Add new comment

ዉድ ተመስገን እንደምን አለህ ? የፍትህ መንገድ በማለት ፍትህ፣ ነጻነትና ዲሞክራሲ ለሚናፍቀዉ ህዝባችን የጻፍካትን መጣጥፍ አንብቤ በጣሙን ተደስቻለሁ ። አባባልህ በሙሉ አሳማኝና ግልጽ ነዉ ። ዛሬ በትዉልዳችን መካከል የተከሰተዉን ሁነኛ ባህሪይ ተገንዝበህ ጨመቅ ጠበቅ በማድረግ የሰጠኸዉ አስተያየት እያንዳንዳችንን አጥንታችን ድረስ ዘልቆ በመግባት የሚቆረቁርና እንቅልፍ የሚነሳ መሆኑን እንገነዘባለን ። ግን አንድ ነገር በያንዳንዳችን ዉስጥ እንደሚጎድለን በራሴ በኩል በጉልህ ይታየኛል ያን የሚጎድለንን ነገር መሙላት ደግሞ ከማንም ሊሰጥ የሚችል ወይም እንደ ዕቃ ገዝተን የምናሟላዉ ወይም የምናመጣዉ ነገር አይደለም ። ይህን ነገር ደግሞ መሙላት የራሳችን ፋንታ ወይም ድርሻ ብቻ ነዉ ። ስለዚህ ማንም ሰዉ ለራሱ አንድ ጥያቄ በማቅረብ ይህን የሚግድለንን ነገር በማወቅ ለሱም መልስ በመስጠት እራሱን ማዘጋጀት ካልቻለ አሁን የጀመረዉ ወደፊትም እየቀጠለ የዘላለም ተወቃሽ እየሆንን መሄዳችን የማይቀር ስለሆነ ይህን አዉቀን ካሁነ እንዘጋጅ እናንተም በሙያችሁ ህዝብና ሀገራችን የጣለባችሁን የማበረታታት መስመር የመምራት ሀላፍነታችሁንና ይህን የያዛችሁትን ወኔ አደራ ባለመተዉ ወደፊት በአንድነት ተያይዘን ለምንመኘዉና ለምናስበዉ ግብ እንደምንበቃ የኔም ምኞት ነው ። ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይርዳት ለኛም ልቦናንና ብርታትን ይስጠን አሜን !!!

Filtered HTML

  • Web page addresses and e-mail addresses turn into links automatically.
  • Allowed HTML tags: <a> <em> <strong> <cite> <blockquote> <code> <ul> <ol> <li> <dl> <dt> <dd>
  • Lines and paragraphs break automatically.

Plain text

  • No HTML tags allowed.
  • Web page addresses and e-mail addresses turn into links automatically.
  • Lines and paragraphs break automatically.