Add new comment

ተመስገን፣
ካለንበት፡ወቅት፡በመነሳት፡ያደረግኸው፡እይታ፡ከብዙ፡አንጻር፡ለመወያየት፡ይጠቅማል፡፡
አሳብህ፡ሁሉ፡ለኢትዮጵያ፡በጎ፡እንደሆነ፡ግልጽ፡ነው።
ስለ፡ወታደራዊው፡የመጨረሻው፡አንቀጽህ፡ብዙም፡ስላላልክበት፡ተዳፍኖ፡ቀርቷል።ሊከሰቱ፡
የሚችሉትን፡ሁኔታዎች፡በሙሉ፡ለመተንበይ፡አዳጋች፡ነው።የ"ሊሆን፡ይችላል"አስተሳሰብንም፡ከመላ፡ምት፡አነጋገር፡በላይ፡አድርጎ፡መውሰድ፡ያስቸግራል።

የኢትዮጵያና፡የሕዝቧ፡የወደፊት፡በአርቆ፡አሳቢዎችና፡በእርቀ፤እግዚአብሔር፡በሚያምኑ፡እስካልሆነ፡ድረስ፣ውጤቱ፡በስልጣን፡ታሻሚዎች፡መካከል፡ለኢትዮጵያና፡ለሕዝቧም፡በማይበጅ፡መንገድ፡የሚወሰን፡ይሆናል።

"የሸዋ፡ፓለቲካ"ያልከውን፡ባለፉት፡ሃያ፡አንድ፡ዓመታት፡ውስጥ፡ኢትዮጵያ፡ውስጥ፡ከተከሰተው፡ዓይን፡ያወጣ፡የጎሣ፡እና፡የመንደር፡ፖለቲካ፡ጋር፡ለማዛመድ፡ወይም፡ለማነፃፀር፡መሞከር፡ስህተት፡ነው።ከአፄ፡ምኒሊክ፡በኋላም፡የነበረው፡ፖለቲካ፡ከምኒሊክ፡ሸዌነት፡በስተቀር፣ኢትዮጵያዊ፡ፖለቲካ፡እንጂ፡"የሸዋ፡ፖለቲካ"ሊያስኘውስ፡የሚችለው፡ከምን፡ማስረጃ፡በመነሳት፡ነው?ራስ፡ጎበና፡ዳጬ፣ፊትአውራሪ፡ኃብተ፡ጊዮርጊስ፣ደጃች፡ባልቻና፡ሌሎችም፡ምኒሊካዊ፡የኢትዮጵያ፡ፖለቲካ፡ታሪክ፡አዕማዶች፡እናስትውስ።ለወሬና፡ለጥላቻ፡ተረቶች፡አንበገር!

በኢትዮጵያ፡አንድነት፡ላይ፡የጸኑ፡የታሪክ፡እውነታዎቻች፡ሊዘነጉ፡አይገባም፡፡ማንም"ሊለውጣቸው"አይችልም!እስከዛሬም፡ተሞክሮ፡ያልተሳካው፡ይኸው፡ክህደት፡ነው።ወደፊትም፡አይሳካም!ታሪካዊ፡እስነታዎቻችንና፡አለኝታዎቻችን፡የኛነታችን፡መስታወቶች፡ሆነው፡ይኖራሉ!!!ለጊዜ፡ፈጠርና፡ፀረ-ሸዋ፡አሻሚ፡ንግግር፡ሲባል፡እንዳልነበሩ፡ሊገፉም፡አይገባም።

ሸዋ፡ላይ፡ብዙ፡ሐሰትና፡ጥላቻ፡ስለተነዛ፡እንደውነት፡ተቆጥሮ፡ከማይመሳሰለውው፡አውዳሚ፡ታሪክ፡ጋር፡ማነፃፀሪያ፡አድርጎ፡ማቅረቡስ፡ለምን፡አስፈለገ?ያለንበትን፡ወቅታዊና፡በሃያ፡አንዱን፡ዓመታት፡የጎሣ፡አገዛዝ፡ሥርዓት፡የደረሱብንን፡ለመግለጽ፡የማይገባ፣ጥንት፡ከነበረው፡የአገራችን፡ሥርዓት፡ጋር፡አንዳችም፡ተመሳሳይነት፡ወይም፡ተዛምዶ፡የሌለውን፡የጎሣ፡ሥርዓት፡የወደፊት፡መተንበያነት፡መቅረብ፡የማይገባው፡አስተሳሰብ፡ነው።

ዛሬ፡በስልጣን፡ታሻሚ፡የጎሣ፡አገዛዝ፡ሥርዓት፡ውስጥ፡ስለምንገኝ፣የዚህን፡ከኢትዮጵያ፡ታሪክ፡ውጭ፡የሆነ፡ክስተት፡በራሱ፡ተለምዶና፡ተሞክሮ፡መመዘንና፡ማነፃፀር፡ይበልጡን፡ሊረዳ፡ይችላል።

ስለ፡"ሸዋ፡ፖለቲካ"መነጋገር፡አስፈላጊ፡ከሆነ።ከአድዋ፡እስከ፡ማይጨው፡ጦርነቶች፡ድረስ፡የሸዋን፡ለጠላት፡አልገዛም፡ባይነት፣የእኛ፡ሰው፡ያለውን፡ሳይሆን፡ጣልያኖች፡ያሉትንና፡የጻፉትን፡እየጠርቀስን፡መነጋገር፡እንችላለን።ያን፡ግን፡እርግጠኛውና፡ጠላት፡አይገዛንም፡ባዩ፡ኢትዮጵያዊው፡የ"ሸዋ፡ፖለቲካ"ብሎ"መናገር፡ይቻላል።

የዛሬውን፡ፖለቲካ፡ባይሆን፡በደደቢት፡እንጂ፡በሸዋ፡መመንዘር፡አይቻልም።የ"ደደቢትን፡ፖለቲካ"የወደፊት፣በማይገባው፡"የሸዋ፡ፖለቲካ"፡ተምሳሌት፡መመዝንና፡ማየት፡አይቻልም!!!

የሸዋ፡ፖለቲካ፡መሠረት፡ኢትዮጵያ፡ስትሆን፣የደደቢት፡ግን፡ኢትዮጵያን፡የመገንጠልና፡የማስገንጠል፡መሆኑን፡አንቀጽ፡39ን፡የቸሩን፡ገዢዎቻችን፡ባደባባይ፡ስለነገሩን፡ሁላችንም፡የምናውቀው፡ነው።

እግዚአብሔር፡ኢትዮጵያንና፡ልጆቿን፡ከታለመለን፡ጥፋት፡ሁሉ፡ያድነን።አሜን።

ገብርዬ፡ዘብሔረ፡ኢትዮጵያ።

Filtered HTML

  • Web page addresses and e-mail addresses turn into links automatically.
  • Allowed HTML tags: <a> <em> <strong> <cite> <blockquote> <code> <ul> <ol> <li> <dl> <dt> <dd>
  • Lines and paragraphs break automatically.

Plain text

  • No HTML tags allowed.
  • Web page addresses and e-mail addresses turn into links automatically.
  • Lines and paragraphs break automatically.