ተቀናቃኝ ቡድኖችና ፖለቲካ

ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም
በወያኔ/ኢሕአዴግ ዘመን አንድ የተለመደ አጉል ፈሊጥ አለ፤ በሆነ ባልሆነው ወያኔ/ኢሕአዴግን መውቀር ያስመሰግናል፤ በአንጻሩ በተቀናቃኝ ቡድኖች ወይ በመሪዎቻቸው ላይ ትችት ማቅረብ እንደክህደትና ከኢትዮጵያዊነት መስመር እንደመውጣት ይታያል፤ ይህ በተደጋጋሚ የታየ ነው፤ በቅንጅት መሪዎች መሀከል የነበረውን የስልጣን ሽኩቻ በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ስናገር በመጀመሪያ የራዲዮው ጠያቂ የነበረችው አነጋገሬን አልወደደችውም፤ የግል ስሜትዋን ለመግለጽ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ እንደገና ደውላ ተገቢ ያልሆነ ጥያቄ ጠየቀችኝ፤ ወሬው ከተላለፈ በኋላም ብዙ ሰዎች እየደወሉ ለብቻቸው ብታነጋግራቸውና ብትመክራቸው ይሻል ነበር በማለት የወቀሳ ትችት አቀረቡልኝ፤ እነዚህ ሰዎች የማከብራቸውና ሀሳባቸውን የማልንቅባቸው ናቸው፤ ለሁሉም የመለስሁላቸው እነሱ ለእኔ የሰነዘሩትን ምክር አንደኛ እኛ ሳናስብበትና ተግባራዊ ሳናደርገው ቀረን ብለው መገመታቸው የሚያሳዝን መሆኑን ነበር፤ ሁለተኛ ሁለትና ሶስት ወራት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ በተዋናውያኑ በራሳቸው እውነቱ ገሀድ እንደሚወጣ ነግሬአቸው ነበር፤

የፍትህ መንገድ-ከአሲምባ እስከ ቀራኒዮ

ተመስገን ደሳለኝ

የፍትህ ጉዞንም በእሾህ የተከበበ ያደረገው ይህ ነው። ለዚህም ነው ደግመን ደጋግመን ‹‹ጉዞአችን ቀራኒዮ›› ድረስ ነው ያልነው። በእርግጥ ላለመሰናከል መበርታት እንደአለብን ብናውቅም ቀራኒዮ ከዚህ ምን ያህል እንደሚርቅ ግን ማናችንም አናውቅም፤ ዛሬ ምሽት እንድረስ ወይም ነገ አሊያም የሚቀጥለው አመት የሚያውቀው ገዢው ፓርቲ ብቻ ነው። ምንም አይነት እርምጃ የመውሰድ ምርጫው በገዥው ፓርቲ እጅ ነው። አዎን! ውሳኔው በእጁ ነው። ወይ ፍትህን አጥፍቶ የሚመጣውን በፀጋ መቀበል፤ አሊያም የፍትህን ጎምዛዛ ሂስ ውጦ መታረም። ከዚህ በተጨማሪም ፍትህን መዝጋት አሊያም እንድትዘጋ በስውር መዳፍ መደፍጠጥ በኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ላይ የመጨረሻውን ሚስማር መምታት ነው፡፡ ሚስማር ደግሞ የሚፈነቅለው ነገር ሊኖር እንደሚችል ማወቁ ጠቃሚ ነው፡፡ እስከዛው ድረስ ግን እኛ እንፅፋለን።

Pages