ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ እና ፊሊጶስ
Submitted by Admin on Tue, 08/30/2011 - 13:01ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ እና ፊሊጶስ
(ገጽ 16 ቅፅ 4 ቁጥር 150 አርብ 20 ነሐሴ 2003ዓ.ም)
ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ እና ፊሊጶስ
(ገጽ 16 ቅፅ 4 ቁጥር 150 አርብ 20 ነሐሴ 2003ዓ.ም)
አቤ ቶኪቻው ( abeto2007@yahoo.com )
ወዳጄ እንዴት ሰነበቱልኝ? ሰላም እንኳን ሳልልዎ በወሬ ጠምጄ ያዝኩዎት አይደል እንዴ? ይቅርታ ይደረግልኝ! እኔ የምለው “ቡሄ ካለፈ የለም ክረምት!” የሚለው አባባል ቀረ እንዴ? ይኸው እኛ አባባሉን አክብረን በቲሸርት እየወጣን ስንት ጊዜ ተሸወድን እኮ!
ሌላ የተረሳ ነገር ክርስቲያን ወዳጆቼ እንኳን ፆመ ሉጋሙን ፈጻላችሁ! አንድ ወዳጄን እንዲህ ብዬ መልካም ምኞቴን ብገልጽለት እስቲ ተወኝ ሲል ፊቱን ኮሶ አስመስሎ ተኮሳተረብኝ! እኔ ደግሞ ምን ባስቀይመው ነው እንኳን አደረሰህ ባልኩት ፊት የሚነሳኝ ብዬ ስጨነቅልዎ ለካስ ወዳጄ በማጣት የተነሳ ፆሙን አራዝሞት ኖሯል... “እኔ አሁንም ከሙስሊም ወዳጆቼ ጋር ደግሞ ሣየፆምኩ ነው!” አለኝ፡፡ አዬ ጉድህ ረመዳን ሲፈታ ደግሞ በምን ሰበብ ትፆም ይሆን? ብዬ ብለው “የርሃብ አድማ አደርጋለና” አለኝ!. እውነት ግን ለሀገራችን መልካም ገጽታ ሲባል የሀይማኖት አባቶቻችን አመቱን ሙሉ ፆም ነው ብለው ቢያውጁልንና ምግቡ ከጠፋ አይቀር በፆም ሰበብ ሳንበላ ብንውል መልካም ነበር!
ገብሩ ታረቀ (ፕሮፌሰር)
ሰላምታየን ላስቀድምና በፍትሕ ጋዜጣ ነሐሴ 6 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም. “ንግግራችን ትርፋማ እንዲሆን ከአሉባልታ እንውጣ” በሚል ርዕስ ያቀረቡትን ጽሑፍ በአንክሮ አንብቤ (በጊዜው ባይሆንም) አንድ ሁለት ጥያቄዎችን ለመሰንዘር ፈለግኩ፡፡ እንደመቅድም አድርጌ ግን የማይተኛና የማያስተኛ አዕምሮዎትን ብሎም ኃይለኛ ብዕርዎን ከሚያደንቅልዎት የቀድሞ ተማሪዎችዎ አንዱ መሆኔን እንዲያውቁልኝ እፈልጋለሁ፡፡
ከአሉባልታ እንውጣና በቁም ነገር አዘል ጉዳዮች ላይ እንወያይ በማለት የቸሩንን አስተምህሮት በአክብሮት ተቀብየዋለሁ፡፡ የፍትሕ አንባቢያንም እንደሚስማሙበት አልጠራጠርም፡፡ ነገር ግን በጽሑፉ ውስጥ አሳሳቢ ስህተቶችና ክፍተቶች መስለው ስለታዩኝ ነጥቦች ባጭሩ ላብራራ ይፈቀድልኝ፡፡
አቤ ቶኪቻው abeto2007@yahoo.com
“ኢህአዴግን ተቀበሉ! እንቢ ካላቹ ተዘጋጁ ለበቀሉ!” (ይቅርታ “ተዘጋጁ ለበቀሉ” የሚለውን ያልኩት የግጥም አዚም በላዬ ላይ ሰፎብኝ ነገሩ ቤት ስለመታልኝ ነው እንጂ ካድሬ እንዲህ አይልም!)
የሆነ ሆኖ ጊዜው የኢህአዴግ ነው! ኢህአዴግን ያሉ አዎ አያፍሩም! ኢህአዴግን ሲሉ ትምህርት ይገባል! ንግድ ይሳካል! በስራ እድገት በሴራ ሹመት ይገኛል! (ይቺ ይቺ እንኳን አሉባልታ ናት) የምግብ ፍላጎት ይከፈታል! የምግብ አቅርቦት ይሟላል! ደመና እንኳን ቢሆን ፀሐይ ይበራል! ምክንያቱ ግልፅ ነው! “ኢህአዴግ ጌዉ ነው! በቀረቡት ላይም በረከቱ የበዛ ነው!”
ዳኛቸው አሰፋ (ዶ/ር)
ይህንን ጽሁፍ ልጽፍ ስዘጋጅ አእምሮዬ ላይ የተመላለሰውና ያስደመመኝ ከጥንታዊ ግሪካዊያን ሚቲዎሎጂ ላይ የአነበብኩት ተረት ደብዳቤውን ለመጀመር እንደመንደርደሪያ ይሆናል ብዬ አመንኩ፡፡
ታላቁ የግሪክ ፀሐፊ ሂሶይድ (Hesoid) ‘Works and Days’ በሚለው መጣጥፉ ላይ አንድ በስርዓቱ የተከፋ ገበሬ እና ዛፍ ላይ ተቀምጣ ምክር በምትለግስ አሞራ መካከል የተካሄደውን ውይይት እንደሚከተለው ያቀርበዋል፡፡
"የልዑላኑ ነገር በጣም ጨነቀኝ፡፡ ፍርድ ያዛባሉ፣ ስጦታ ያግበሰብሳሉ፣ ጉቦ ይሰበስባሉ" እያለ ገበሬው እሮሮ ያቀርባል፡፡
መስፍን ወልደማርያም /ፕሮፌሰር/
ስብሓት ነጋ ስለወያኔ ድርጅት የሚናገረው እኛ ሃያ ዓመታት ሙሉ ከተከታተልነውና ከአወቅነው በፍፁም የተለየ ነው፡፡ ምናልባት እሱ ከፍ ብሎ ማማው ላይ ተቀምጦ የሚታየውና እኛ ታች ሆነን የሚታየን አይመሳሰልም ይሆናል፤ የምንሰማው ግን ጆሮአችንን ካልደፈንነው በቀር ሊለያይ አይችልም፤ ከወዲያ ማዶ እግዚአብሔር አቶ አስገደ ገብረ ስላሴ የሚባል ሰው አስነስቶ ያልተበረዘውን ደረቁን እውነት እንዲመሰክር እያደረገልን ነው፡፡ ስብሓት ነጋ ጥላሸት እንዳይቀባቸው እንጂ አንገፍግፎአቸው ከተሰደዱትም ምስክሮችን መጥራት ይቻላል፡፡ አቶ ስብሓት እናንተን ማየቱና እናንተን መስማቱ አቃተኝ ከአለ አቶ አስገደን ቢያዳምጥ እውነቱ ይገለጥለታል፡፡ ነገር ግን እውነቱ ቢገለጥለትም የማይቀበለው ከሆነ ለአክሱም ጽዮን እንሳልለታለን፡፡
ከጌታቸው ኃይሌ /ፕሮፌሰር/
ከዜናው ጋር ተያይዞ የመጣልኝ ቅድመ ሁኔታ ደስታዬን ከስሩ አናጋው፡፡ "የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመንግስት ድርጅት ስለሆነ መንግስትን የሚነቅፈውን የፕ/ር መስፍን ወልደማርያምን ቀዳሚ ቃል አብረን ለማሳተም አንችልም" የሚል ነበር፡፡ ያሳዘነኝ የመስፍን ድርሰት አብሮ አለመታተሙ አይደለም፡፡ የወያኔዎቹን በደል ለማጋለጥ ከሆነ መስፍን ኢሰመጉን አቋቁሞ ቀዳሚ ቃል ውስጥ ከጻፈው ይበልጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ አጋልጧቸዋል፡፡ ምክንያታችን የተለያየ ውስጥ ይሁን እንጂ መስፍንም ቁጭቱ ይሄ እንዳይደለ ገልጿል፡፡ እሱ ያዘነው ሽፈራውና እኔ ባላጠፋነው ጥፋት ነው፤ አኔን ያሳዘነኝ በመስፍን ፊታውራሪነት የተዋጋንለት የዩኒቨርስቲ የመጻፍና የመናገር ነፃነት እስከዛሬ የሰናፍጭ ቅንጣት እንኳን የምታህል ፍሬ አለማፍራቱ ነው፡፡ መስፍን ሽፈራውና እኔ ድርሰቱን የሸበብንበት አድርጎ ከመተርጐም ይልቅ መውቀስ የነበረበት ለዩኒቨርስቲው ነፃነት የነፈገውን መንግስት ነበር፡፡ ዳውላውን ሲፈልግ ተራጋጩ አህያው አመለጠው፡፡
አስራት አብርሃም (ከመቀሌ)
አቦይ ስብሓት የህወሓት አቋም የለሽነት ከሁኔታዎች እየተማረ የሚሄድ ድርጅት ስለሆነ ነው የሚል ምክንያት ይሰጡታል፡፡ የትግል ስልትና ስትራቴጂ እንደሁኔታው በአጭር ጊዜ ውስጥ መቀየር ይቻል ይሆናል፤ ተገቢ ነውም ዓላማ ግን እንደከተማ ልብስ በየዕለቱ የምትቀየረው ነገር አይደለም፡፡ ህወሓት ከትግል ዓላማ አንፃር ከየት ወዴት ይዘል እንደነበር የሚረሱት አይመስለኝም፡፡ ይህ ባህሪው ነው አንዳንዶቹ ዞሮ ዞሮ ዓላማው የነበረው ስልጣን መያዝ ነው ያን ግቡን ደግሞ መቷል የሚሉት፡፡
(ተመስገን ደሳለኝ)
Copyright © 2013,
Theme by Devsaran
