Add new comment

ፕሮፌሰር መስፍን ባሉት እስማማለሁ። ውርደቱ ለጠ/ሚ መለስ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያና ለሕዝቦቿ ጭምር ነው። የጋዜጠኛ አበበም አድራጎት የብሶቱን መጠን ይገልጻል። የተሰደደበትን ምክንያት ያውቃል፤ በገዛ አገሩ ድምፁን መነጠቁ ያስከተለበትን ምሬት ያውቃል። በፕሮፌሰር አሳብ ላይ የምጨምረው አለኝ። በ1928 አፄ ኃይለ ሥላሴ በተባበሩት መንግሥታት ንግግር ሲያደርጉ የፋሺስቶች ጩኸት አንገት ያላስደፋቸው ምክንያቱ የኢትዮጵያን ሕዝብ ወክለው፣ እውነትን ይዘው በአምላክና በዓለም ሕዝብ ፊት ፍትሕ ይጠየቁ ስለነበረ ነው። እንዲያውም በሚያስፈራና በሚያኮራ ግርማ ነበር የቆሙት። ሊያሳፍሯቸው የመጡ ይልቅ አፈሩበት። ንጉሡ አጀማመራቸው መልካም እንደነበረ አንርሳ። የፕሬዚዳንት ኢሳይያስ እንኳ እዚህ ሊጠቀስም አይገባም። ያኔም ሆነ ዛሬ ከኤርትራውያን የሚታየው እያዩ እውነቱን መካድ ነው። ፈረንጆች "ግሩፕ ቲንክ" የሚሉት ነው። እና፣ ከኢትዮጵያ ሁናቴ ጋር ብዙ ማነጻጸር አይቻልም። አንድ የሚያመሳስለን ነገር ቢኖር ኢሳይያስና መለስ ሁለቱም በሕዝብ ምርጫ ሳይሆን በነበረው የሽግግር ሁናቴ ሥልጣን የያዙ መሆናቸው ነው። መለስ ግልጽ እንዳደረጉልን ከርሳቸውና ከፓርቲአቸው ወይም እርሳቸው ከሚሾሙት ውጭ ምርጫ እንደሌለን ነው። ሌላ የሚገርመው፣ በጥር ወር በተመረቀው የአፍሪካ ኅብረት ማእከል አፄ ኃይለ ሥላሴ ለአፍሪካ ስላበረከቱት አስተዋጽዖ መታሰቢያ እንዳያገኙ በጽኑ የተከራከሩት ጠ/ሚ መለስ ናቸው። አፍሪካውያን ግር እስከሚላቸው ድረስ ንጉሡን አንቋሸሿቸው፤ ክብር እንዲነፈጋቸው በጣም ታገሉ። የንጉሡ መከበር የሁላችንም [መለስን ጨምሮ] ክብር ሊሆን ሲችል። መለስ፣ እኛንም በሕዝብና በአገር ደረጃ ክብር ነሡን። ታሪክ ግን የ1928ቱን በደል እንደካሰን ሁሉ ወደፊት ጠ/ሚ መለስ በሌሉበት በሌላ ትውልድ ይክሰናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። መለስ ይህን ባደረጉ በጥቂት ወራት ውስጥ የዓለም መሪዎች በተገኙበት በርሳቸው ላይ መድረሱ እጅግ የሚገርም ነው፤ የሚያስፈራም ነው። ልብ ላለው ልብ የሚያስገዛ ነው።

Filtered HTML

  • Web page addresses and e-mail addresses turn into links automatically.
  • Allowed HTML tags: <a> <em> <strong> <cite> <blockquote> <code> <ul> <ol> <li> <dl> <dt> <dd>
  • Lines and paragraphs break automatically.

Plain text

  • No HTML tags allowed.
  • Web page addresses and e-mail addresses turn into links automatically.
  • Lines and paragraphs break automatically.