cite> <blockquote> <code> <ul> <ol> <li> <dl> <dt> <dd>
  • Lines and paragraphs break automatically.

Plain text

  • No HTML tags allowed.
  • Web page addresses and e-mail addresses turn into links automatically.
  • Lines and paragraphs break automatically.