የትግራይ ወይስ የህወሓት የበላይነት?

ተመስገን ደሳለኝ
ከወር በፊት ስለኬኒያ ቆይታዬ በሁለት ክፍል እዚህችው ቦታ ላይ ማቅረቤ ይታወሳል፡፡ ሆኖም ከትረካዬ የተረፈውን ለዛሬው፤ ፅሁፌ መግቢያ ይሆን ዘንድ ትንሽ ልቆንጥርለት፡፡ ...አነሆ ሰዓቱ ከምሽቱ 4፡30 ነው፡፡ አንድ ለእናቱ በሆነው የናይሮቢ ጎዳና ላይ ከሀገሩ ከፍቶት በመሰደድ ኬኒያ መኖር ከጀመረ ከረም ካለ ወዳጄ ጋር እየተጓዝንበት ነው፡፡ (ይሄ ጎዳና ..ኃ/ስላሴ ጎዳና.. በመባል ይታወቃል፡፡ የናይሮቢ ትልቁ ችግር መንገድ ነው፡፡ የሚረባ መንገድ የላቸውም፡፡ ትንሽ ኃ/ስላሴ ጎዳና የተሻለ ነው) እናም ወሬያችንን እየሰለቅን ውብ በሆነችው ናይሮቢ እየተመነሸነሽን ..ወክ.. ስናደርግ አስቀድመን ያላስተዋልነው አንድ ሰው ከፊት ለፊታችን ገጭ አለ፡፡ በግምት እድሜው ከ45 የሚያልፍ ይመስላል፡፡ ይህ ሰው ..ወንድሞቼ ሳያችሁ ኢትዮጵያዊ እንደሆናችሁ ስላወኩ ነው.. አለን ጥርት ባለ አማርኛ አስከትሎም ስሙ ሰለሞን እንደሚባል እና በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት እትብቱ ከተቀበረባት አዲስ አበባ እንደተባረረ እና አሁን ችግር ላይ እንደሆነ አስተዛዝኖ ነገረን፡፡ እኛም በሰው ሀገር ላይ የተቸገረ ወንድማችንን በማግኘታችን ተደስተን የተጠየቅነውን ጥያቄ መለስን ..አይዞን.. ደግም በሀገራችን መሰባሰባችን አይቀርም.. ተባብለን፤ ተመራርቀን የኃ/ስላሴ ጎዳናን ይዘን ወደ ፊት ነጎድን...
እየውልህ ኢትዮጵያዊ ማለት ይሄ ነው ..ወንድሞቼ ሳያችሁ ኢትዮጵያዊ እንደሆናችሁ ስላወኩ ነው.. ሰለሞን እንዳለው ማለቴ ነው፡፡ ለዚህም ነው ዛሬም ድረስ ..አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ..... ሲሉኝ የማይዋጥልኝ፤ ያውም በኢትዮጵያ ምድር እና በኢትዮጵያዊ፡፡ እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡ አንተም ኢትዮጵያዊ ነህ፡፡ አንተ አማራ ነህ፤ አንተ ትግሬ ነህ የሚሉህን እርሳው፡፡ ይሄ ፖለቲካ እንጂ፤ የአንተ ደም እና አጥንትህ አይደለምና፡፡ ደግሞም ኢትዮጵያዊነትህ ዝም ብሎ ከሜዳ የተገኘ እንዳይመስልህ፤ ምንጅላቶችህ እና ቅድም አያቶችህ አጥንታቸውን ከስክሰው እና ደማቸውን አፍስሰው ያቆዩልህ ነው፡፡ ለምን ይመስልሃል አፍሪካውያን ዘመዶችህ ..ኢትዮጵያኒዝም.. ሲሉ የነፃነታቸውን ትግል የሰየሙት? አየህ ኢትዮጵያዊነት ማለት ይሄ ነው፡፡ ያውም ከአንተ አልፎ ለሌሎች የሚተርፍ፡፡ ብታምንም ባታምንም የ..ነፃነት.. ሌላኛዋ ስም ..ኢትዮጵያ.. ማለት ነው፡፡ እኔ የምለው ካልተዋጠልህ ብትፈልግ የኑዋሚን ንኩርማን፤ አሊያም የኬኔት ካውንዳን ዘመዶች ጠይቅ፡፡ ረጋ ብለው ..ኢትዮጵያዊነት ማለት..... ሲሉ ጀምረው ብዙ ይተርኩልሃል፡፡ እስቲ የአብዛኛውን አፍሪካዊ ሀገር የባንዲራ ቀለምም ልብ ብለህ ተመልከት? አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀለም ታገኝበታለህ፡፡ ያን ጊዜ እኔ የምለው በደንብ ይገባሃል፡፡ እንዳልኩህ ይሄ ግን ዝም ብሎ የተገኘ ወይም ወፍ ዘራሽ እንዳይመስልህ፤ አያት ቅድመ አያቶችህ እንዲህ ብሎ ዘፈነው፡-
..አጥንቴም ይከሰስከስ
ደሜም ይፍሰስላት፣
ይች ሀገሬን ጭራሽ
አይደፍራትም ጠላት..... ዳር ድንበራቸውን ከደፈረ ሁሉ ጋር ተፋልመው ነው፡፡
አሁን ግን ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆነ፤ ዛሬ አንተ ኢትዮጵያዊ ሳትሆን አማራ ወይም ትግሬ አሊያም ኦሮሞ... ነህ ተባለ፤ አንተም ወይ አምነህ ወይ ፈርተህ ተቀብለከዋል፡፡ ግን እመነኝ ተሳስተሃል፡፡ እነሱ አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ፣ ወላይታ፣ ሲዳማ፣ ሱማሌ፣ አኝዋክ፣ኑዌር፣ አፋር... የሚሉህ ኢትዮጵያዊ መሆንህን ዘንግተውት ሳይሆን ከፋፍለው አድክመው ለመግዛት ሲያመቻቹ ነው፡፡ "ትግሬ ተጠቀመ" የሚሉህንም እርሳው፡፡ የተጠቀመው የህወሓት ካድሬ እንጂ የትግራይ ሰው አይደለምና፡፡ ይሄ ደግሞ የአማራ ወኪል ነኝ የሚለው ጋር ብትሄድም የብአዴን ካድሬ እንደተጠቀመ ታያለህ፡፡ የኦህዴድ ካድሬም እንዲሁ፡፡ በተቀረ አቢ አዲ፣ ሽራሮ፣ እደገ ሀሙስ፣ ማይጨው፣ መሆኒ፣ ኮረመ፣ አዲ ነበርዲ፣ ሀውዜን፣ ራማ፣ አደጋ አርቢ፣ ፋጢ፣ አዲጉደም፣ ውቅሮ፣ ዛላንበሳ፣ አዲግራት፣ አድዋ፣ አክሱም፣ ፣ ማረይ፣ መቀሌ... ሂድ ያጡ የነጡ ድሆች ፈሰውበት ታያለህ፡፡ እነዛ የዋህ እና ሩህሩህ የትግራይ እናቶች በችግር ተቆራምደው ስታይ ..ጊዜው የትግሬ ነው.. የሚሉት መሰሪ ፖለቲከኞች መሆናቸውን ትረዳለህ፡፡ ወንድሜ.. ጊዜው የትግሬ ሳይሆን የገዥው ፓርቲ አመራሮች እና እፍኝ የማይሞሉ ዘመዶቻቸው ነው፡፡
.....ሰዎቹ.. የዋዛ እንዳይመስሉህ፡፡ ገና ከበረሃ ሲነሱ እንዲህ እንደዛሬው በየጎጡ ካልከፋፈሉን፤ በዴሞክራሲያዊ መንገድ እንጂ በአምባገነን ስርዓት ሊፈነጩ እንደማይችሉ ስለተረዱ በቋንቋ ላይ የተመሰረተ ፌደራሊዝምን ቀመሩልህ፡፡ እስቲ ናይጄሪያ ሂድ.. እድሜ ዘመናቸውን በብሔር ተቧድነው ደም ሲፋሰሱ በቅራኔ የኖሩ እነ ፉላኒ (በቁሮቃሽ..፣ ቲቪ (ማሽባ..፣ ዮሩባ (ሥቄቈበሯሮ..፣ ሀውሳ (Hausa)... የሚባሉ ብሄሮች ነበሩ፡፡ ዛሬ ግን የናይጄሪያ ፌደራሊዝም በመልካምድር (Geographical) ላይ የተመሰረተ እንጂ በሚናገሩት ቋንቋ ላይ የተመሰረተ አይደለም፡፡ እንግዲህ እግዜር ያሳይህና.. በናይጄሪያ የሚኖሩ ብሄሮች ቅልጥ ባለ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ያለፈ ታሪክ ቢኖራቸውም ዛሬ የሚወዷት ሃገራቸው በብሔር ላይ የተመሰረተ ፌደራሊዝም እንድትመራ ግን አልፈለጉም፡፡ ከመከፋፈል አንድነት እንደሚበልጥ በደንብ ያውቃሉና፡፡ ዛሬ በናይጄሪያ የስነ-ልቦና ጦርነትም (Psychological warfare) የለም፡፡ እዚህ ግን ሞልቶአል፡፡ ..የቡርቃ ዝምታ.. የሚባለውን መጽሐፍ ብታነበው ጥሩ ማስረጃ ይሆንልሃል፡፡ ውስጥ ውስጡንም ትግሬ ተጠቀመ፤ የትግራይ ክልል በለፀገ እያሉ የሚያስወሩት ለእኔ ግለሰቦች አይመስሉኝም፡፡ ሆነ ብለው ይህንን እንዲያደርጉ የሳይኮሎጂካል ዋር ጄነራሎች ተመድበውብን ነው ብዬ ነው የማስበው፡፡ እርስ በእርስ በጥርጣሬ እና በስጋት እንድንተያይ ለማድረግ፡፡ እኛ ከተከፋፈልን፤ በአይነ ቁራኛ ከተጠባበቅን ለብሔራዊ አምባገነንነት፣ ለብሔራዊ ጭቆና፣ ለብሔራዊ አፈና፣ ለብሔራዊ ድህነት፣ ለብሔራዊ ድርቅ፣ ለብሔራዊ ችጋር፣ ለብዙ ብሔራዊ ችግሮች... የእድሜ ማራዘሚያ ኪኒን እንደማለት ነው፡፡ በግልባጩ ለእነዚህ ብሔራዊ ችግሮች መቃብር መውረድ ደግሞ በወንድማማችነት መተሳሰር እና መፋቀራችን እንደሆነ እነዚህ ሰዎች ጠንቅቀው ያውቁታል፡፡
...በብሔሮች መካከል የሚከሰት ጠብ እና ግጭት ምን ያህል የከፋ እንደሆነ ለማወቅ ከፈለክ የሁቱ እና ቱትሲን ታሪክ ፈልገህ አንብብ፡፡ ማንበብ ከደበረህም “Hotel Rwanda” የሚል ፊልም ወይ ተከራይተህ ወይ ገዝተህ ተመልከት፡፡ ያን ጊዜ ሁሉም ነገር ይገባሀል፡፡ ኢትዮጵያዊነት ምን ያህል አስፈላጊያችን አንደሆነም ትረዳለህ፡፡
አንድ ብሔርን ከሌሎች የበለጠ ተጠቃሚ አድርጎ ማቅረብ ወይም ሌሎች ብሔሮችን በጥላቻ እና በበታችነት የሚያይ አድርጎ ማቅረቡ የዳያቢሎስ ስራ እንዳይመስልህ፤ የፖለቲካ ስራ ነው፡፡ ትግራይ ብትሄድ ስለፖለቲካ ቀርቶ ስለውሃ ችግር ቅሬታ ማቅረብ እንኳ መንግስትን መቃወም ተደርጎ ነው የሚወሰደው፡፡ የመፃፍም ሆነ በነፃ የማሰብ መብት በማንኛውም መለኪያ ቢለካ ከትግራይ አዲስ አበባ በእጅጉ የተሻለ ነው፡፡ (ከትግራይ የተሻለ ነው አልኩህ እንጂ አዲስ አበባ የነፃ አየር መተንፈሻ ነው አላልኩህም)
የትም ብትሄድ ፖለቲካ የተከበረ ስራ ነው፡፡ በአንተ እና በሌሎች ጥቂት ሀገራት ደግሞ ፖለቲካ አስፈሪ አውሬ ነው፡፡ ምእራባውያኖቹ ፖለቲካ ሲሉ የተሻለ ብቃት፣ ንቃት፣ አማራጭ ፖሊሲ... ማለት ሲሆን፤ በአንተ ሀገር ደግሞ ፖለቲካ ሲባል ክላሽ እና ቦንብ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡ እናም የቱንም ያህል ተከራክረህ አሸናፊ ብትሆን፤ ክርክር እና ያገኘኸው የህዝብ ደጋፍ መትረየስን አያሸንፍም ትባላለህ፡፡ የለም መትረየስም በሃሳብ የበላይነት ይሸነፋል ካልክ ደግሞ በእከሌ ብሔር ላይ ጭፍጨፋ ሊያካሂድ አስቦአል ትባልና ህገ-መንግስቱን በኃይል መናድ ወይም ሀገር ክደት በሚል ክስ ትከሰሳል፡፡ ...ገና ከመነሻው በሌሎች ሀገራት ፖለቲካ ደም አያፋስስም፤ ማንንም ከማንም አያጋጭም፡፡ እዛ የሚጋጩት አማራጭ ፖሊሶዎች እና አይዶሎጂ ላይ ነው፡፡ ለምሳሌ በሚቀጥለው አመት በሚደረገው የአሜሪካን ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ኦባማን ከስልጣን ለማውረድ ጫካ የገባ ኃይል እንደሌለ ምዬ ተገዝቼ እነግርሃለሁ፡፡ እዛ ሰውን ሰው የምታደርግ አንድ እለት አለች፡፡ የምርጫ ቀን የምትባል፡፡ በቃ ያን እለት ማክዶናልድ በርገርህን እየነጨህ፤ በዋሌትህ በያዝካት ..ካርድ.. ኦባማን ..በቃክ.. ትለዋለህ፡፡ ከወደድከውም እንደምርጫህ ነው፡፡ እዚህ ግን...
እዛ አንዱን ብሔር በሌላው ብሔር ላይ የሚያነሳሱ ..ጊንጥ ሰላዮች.. እና ..ሆድ አምላኩ ካድሬዎች.. ወይም ራሳቸውን ልማታዊ ሲሉ የሰየሙ ጋዜጠኞች የሉም፡፡ እንኳን የሃበሻ ምድር ልጆች፤ እንኳን እኛ ኢትዮጵያውያኖች ቀርቶ ከደች (ሆላንድ) ተጉዘው ደቡብ አፍሪካን በቁጥጥራቸው ስር ያዋሉ ሰዎች “Nationalist Afrikaner Party” የሚባል አቋቁመው እንደነበረ ከታሪክ ትረዳለህ፡፡ እዚህ ግን ህወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደኢህዴን... ይሉሃል፡፡ እናም አንዳንድ የውሃኖችንም በሌላ ብሔር ላይ ..እንዲያፈጡ.. ያስገድዳቸዋል፡፡ ወይም ይገፋፉአቸዋል፡፡ ይሄ ግን የተሳሳተ አመለካከት ነው፡፡ ይሄ ከጥቂት አምባገነኖች በስተቀር ለማንም አይጠቅምም፡፡ ወደድክም ጠላህም ለኢትዮጵያ ትንሳኤ አንድነት እንጂ ልዩነት ዋጋ የለውም፡፡ ደግሞም ባለጊዜ እና ኢንቨስተር በሆኑ ፖለቲከኞች እና በብሔር መካከል ያለውን የመንግስተ ሰማያትን እና የሲኦልን አይነት ልዩነት ጠንቅቀህ ተረዳ፡፡ ያንጊዜ ነው ..ጎበዝ.. የምትሆነው፡፡ ያንጊዜ ነው ..ኃይለኛ.. የምትሆነው፡፡ እናም ያንጊዜ ነው ኢትዮጵያዊ የምትሆነው፡፡ ያንጊዜ ነው በናይሮቢው የኃይለስላሴ ጎዳና ..ወንድሞቼ ሳያችሁ ኢትዮጵያዊ እንደሆናችሁ ስላወኩ ነው.. የሚለውን አይነት ውብ ድምፅ ስትሰማ ሃሴት የምታደርገው፡፡ እናም መቼም ቢሆን መቼ የትግሬ የበላይነት አለ ብለህ እንዳትሸወድ ፡፡ ያለው የህወሓት አመራሮች የበላይነት ነውና፡፡ ከዚህ ውጭ የትግራይ እናቶች እና አባቶች፤የትግራይ ወጣቶች እና ህፃናቶች የአንተን ያህል ስለሚበሉት እና ስለሚጠጡት የሚጨነቁ ምስኪኖች ናቸው፡፡

Comments

thats true tigray did not get any extra benefit.you can see extrem poverty all over the region.if you go to raya alamata chercher mekelle howzien abyadi negash wokro adigrat enticho adwa axum shire wolkaite mysebri tselemti tsegede humera kafta maycadra you will get true needy ethiopian tegaru. who are willing to die to our beloved countray ethiopia but not to aka weyane.tigray the land of alula,yohannes,awalom abebe aregay,hayelom mussie amora and all of the martryars who die to see the civilaized democratic and prosperaous ethiopia but they are very lucky to not see this tyrant regiem.ethiopia ni zelealem tiniber.

TEMSEGEN egzeyabher yesteh. kenzehe sewe belawoche yetbekeh

Dear Temesgen,most have not got the courage to swallow this truth.I myself has witnessed the misery of the people of Tigray.But when I talk to people about it,they don't even need to hear it;because they are victims of the hatred and dividing strategy of the regime.I think we should genuinely analyse what is going on...remaining far away from emotions.

Add new comment

Filtered HTML

  • Web page addresses and e-mail addresses turn into links automatically.
  • Allowed HTML tags: <a> <em> <strong> <cite> <blockquote> <code> <ul> <ol> <li> <dl> <dt> <dd>
  • Lines and paragraphs break automatically.

Plain text

  • No HTML tags allowed.
  • Web page addresses and e-mail addresses turn into links automatically.
  • Lines and paragraphs break automatically.