የእስክንድር ነጋ ቃል

የተከበረው ፍ/ቤት ጥር 15 2004 እኔን 7ኛ ተከሳሽ እስክንድር ነጋን አስመልክቶ የሰጠው ብይን በ3 ይከፈላል፡፡ እነዚህም፡-
1ኛ. የአመፅ ተግባርን ለመፈፀም ከሚንቀሳቀሱ የሀገር ውስጥ ፓርቲ አመራሮች ጋር ስለጉዳዩ ተደጋጋሚ ስብሰባ ያደረግኩ መሆኔን፤
2ኛ. የተከበረው ፍ/ቤት የግንቦት 7 ልሳን ነው ብሎ ለጠረጠረው የኢትዮጵያ ሣተላይት ቴሌቪዥን የተለያዩ መረጃዎች የሰጠኹ መሆኔን፤
3ኛ. ሁከትን የሚቀሰቅሱ ፅሁፎችን የፃፍኩና ያሰራጨኹ መሆኔን የሚያስረዱ መረጃዎች እንደቀረቡብኝ የተከበረው ፍ/ቤት በይኗል፡፡
‹‹የአመፅ ተግባርን ለመፈፀም ከሚንቀሳቀሱ የሀገር ውስጥ ፓርቲ አመራሮች ጋር ስለጉዳዩ ተደጋጋሚ ስብሰባ አድርጓል›› ከተባልኹት ልጀምር

Pages