እንደንጉሡ አታጎንብሱ
እንደንጉሡ አታጎንብሱ
ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም
(ፍትህ እትም ቁጥር 176 አርብ የካቲት 16 2004 ዓ.ም)
መንግሥት ለሚባለው ድርጅት የመጨረሻው ተጠያቂ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ‹‹መንግሥት ሌቦች›› በአደባባይ ሲናገር ከሌቦች ጋር እየሠራ በመሆኑ እንድናዝንለት ነው? ወይስ ምን እንድናደርግ ነው? ሰዎቹን እንዳንቆጣለት ስማቸውን አልነገረንም፤ ከዚያም በላይ የሚያስፈራው ማፈኛ የሽብርተኛነት ክስ አለ፤ ሰሞኑን በኢንተርኔት የሚሰራጨው ወሬ ታላላቅ ባለሥልጣኖች የሚያሠሩዋቸው ስለተባሉት ታላላቅ ሕንፃዎች ነበር፤ ስደት ለወሬ ይመቻል እንደሚባለው አጉል ጉረምረም መስሎን ነበር፤ አሁን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አምርሮ ስለ‹‹መንግሥት ሌቦች›› የሰጠው ምስክርነት ወሬውን ያጠናክረዋል፡፡
ለመሆኑ ‹‹የመንግሥት ሌቦችን›› ጉዳይ ሊነግረን የሚገባው ማን ነበር? ፖሊሶቹ ‹‹የመንግሥት ሌቦች›› ከተባሉት ውስጥ ይኑሩበት አይኑሩበት የታወቀ ነገር ስለሌለ እንተዋቸው፤ ይህ ጉዳይ ምናልባት የጋዜጦች ዋና ሥራቸው ሊሆን ይችል ነበር፤ ግን በአሁኑ ጊዜ የመንግሥት ሌቦች እየበረከቱ ነው ብለው ቢጽፉ ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሌቦች አለቃ አደረጋችሁ ተብለው በሽብርተኛነት ይከሰሱና በማዕከላዊ በኩል ወደቃሊቲ ይጓዙ ነበር፤ አሁንስ ‹‹የመንግሥት ሌቦች›› ከተባሉት ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚከስና ራሱን ከሌብነት ነፃ ለማውጣት የሚከጅል ሰው ሳይኖር ይቀራል እንዴ? በደርግ ዘመን አንድ ጎረምሳ ሻምበል ሎሌ በዩኒቨርስቲ መጣና ፕሬዚደንቱ ዶ/ር ዱሪ መምህራን ሁሉ በራስ መኮንን አዳራሽ እንድንሰበሰብ አስደረገ፤ ካድሬው ተነሥቶ ትንሽ እየተውረገረገ ንግግር አደረገና አንዳንድ ጥያቄዎች ተነሡ፤ በጥያቄዎቹ ያልተደሰተው ካድሬ በራሱ ንግግር ሞቅ እያለው ሲሄድ ‹‹ዱሮውንም ይሄ ዩኒቨርስቲ የአድኃርያን መናኸሪያ መሆኑን እናውቃለን›› አለ፤ እኔ ተነሥቼ በዩኒቨርስቲ ውስጥ ያለው ሰው ቁጥርና በሕዝብ ድርጅት ውስጥ ያለው የሰው ቁጥር መጠን አድኃርያን የሚባሉትን ብናሰላ የአንተ ድርጅት የበለጠ የአድኃርያን መናኸሪያ ሳይሆን አይቀርም፤ ሁለተኛ በእውቀት የምትመራ ሰው ብትሆን ዩኒቨርስቲውን በአጠቃላይ የአድኃርያን መናኸሪያ ከማለት ስም እየጠራህ አድኃርያን የምትላቸውን ማጋለጥ ተግባርህ ነበር አልሁት፤ ተቀለበሰና ማድበስበስ ጀመረ፤ ዛሬስ ቢሆን ከመንግሥት ባለሥልጣኖች ውስጥ ‹‹የመንግሥት ሌቦች ካልካቸው ውስጥ ስሜን አስወጣልኝ፤ አለዚያ እኔ የለሁበትም ብዬ ራሴን አወጣለሁ፤የሚል ሰው አይኖርም እንዴ? የምክር ቤቱ አባሎቹም ቢሆኑ የቀረበላቸውን ተሽዋሚ ሁሉ ሳይመረምሩ እየተቀበሉ በማጽደቃቸው ስሞታው እነሱን ይመለከት ይሆናል፤ አለዚያማ ጠቅላይ ሚኒስትሩ…
የኢትዮጵያን ሕዝብ ከወሮበሎችና ከሌቦች ይጠብቃቸዋል ተብሎ ተስፋ የጣለበት መንግሥት እንዲሁ በጅምላ፣ ሾላ በድፍኑ የሌቦች ዋሻ መስሎ እንዲታይ ማድረግ እጅግ ተስፋን የሚያስቆርጥ ነው፤ ተስፋ አስቆራጭ የሚሆንበትም ምክንያት ግልጽ ነው፤ የመንግሥት የበላይ የሆነው ጠቅላይ ሚኒስትር በብስጭት ስለ‹‹መንግስት ሌቦች›› ሲናገር ሌቦቹ ያየሉበትና የተቸገረ ይመስላል፤ ተስፋ የሚያስቆርጠው ለዚህ ነው፤ ‹‹ከሽብርተኞች ሙሰኞች›› ይብሳሉ እስከማለት የደረሰበት ያለምክንያት ነው ብሎ ለማመን ያስቸግራል፤ ለሕዝቡ ግን ትልቁ ችግር የሚሆነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹የመንግስት ሌቦች›› ያላቸውን ያነሣበት ምክንያት ሳይሆን የነዚያ ‹‹ሌቦች›› የተባሉት ሰዎች ሥልጣን ነው፤ ሥልጣኑን የሰጣቸው ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው፤ ተጠያቂነትና ኃላፊነት የጠፋበት ሁኔታ ውስጥ መግባታችንን የሚያመለክት በመሆኑ የሚያሳዝን ነው፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ውስጥ ሁለተኛው አስገራሚ ነገር ‹‹የሎጂክ›› ጉዳይ ነው፤ እኔ ሎጂክን ሕገ ኀልዮት እለዋለሁ፤ በትክክል የማሰብ ሕግ ማለት ይሆናል፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ መለስ ለምክር ቤት ሲናገር ያንድ ፖለቲካ ድርጅት ስም ጠርቶ አመራሩ በሽብርተኛነት ውስጥ እንዳሉበት ‹‹መቶ በመቶ እናውቃለን›› እያለ ደጋግሞ ገለጠና ሰዎቹ ያልተያዙትና ያልታሰሩበት ምክንያት ‹‹አስተማማኝ ማስረጃ ስለሌለ ብቻ ነው›› ብሎ ተናገረ፤ አቶ መለስ ይህንን የተናገረው በግል ለአንድ ጓደኛው ቢሆን የሚታለፍ ነበር፤ ግን የተናገረው በአደባባይ ብዙ የአገር ውስጥና የውጭ ምስክሮች ባሉበት፣ ሕግ አስከባሪዎች የሚባሉት ሁሉ (ፖሊሶች፣ ደኅንነት የሚባሉት፣ በየቡና ቤቱና መጠጥ ቤቱ የሚርመሰመሱት ሰላዮች፣ ዓቀብያነ ሕግ የሚባሉት፣ ዳኞች ተብለው የሚሰየሙት) እነዚህ ሁሉ አቶ መለስ ‹‹የመንግሥት ሌቦች›› ያላቸውን ጨምሮ ሰምተዋል፤ እንግዲህ አቶ መለስ ለወንጀለኛነታቸው መቶ በመቶ እርግጠኛ የሆነባቸውን ሰዎች ለመያዝና ለማሰር፣ ምስክሮችን በማሠልጠን ማስረጃ ለማዘጋጀትና አስፈላጊውን ፍርድ ለመስጠት የሚሸለሙበትን ሥራ ከአሁኑ አልጀመሩም ለማለት ይቻላል? አቶ መለስ ማስረጃ ቸግሮታልና አዘጋጅቼ ላቅርብለት ብለው የሚያስቡ ሰዎች የሉም ለማለት እንችላለን? በቅርቡ ርዕዮት ዓለሙና ሌሎችም አሥራ አራት ዓመት እስራትና ሠላሳ ሺህ ብር ቅጣት ሲፈረድባቸው አይቻለሁ፤ ምን አድርገው? በእኔ ግምት አደረጉ የተባለው ሁሉ ከወሬ አያልፍም፡፡
አቶ መለስ ሎጂክ የሚለውን ቃል ይወደዋል፤ ግን አይተዋወቁም፤ ቢያውቀው ይበልጥ ይወደው ነበር፤ ከመጀመሪያ ደረጃ ሎጂክ ውስጥ አንዱና ዋናው የቅራኔ ሕግ የሚባለው ነው፤ ይህ ሕግ የሚለው አንድ ነገር በአንድ ጊዜ መሆንም አለመሆንም አይችልም ነው፤ ይህንን የቅራኔ ሕግ መጣስ ወፍራም የአስተሳሰብ ግድፈት ነው፤ የመድረክ መሪዎች በአንድ ጊዜ ሽብርተኞች ሊሆኑና በማስረጃ አለመኖር ምክንያት ሽብርተኞች ላይሆኑ አይችሉም፤ አቶ መለስ ደጋግሞ መቶ በመቶ እርግጠኛ ነኝ የሚለው ይህንን ነው፤ የመድረክ መሪዎች መቶ በመቶ የተረጋገጠ ሽብርተኞች ናቸው፤ ግን ማስረጃ ስለሌለ ሽብርተኞች አይደሉም!
አቶ መለስ በእምነትና በእውቀት መሀከል ያለውን ድልድይ ብዙ ተመልካቾች ባሉበት ሳተው፤ ምናልባት በመንፈስ ቅዱስ የሚገለጥ እውነት ይዞ ይሆናል፤ ‹‹እግዚአብሔር ወልድ ከእግዚአብሔር አብ ቅድመ-ዓለም ያለእናት ተወለደ፤ እግዚአብሔር ወልድ ድኅረ-ዓለም ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለአባት ተወለደ፤›› ይህ ከእምነት የሚመጣ እውቀት ነው፤ ማስረጃ አይጠየቅበትም፤ ወደ እውቀት ዓለም ስንገባ ማስረጃ የለኝም እንጂ መቶ በመቶ አውኘቃለሁ ብሎ በአደባባይ መናገር ከእምነት ውጭ ምንም አላውቅም ማለት ነው፤ በተጨባጩ ዓለም እውቀት (ሳይንስ) ያለምንም ማስረጃ መቶ በመቶ እርግጠኛነት በጭራሽ፣ በፍፁም፣ በየትኛውም ዓለም፣ በማንኛውም ጊዜ አይታለምም፤ የሂሳብ ነገር ወዲህ ቢሉት አራት፣ ወዲያ ቢሉት አራት ነው፤ የብልጠት አቋራጭ መንገድ የለውም፤ የእድገቱ መመዘኛ እንደሽብርተኞች መመዘኛ ከሆነ ዘፋኙ ሁሉም ዜሮ ያለው ደረሰ ማለት ነው፡፡
መቶ በመቶ እርግጠኛ ባልሆንም አቶ መለስ ሀኪም የመሆን ምኞት ነበረው ሲባል የሰማሁ ይመስለኛል፤ እውነት ከሆነ እግዚአብሔር በጥበቡ ሕመምተኞችን ለማዳን መንፈስ ቅዱስን ልኮ አቶ መለስን ከዩኒቨርስቲ ወደጫካ አስወስዶታል ማለት ነው፤ አለዚያ መቶ በመቶ እርግጠኛ ሆኖ ያዘዘው መድኃኒት የመጡለትን ሕመምተኞች ሁሉ ለዘለዓለም እንዳያማቸው እያደረገ ያሰናብታቸው ነበር! የማሰናበቱ ሥልጣን በጠቅላይ ሚኒስትርነትም አለ፤ ፕሮፌሰር ዓሥራትና ዶ/ር ታየ የአርበኞች ግንባር መሪዎች መሆናቸው መቶ በመቶ ‹‹እውነት መሆኑ ታውቆ›› ታሰሩና ማስረጃው ስለጠፋ ከመንገድ እየተያዙ በማዕከላዊ ለምስክርነት ሠልጥነው ፍርድ ቤት በቀረቡ ጊዜ ተናግረዋል፤ በጊዜው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ እነዚህ በማዕከላዊ የሠለጠኑ ምስክሮች በፍርድ ቤት የሰጡትን ቃል በይፋ በአማርኛም፣ በእንግሊዝኛም አውጥቶታል፡፡
አቶ መለስ በምክር ቤት ለሚቀርቡለት ጥያቄዎች መልስ ሲሰጥ በጠያቂዎቹ ላይ ከማተኮርና እነሱን ለማሸማቀቅ ከመጣር ይልቅ ጉዳዩን በቀጥታ ቢያስረዳ ከብዙ የሚመዘገቡ ግን አላስፈላጊ ስሕተቶች ይድን ነበር፤ እግዚአብሔር እሱንም እኛንም ይርዳን፡፡

Comments
F (not verified)
Sun, 02/26/2012 - 00:48
Permalink
Congra
This is a masterpiece written by the prof ever. Let Zenawi swallow this. This needs to be translated into English and let his admirers like sachs and Stiglitz read it. We've been led by a ruler who cliams to have known everything buy knows nothing. He is a jack of all trade, a master of none.
getinet (not verified)
Sun, 02/26/2012 - 15:34
Permalink
Long live Professor Mesfin!
Let God give you many more years so you carry on striving, though mostly unsuccessfully, to inculcate sense into our senseless leaders…..
Yihun (not verified)
Sun, 02/26/2012 - 17:40
Permalink
We need such logical arguments
Yes. i said yes. PM Meles talks iressponsible politics. and responsibel politician could only argue the way H.E professor mesfin puts arguments. Thanks.
kidane (not verified)
Mon, 02/27/2012 - 00:41
Permalink
bravo mesfin
you are a true son of ethiopia.
long live for your flesh and sprit
Ermias (not verified)
Mon, 02/27/2012 - 11:39
Permalink
PDF
Please upload Number 176 edition in PDF , please,....please........ ስለ ኢትዮጵያ አምላክ ብላችሁ::
PDF (not verified)
Mon, 02/27/2012 - 14:03
Permalink
Prof. Mesfin
please upload the PDF and have too much thanks for prof. mesfin as he clearly show us the fallacies presented by the prime minister.
yes (not verified)
Mon, 02/27/2012 - 16:27
Permalink
prof. you are always true,
prof. you are always true, but they didn't listen you. may God keeps as a true son of ethiopia.
Anonymous (not verified)
Mon, 02/27/2012 - 19:34
Permalink
TANKS U VOICE OF ETIOPIA
TANKS U VOICE OF ETIOPIA
C'est moi B (not verified)
Tue, 02/28/2012 - 22:20
Permalink
God bless you.
I am pround of you professor. God bless you. If they listen ,that is enough to bec hanged but they are all arrogant that their sprite and physic is locked up to one and only one,i.e thier propoganda.
Yewegnesh (not verified)
Wed, 02/29/2012 - 09:31
Permalink
Prof
ፅሁፉን ሳነብ አንጀቴ ነው የራሰው፡፡ ፕሮፍ እውነታቸውን ነው፡፡ እኛ ሳናቅ ፖሊሲ ተቀርፆ ይጸድቅና ለምን ሲባል ‹‹ይቅርታ አዎ ልክ ናችሁ እናንተን ማሳተፍ ነበረበት›› ተብሎ እንደቀላል ነገር ይታለፋል፡፡ እንደገናም ‹‹የመንግስት ሌቦችም አሉ›› ይለናል፡፡ አንጀት ለመብላት ነው? ወይስ? ግራ የሚያጋባ ነው፡፡ ኢሃዲግ አዲስ ያመጣው ስትራቴጂ መሆን አለበት፡፡ ስህተቱን አደባባይ ላይ በማመን የተሰራውን ስህተት ከስህተት እንዳንቆጥረው ወይም ቀለል አድርገን እንደንወስደው እንዲሁም ጩኸታችንን እንድናቆም የሚጠቀምበት ዘዴ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ አልገባንም እንጂ እያታለለን ነው፡፡
tokuma (not verified)
Fri, 03/02/2012 - 03:00
Permalink
reply
One of the best challenging article for the guy who feels " he knows All". Thank you Prof. Mesfin
ABBY (not verified)
Sat, 03/03/2012 - 21:02
Permalink
Professor Mesfin, Peace and Happiness Always will be with you
That is an excellent article I love it. This article is well written with an experience, respectful and admirable professor in the country and in the world. I hope Ato. Meles and his supporters read this well written article maybe it may touch their brain and to come to their senses, but I doubt it because they are already have addicted with corruption drinks or pills and drunk for a long time over the Ethiopian people.
God Bless Ethiopian and the Ethiopian People
ፍሥሓ (not verified)
Tue, 03/06/2012 - 17:49
Permalink
"...እግዚአብሔር እሱንም እኛንም ይርዳን"?
"...እግዚአብሔር እሱንም እኛንም ይርዳን"? ነቢዩ ሳሙኤልን መሰሉኝ፣ ፕሮፌሰር። ይህም ለርስዎ ክብርዎ ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር እንዲህ የሚልዎ ይመስለኛል፦ "እስከማእዜኑ ትላሕዎ አንተ ለሳኦል ወአንሰ መነንክዎ..."
ስለኾነም ያለጥርጥር "ጸሎትከ ትገብእ ውስተ-ሕፅንከ።"
G/Michael (not verified)
Sat, 03/10/2012 - 13:21
Permalink
Yes I believe you are the icon for us
Dear Professor! I really appreciate every time on what you are doing! If our socalled leaders were serviving as a human being, they could have been read this article and stop to think on themselves! I am sorry we are not gifted to have such a wise leader! may be it could be "ëregeman" from one of our anscistors
regards
E.T (not verified)
Mon, 03/12/2012 - 13:37
Permalink
Yes I belive Profesoor you are our Dila lama
Pro please continue your criticized and comment on Ethiopian naive elite and politician, you are deserve it b/c you are the chain that fill the generation gap in our country. long life for our Dila lama
E.T (not verified)
Mon, 03/12/2012 - 13:12
Permalink
Profesoor you are our Dila lama(
Pro i think you are reach Abraham maslow last stage that is self actualized like Mandela and dila lama, so please pro continue your writing and criticized that is high value and essential for new generation. long life for our Dila lama.
E.T (not verified)
Mon, 03/12/2012 - 13:13
Permalink
Profesoor you are our Dila lama
Pro i think you are reach Abraham maslow last stage that is self actualized like Mandela and dila lama, so please pro continue your writing and criticized that is high value and essential for new generation. long life for our Dila lama.
Soltan (not verified)
Tue, 03/13/2012 - 08:02
Permalink
PqyebblOWVpKQJX
I cannot tell a lie, that rellay helped.
Cielo (not verified)
Tue, 03/13/2012 - 09:41
Permalink
AbhMsTyeIRYpxL
I don't know who you wrote this for but you hlpeed a brother out.
Add new comment